የግኖስቲክስ ትምህርትና የዘመኑ ምንፋቃና
የክርስቶስ ሃይማኖት በእምነት በተስፋና በፍቅር የተመሠረተች አንዲት ናት፡፡ ከእርሷ የተለየ ሌላ ሃይማኖት የለም፡፡ የጽሑፍ መመሪያዋም በመንፈስ ቅዱስ እየተመሩ ነቢያት የተናገሩት ጌታ ራሱ ያስረማረውና ሐዋርያት የሰበኩት ነው(ኤፌ 4፥ 5 2ኛ ጴጥ 1፥20 ዕብ 1፥1-2) ይህን እውነት ይሽሩ መስሎቸው በተለያየ ዘመን የተነሱ መናፋቃን ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ለማፍረስ ወይም ለማደስ መንቀሳቀሳቸው እሙን ነው፡፡ እነዚህ መናፋቃን ታዲያ ስልታቸው ይለያይ እንጂ ትምህርታቸው ቀድሞ የተገለጠና የተወገዘ ነው፡፡ በተለይም ቤተ ክርስቲያን ከምትቀበላቸው ከሦስቱ ጉባኤያት በኋላ(ከጉባኤ ኤፌሰን በኋላ) የተደረጉ ጉባኤያት ቀድሞ የተወገዙ የምንፍቅና ትምህርቶችን እውቅና የሰጡ እንጂ አዲስ ምንፍቅና የተንጸባረቀባቸው አይደለም፡፡ የዘመናችን ምንፍቅናን ስንመለከት ይህንኑ ተመሳሳይ ሐቅ እንገነዘባለን፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በተለያየ ጊዜ የቤተ ክርስቲያን አባቶች የወሰኞቸውን ውሳኔዎች ለመሠረተ እምነቷ (ለዶግማዋ) እንደምንጭነት ትጠቀምበታለች፡፡ ይህም የሆነበት ምክንያት በዘመኑ በነበሩት አባቶች ሐዋርያነ አበው ለመናፋቃኑ ትምህርት በሚገባ መልስ ስለተሰጠና ይህም መልስ ለኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያንን አስተምሕሮ ምንነት ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ በመሆኑ ነው፡፡ የአባቶች ትምህርት ለዘመኑ መናፋቃን መልስ የሚሆን ነውና፡፡ በዚህ ዘመን ያለ ሰው ለመናፋቃን መልስ ለመስጠት የአባቶቹን ትምህርት በሚገባ ማጥናት በራሱ በቂ ነው፡፡ የዚህም ጹሑፍ ዓላማ የመናፍቃኑን ምንነት ምንፍቅናቸውንና የቤተ ክርስቲያን አባቶችን መልስ ማስገንዘብ ነው፡፡ ከዘመነ ሐዋርያት አንስቶ በተለይ የአሕዛቡን ፍልስፋና ከክርስትና ጋር በመቀየጥ(ይህ ቀድሞ የአሕዛቡን ፍልሰፍና ከአይሁድ እምነት ጋር በመቀላቀል የተጀመረ ነው) የተሳሳተ ትምህርት ከምትሐት ጋር በመደባለቅ ብዙዎችን ካሳቱ ልፋፎች መካከል ግኖስትሲም ማኒኬይዝምና የጸረ ኒቂያ አባቶች ትምህርቶች ተጠቃሽ ናቸወ፡፡
የግኖስቲኮች ትምህርትና ምንፍቅና
