የቅድስት ቤተ ክርስቲያን መሠረተ
እምነት(ዶግማ) ምንጮች መካከል መጽሐፍ ቅዱስና ትዉፊት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ቅዱሳን መጻሕፍት በቤተ ክርስቲያን ትልቅ ቦታ(ሥፍራ)
አላቸው፡፡ አሥራው መጻሕፍት ሙሉዕ የሚያደርገው ትዉፊት እንደሆነ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ታስተምራለች፡፡
ትዉፊት ስንል በቃል የሚተላለፈውን
ትውፊት፣የቅዳሴ መጻሕፍት የአበው ጽሑፎች ቀኖናዎች በጉባኤያት የተወሰኑ ውሳኔዎች (የሃይማኖት መግለጫዎች) እንዲሁም የቤተ ክርስቲያን
አገልግሎቶች(Practices in the church) የሚያጠቃልል ነው፡፡
የቤተ ክርስቲያን ትውፊት ብዙ
ቁም ነገሮችን የያዙ ናቸው፡፡ ሁሉም በመጽሐፍ ቅዱስ(አሥራው መጻሕፍት) ያለና የተገለጠ(የተጻፈ) ነው ለማለት ይቸግራል፡፡ መጽሐፍ
ቅዱስ ራሱ ምሉዕ እንዳልሆነ ይገልጻል፡፡(ዮሐ 20፥30 ዮሐ 21፥25) ትውፊት ምንጊዜም የመጽሐፍትን ምሥጢር ነገረ ድኅነትን ነገረ
ቅዱሳንን ነገረ ክርስቶስን ሌሎችን የቤተ ክርስቲያን ትምህርቶች ጋር የሚጣጣም እንጂ የሚቃረን መሆን የለበትም፡፡
ትውፊት
ከመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ቀጥሎ ስለ ክርስትና የሚነግረን እና ከቅዱሳን ሐዋርያትና ከአባቶቻችን የተቀበልነው ትምህርት ነው፡፡ ትውፊት በመጽሐፍ ቅዱስ ያልተጻፉ ነገር ግን ፈጽሞ ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጪ ያልሆኑ ጽንሰ ሐሳቦችን፣ ታሪኮችን የያዘ ነው፡፡ ትውፊት ቅዱሳት መጽሐፍትም ከመጻፋቸው በፊት የነበረ ነው፡፡ ይህም በቃልም ሆነ መጽሑፍ የሚወርሱት ነው፡፡
ለምሳሌ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እሑድን የክርስቲያን ሰንበት እንደሆነ ታስተምራለች
በዚህ ወቅት ነው ክርስቲያኖች ሁሉ ተሰብስበው እግዚአብሔርን የሚያገለግሉት ሥጋውን ደሙን የሚቀበሉት ይህ ታዲያ በመጽሐፍ ቅዱስ
አልተጻፈም በትውፊት ያገኘነው ነው፡፡
ትዉፊት ከመጽሐፍ
ቅዱስ በፊት ነበረ
ትውፊት ከመጽሐፍ ቅዱስ ቀዳሚ ነው፡፡ ትውፊት ከአባታችን አዳም ጀምሮ የነበረ ነው፡፡
እስራኤል በተጻፈ ሕግ ከመመራታቸው በፊት ከትውልድ ትውልድ እየተላለፈ ሲመራቸው የነበረ ትውፊት ነው፡፡
ለአብነትም
1.
በኦሪት ዘፍጥረት አቤል ለእግዚአብሔር ንጹሕ መስዋዕት አቀረበ(ዘፍ. 4፥4) ታዲያ
አቤል መስዋዕት ማቅረብ እንዴት አወቀ? እምነቱንስ ከየት አገኘው ብለን ብንጠይቅ ያለጥርጥር ከአባታችን ከአዳም እንዳገኘው መናገር
ይቻላል፡፡ ይህም የሆነው በትውፊት ነው አቤል ይህንን ያደረገው ሙሴ ስለመስዋዕት ከመጻፉ 1400 ዓመት በፊት ነው፡፡
2.
አባታችን ኖኅ አብርሃም
ይስሐቅ ያዕቆብ ያቀረቡት የሚቃጠል መሥዋዕት ከዚህ ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ በተቀበሉት ትውፊት መሠረትም ስለመሥዋዕትና መሰዊያን ስለመሥራት
ያውቁ ነበር (ዘፍ. 12፥7)
3.
ኖኅ በተመሳሳይ መሥዋዕት ለእግዚአብሔር አቀረበ(ዘፍ 8፥20-21)
4.
አብርሃም ካህኑን መልከ ጸዴቅን ስያገኘው ያሳየው ክብር ለካህናት ስለሚገባው ክብር
ከመጻፉ አስቀድመው የተገለጹ ናቸው (ዘፍ.