ግኖስቲኮች ማለት አዋቂዎች የእወቀት ሰዎች ማለት ነው፡፡ ስያሜውን የወሰዱት ግኖሲስ እወቀት ከሚለው ከጽርዕ ቋንቋ ነው፡፡ አዋቂ ነን ለማለት ስያሜውን በራሳቸው አውጥተውታል፡፡ ትምህርታቸውን ግኖስቲሲዝም ይባላል፡፡ አእምሮታዊ እውቀታዊ እንደ ማለት ነው፡፡ መዳን በማወቅ እንጂ በእምነት አይደለም ባዮች ናቸው፡፡ እነዚህ ግኖስቲኮች ክርክራቸውን የሚያቀርቡት መጽሐፍ መነሻ አድርገው ሳይሆን በልብ ወለድ ፍልስፍና ነበር፡፡ ይህም ትምህርታቸውን ማስተማር የጀመሩት የመጀመሪያ ክርስቲያኖች በብዛት በሚገኙባቸው ቦታዎችና ከተሞች ናቸው፡፡ የግኖስቲኮችን አስተሳሰብ ያመነጩት ከቤተ አሕዛብ ከተመለሱት ክርስቲያኖች ውስጥ ነበር፡፡ በመሠረቱ የአይሁድና የፅርዓውያን እምነትና ባሕል ፈጽሞ የተለያየ ነው፡፡ ይህም አይሁድ ሰማይና ምድርን(ዩኒቨርስን) ሁሉን እጅግ ውብ አድርጎ ፈጠረ ብለው ሲያምኑ ፅርዓውያን ግን የተራቀቀ መንፈሳዊ ነገር ሁሉ ከረቀቀውና ከሉዓላዊው አምላክ ጋር ግንኙነት ስላለው መልካም ነው የተፈጠረውና ግዙፍ የሆነው ነገር ግን ርኩስና የክፋት ሁሉ ምንጭ ነው ስለሆነም ከረቂቁና ከሉዓላዊው አምላክ ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት የለውም የሚል ነው፡፡ ይህን ትምህርት በመቀላቀል የተጀመረው የግኖስቲካዊይን የምንፍቅና እርምጃ በክርስትናው መሠረተ እምነት(ዶግማ) ላይም ተመሳሳይ የፍልስፋና ትምህርት በመቀላቀል ምንታዌነትን(dualism) አስተምረዋል፡፡ እነዚህም ሁሉ ጋር ከብሉያትና ከሐዲሳት መጽሐፍት አንዳንድ ለአስተምሮቸው(ለአስተሳሰባቸው) ምቹ የሆነውን ይመርጣሩ እንጂ በዋነኝነት መነሻቸው ከዚህ ቀደም በዓለም የታወቁ ፈላስፋዎች ትምህርት ናቸው፡፡ ይህ የግኖስቲክስ ትምህርት እንዳመቺነቱ እንደጊዜው ሁኔታ እየተከለዋወጠ የክርስትናን ትምህርት በመቀላቀል በክስርትና ትምህርት ያልበሰሉትን ክርስቲያኖች የሚያታልል ነበር፡፡ መነሻቸውም ጥንታዊያኑ ፈላስፎች ፕሉቶ አርስቶትል ፒታጎራ ኤፊቆርስ የመሳሰሉት ናቸወ፡፡
የግኖስቲኮች ትምህርት /አመለካከት/
• በሁሉም ነገር ፍጹም (all perfect) በሆነውና በሁሉም ነገር ጎዶሎ(all imperfect) በሆነው መካከል ምንም ዓይነት ግንኙነት ሊኖር አይችልም ስለዚህም በእግዚአብሔር (በሁሉ ነገር ፍጹም በሆነውና) በግዙፉ ዓለም(በሁኩ ነገር ጎዶሎ ) በሆነው መካከል ምንም ዓይነት የቅርብ ግንኙነት የለም
• ሌላው ትምህርት ከፕላቶ ፍልስፋና የተቀዳ ሲሆን ይኸውም እግዚአብሔር መጀመርያ መናፍስትን ፈጠረ እነዚህ መናፍስትም ከእነርሱ ያነሱ መናፍስትን ፈጠሩ እነዚህም ሌሎች ከእነርሱ የሚያንሱ መናፍስትን ፈጠሩ በመጨረሻም አነስተኛው መንፈስ ይህን ዓለም ፈጠረ ይላሉ (ይህም ከላይ ከጠቀስነው ነጥብ አንጻር በእግዚአብሔርና በግዙፉ ዓለም መካከል ምንም ዓይነት ግንኙነት የለም ከሚለው ትምህርት ጋር እንዲገናኝላቸው ያዘጋጁት ትምህርት ነው)
• ቁሳዊው አካል በባሕርዩ መጥፎና ክፉ ነው የእርኩሰትም ሁሉ ምንጭ ነው፡፡ ሰው ይጸድቅ ዘንድ የሥጋውን አስተሳሰብ ለፍቃደ ነፍሱ ብቻ ማስገዛት አለባት፡፡
• ክብር ይግባውና ስለክርስቶስም ሲናገሩ ክርስቶስ በእግዚአብሔርና በዓለም መካከል ገብተው ዓለምንና እግዚአብሔርን ከሚያቀራርቡ(የሚያስታርቁ) አነስተኛ መናፍስት አንዱ ነው ይህንንም ዓለም ያስታርቅ ዘንድ ኢየሱስ የሰውን ሥጋ የለበሰ መስሎ ታየ እንጂ አማናዊ ሥጋን ተዋሐዶ ሰው አልሆነም ብለው ብለው ያምናሉ
• በግኖስቲኮች አስተሳሰብ ሁለት አማልክት አሉ አንዱ ደግ ሲሆን አንዱ ክፉ ነው ይላሉ፡፡
• መዳን በማወቅ እንጂ በእምነት አይደለም ይላሉ፡፡
• መለኮታዊ ቃል አማናዊ ሥጋን ተዋሐደ ብለው አያምኑም፡፡
• ለዳነች ነፈስ የሚጎዳት ምንም ዓይነት ብናደርግ አያረክስም። በለው ያስተመራሉ ሰው በመባል የሚታወቀውና ሰብአዊ ክብርም ያለው ነፍስ እንጂ ሥጋ አይደለም ሥጋ ግን በባሕርዩ ለጥፋት የተፈጠረ ነው ይላሉ፡፡ቅዱስ ጋብቻን ይቃወማሉ ይህንን የፍልስፍና ትምህርት የጀመረው ሲሞን መሠሪ ሲሆን በቤተክርስቲያን ታሪክ የመጀመሪያው ርእሰ መናፍቅ ነው፡፡ ሌሎችንም ጀሌዎች አፍርቷል፡፡ ከግኖስቲኮች በሶርያ ሲሞን መሠርይ(ሲሞን ዘ ሶርሰረር) ሜናንድሮስ ሳቶርኒስ ኬሪንቶስ ኒቄላዎስ በእስክንድርያ ባስሊድስና ቫለንቲኖስ(ቫለንድዮስ) በትንሾ እስያም መርቅያን ተጠቃሾች ናቸው፡፡ የግኖስቲክስ ትምህርት በጽንሰ ሐሳብ አንዱ ከአንዱ ትምህርት ቢለያይም ከላይ የዘረዘርናቸው መዘርዝሮች የሁሉም መናፋቃን ገላጮች ናቸው፡፡ ትምህርታቸው በዘመኑ በነበሩት አባቶች ጽኑ ተጋድሎ(ቅዱሳን አባቶች) የከሸፈ ቢሆንም ርዝራዡ ግን ለብዙ ዘመናት የቆየ ነው፡፡ ይህ የግኖስቲክስ ትምህርት በጊዜው ለነበረው የተለያየ አመለካከት ተቀያይጦ የተቀረጸ የተለያዩ ሕዝቦች ባሕል እምነትና ወግ ከክርስትና እምነት ጋር በመደባለቅ ትክክለኛውን ትምህርት በማስረሳት በተለይም የዋሆችና ዝቅተኛውን የሕብረተሰብ ክፍል ለማታለል ብዙ ጥረት ቢያደርጉም ትምህርቱ በራሱ ወጥነት የሌለውና ድብልቅ በመሆኑ በፍጥነት በሦስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ሊጠፋ ችሏል፡፡
የግኖስቲክስ ትምህርትና የዘመኑ ምንፍቅና