15፥20)
5.
በክርስትናም የሐዲስ ኪዳን ፀሐፊዎች በትውፊት ያገኙትን የብሉይ ኪዳን ታሪኮች ተርከዋል፡፡ለምሳሌ
ቅዱስ ጳውሎስ ሙሴን የተገዳደሩትን ስም በመጥቀስ ጽፎል ይህ ግን በሙሴ መጽሐፍ አልተጠቀሰም፡፡‹‹ኢያኔስና አያንበሬስም ሙሴን እንደተቃወሙት››(2
ኛ ጢሞ 3፥8)
የትውፊት
ጥቅም
v ትውፊት ጥሬውን ብስል ደረቁን እርጥብ አድርጎ የእግዚአብሔርን ቃል ያስተምረናል፡፡ ትውፊት ሐዲስ ኪዳንን ከብሉይ ኪዳን፤ ብሉይ ኪዳንን ከሐዲስ ኪዳን የምንመሳከርበት ነው፡፡ ያለ ትውፊት መጽሐፍ ቅዱስን ምሉዕ ማድረግ አይቻልም፡፡
v ሌላው የትውፊት ጥቅም የመጽሐፍትን ቃል ሳይከለስ ሳይለወጥ ለሚቀጥለው ትውልድ ያስተላልፋል፡፡
v የመጽሐፍትን ትርጉም ለማወቅ ያስረዳናል፡፡ ለምሳሌ (ዮሐ 20፥30) ላይ “ኢየሱስ በዚህ መጽሐፍ ያልተጻፈ ብዙ ምልክት በደቀ መዛሙርቱ ፊት አደረገ” ስለዚህ በደቀ መዛሙርቱ ፊት ያደረገውን ለማወቅ ግድ ትውፊት ያስፈልገናል፡፡ (ዮሐ 21፥25) ላይም “ኢየሱስም ያደረገው ሌላ ብዙ ነገር ደግሞ አለ፡፡ ሁሉም እያናዳንዱ ቢጻፍ ለተጻፉት መጻሕፍት ዓለም ራሱ ባልበቃቸው ይመስለኛል፡፡” ሲል ወንጌላዊው ዮሐንስ ተናግሮዋል፡፡ ስለዚህ ጌታ ያደረገውን ለማወቅ የግድ ትውፊት ያስፈልገናል፡፡
v በትውፊት የቤተ ክርስቲያን ንዋያትና የቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ለእኛ ደርሰውናል፡፡
v በትውፊት የቀና ሃይማኖት ደርሷል፡፡ ሆኖም የመጽሐፍ ቅዱስን ትርጓሜ እያንዳንዱ ሰው እንደሚረዳው ይተርጉም ተብሎ ቢተው ኖሮ አሁን ቤተ ክርስቲያን ላይ ካለው ይልቅ ብዙ መከፋፈል በተፈጠረ ነበር፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ራሱ ለእኛ የደረሰን በትውፊት ነው፡፡
v ትውፊት በዙ ሥርዓቶችንና ትምህርቶችን ጠብቆ አቆይቶልናል፡፡ ለምሳሌ ሰንበትን ማክበር፥ ፍትሐት፥
ክህነት
ደረጃና ተግባር ወዘተ . . .
ማጠቃለያ
- ትውፊት ስንል በሰዎች የተሰሩ ባዶ ዋጋ ቢስ ልምዶችና ወጎች ማለታችን አይደለም፡፡ ወይም ደግሞ ከመጽሐፍ ጋር የማይዛመዱትንና ረብ የለሽ መሆናቸውን የተናገረላቸውን ሰዋዊ ልማዶች ማለታችን አይደለም፡፡ ነገር ግን የቀናውንና
- በትውፊት የደረሰን የጌታችን ትምህርት
- የሐዋርያት ትምህርት የሆነና ከትውልድ ወደ ትውልድ አልፎ የደረሰንና
- ስለ ቤተክርስቲያን ሥርዓት እና ቀኖና በቅዱሳን አባቶች ጉባዔ የተወሰነውንና
ከአባቶቻችን መምህራንና
የቤተክርስቲያን የእምነት
ሰማዕታት ከተቀበልነው ትምህርት ጋር የተስማማውን እንዲሁም እውነተገኛ
ሐዋርያዊ
ትውፊት ማለታችን ነው፡፡
የፕሮቴስታንቱ ዓለም ስለትውፊት ጥቅም(አስፈላጊነት)ን አያምኑም፡፡
ይህም ትምህርት ‹‹መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ››(sola scriptura) ይሉታል፡፡ ከሚቀበሉት ከሥልሳ ሥድስት መጻሕፍት ውጭ ሌሎችን
አይቀበሉም፡፡
ይቆየን
እናመሰግናለን🙏
ReplyDelete