1. በቤተ ክርስቲያን ትምህርት መሠረት ክፋትና ስሕተት እግዚአብሔር የፈጠራቸው አይደሉም ሌላም ፈጠሪ የላቸውም ከሰው ባሕርይ ጋር ዝምድና የላቸውም ክፋትና ተንኮል የተገኙት ሰው የእግዚአብሔርን ትእዛዝ በዘነጋ ጊዜ ነው(ዘፍ 3፥17-20 ሄኖ 37፥18) የሰው ልጅ እንደቤተ ክርስቲያን አስተምሕሮ ሙሉ ነጻነት(free will) ያለው ፍጥረት ነው፡፡ የዮሐንስ ካልቪን (1509-1564) ግን የሰው ልጅ እንደቤተ ክርስቲያን አስተምሕሮ ሙሉ ነጻነት(free will) ያለው ፍጥረት ብላ የምታምን ብትሆንም ከግኖስቲኮችም በኋላም ቢሆን በዮሐንስ ካልቪን አማካኝነት አስቀድሞ መመረጥ የሚለውን የኢስጦይኮችን ፍልስፍናን መጽሐፋዊ በማድረግ በመስበክ ብዙዎችን ከእውነተኛው ጎዳና አውጥቷል፡፡ ይህም ትምህርት የሰው ልጅ ነጻ ፍጥረት እንዳልሆነ በተዘዋዋሪም መንገድ ቢሆን ማስተማር ነው፡፡ ይህ ትምህርት ታዲያ በመሠረተ እምነት ላይ ብዙ ተፋልሶ የሚፈጥር ነው፡፡ ይህ ኑፋቄ አዲስ ባይሆንም በዮሐንስ ካልቪን አማካኝነት በፕሮቴስታንቱ ዓለም የታወቀ ትምህርት ነው፡፡ የይህም ትምህርት የግኖስቲኮች ነው
2. የቤተ ክርስቲያንን ሥርዓትና ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያንን (sacraments) ማንቋሸሽ የግኖስቲኮች መለያ ጠባይ ነው፡፡ ግኖስቲኮች ካህናትን የሚሰድቡ ጥምቀትን የሚንቁ ነበሩ የዘመኑ መናፍቃንም ካህናትን የሚንቁ ምሥጢረትም ለመዳን አስፈላጊ አይደሉም ብለው የሚሞገቱ ናቸው፡፡
3. ለዳነች ነፍስ የሚጎዳት ምንም ዓይነት የኃጢያት ድርጊት የለም በለው የሚያስተምሩት ግኖስቲኮች ለዘመኑ መናፍቃን ኑፋቄ መሠረት የጣለ ነበር፡፡ በጸጋው ድነናል ጸድቀናል ስዚህም መንፈሳዊ ትሩፋት አይስፈልግም ዓይነት ኑፋቄ ምንጩ ግኖስቲኮች ናቸው
4. ግኖስቲኮች በተመሳሳይ ርዕሰ ጉዳይ ላይ ተመሳሳይ አቋም የሚያንጸባርቁ አልነበሩም፡፡ ይህም ጠባያቸው ከዘመኑ መናፍቃን ጋር በእጅጉ የሚያመሳስላቸው ነው፡፡
5. ክብር ይግባውና ስለክርስቶስ ግኖሲቲኮች ሲናገሩ ክርስቶስ በእግዚአብሔርና በዓለም መካከል ገብተው ዓለምንና እግዚአብሔርን ከሚያቀራርቡ(የሚያስታርቁ) አነስተኛ መናፍስት አንዱ ነው፡፡ ይህንንም ዓለም ያስታርቅ ዘንድ ኢየሱስ የሰውን ሥጋ የለበሰ መስሎ ታየ እንጂ አማናዊ ሥጋን ተዋሐዶ ሰው አልሆነም ብለው ብለው ያምኑ ነበር፡፡ ይህንን ትምህርት ልብ ብሎ የሚያስተውል ሰው ክርስቶስን አማላጅ ማድርግና ከባሕርይ አባቱ ከአብ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ መነጠል የተጀመረው በዚህ ዘመን መሆኑን ይረዳል፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ይቆየን
22.04.2008 ዓ.ም.