በዲያቆን ፍሬው ለማ
ነሐሴ 5 2007ዓ.ም
ነሐሴ 5 2007ዓ.ም

ይህ የጾመ ማርያም ወቅት በየዕለቱ ይህን የማርያምን የምስጋና ቃል የምንሰማበት እንዲሁም የምንተረጉምበት ወቅት
ነው፡፡ ሐዋርያት አባቶቻችንም በጎ ልመናቸው ይፈፀምላቸው ዘንድ የጾሙት ጾም ነውና እኛም በፍቅረ ማርያም ተቃኝተን
እንጾመዋለን እነርሱ በመጾማቸው ምሥጢር ተገለጠላቸው እመቤታችን በእውነት የባሕርያችን መመኪያ መሆኗን አዩ፡፡ ሰው
ሁሉ ተስፋ ከሚያደርገው መንግስተ እግዚአብሔር በመሪነት ተካፋይ ሆናለችና በጌታ ቀኝ በክብር ተቀምጣ አይተዋታልና
ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያንም በነቢያት እና በሐዋርያት መሠረት ላይ የታነፀች ናትና የእነርሱን አሠረ ፍኖት በመከተል ቁጥራቸው ከ 7ቱ የአዋጅ አፅዋማት የሆኑ ሁለት ጾሞችን ሐዋርያትን አብነት በማድረግ ትፈፅማለች፡፡ እነዚህም ጾመ ሐዋርያት እና አሁን ያለንበት ጾመ ፍልሰታ ናቸው፡፡ ከሁለቱ ደግሞ ጾመ ፍልሰታ የምዕመናን አንድነት የሚገለጥበት ህጻናት ሳይቀር በታላቅ ፍቅር የሚሰበሰቡበት ነው፡፡
ይህ ወቅት አብያተ ክርስቲያናት 24 ሰአት ሊባል በሚችል መልኩ የሚያገለግሉበት ወቅት ነው ሌሊት በሰዓታት ጠዋት በስብሐተ ነግህ ቀጥሎ በውዳሴ ማርያም በቅዳሴ ማርያም ትርጓሜ ሰርክ በቅዳሴ ከቅዳሴ በኋላም በሰርክ ጉባኤያት የሚደምቁበት ጊዜ ነው ፡፡ ምዕመናንም በቤተክርስቲያን ታዛ ስር ተጠልለው ከእነዚህ ሁሉ የአምልኮ ሥርአቶች ይካፈላሉ፡፡ ሐዋርያት ለጾሙ አብነት ናቸውና አንድም የአዲሲቷ እሥራኤል (ቤተክርስቲያን) መሪዎቿ ጠባቂዎቿ ናቸው እና በእነዚህ የአምልኮ ሥርአቶች ከእመቤታችን ቀጥሎ እጅግ ጎልተው ይታወሳሉ
በቅድምያ ሐዋርያት በቤተክርስቲያን በጠቅላላው ያላቸውን ቦታ እንይና ቀጥለን በሱባኤው ውስጥ ያላቸውን ቦታ እንመለከታለን
ጌታችን በዘመነ ሥጋዌው ኀ ዳጊተ በቀል የሆነችውን አዲሲቷን ህግ አዲስ ኪደንን በሰራት ጊዜ የተስፋውን መፈጸም፤ የእርሱን መውረድ ይጠባበቁ ከነበሩት ህዝቦች መካከል የተናቁትን እና የተገፉትን የእርሱ ባልደረቦች ደቀመዛሙርት እንዲሆኑ መረጠ፡፡ አመራረጡም በወንጌላት ውስጥ ተመዝግቦ እናገኛለን፡፡ ወንጌላዊው ማቴዎስ ይህን ሲነግረን ማቴ9፡36 ላይ ‹‹ብዙ ህዝብም ባየ ጊዜ እረኛ እንደሌላቸው በጎች ተጨንቀው ተጥለውም ነበረና አዘነላው›› ብሎ ነው ከዚያም አሥራ ሁለቱን ሐዋርያት ጠራቸው አጋንንትን ያወጡ ዘንድ ድውያንን ይፈውሱ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፡፡ እነርሱም በህዝቡ ዘንድ ባለመማራቸው እና በሥራዎቻቸው የተናቁ እና የተገፉ በእኛ በልጆቻቸው ዘንድ ግን የሚያበሩ ፋናዎች የሆኑን ናቸው፡፡ የሁለተኛው አዳም አካል ለሆነችው ቤተክርስቲያን መሠረቶች ናቸው (ኤፌ2፡20)
የአዲስ ኪዳን መጽሐፍትም በአራት ቦታዎች የበጉን ሐዋርያት ስም ዝርዝር ጽፈውልናል ይህም በ (ማቴ10፡12፤ ማር3፡13፤ሉቃ6፡14 እና ሐዋ1፡13) የተገለጠ ነው፡፡ እነዚህ ወንድሞች የአዲሲቷ እሥራኤል መሪዎች ሆነዋል፡፡ ጌታም ከዋለበት እየዋሉ ካደረበት እያደሩ 3 አመት የተማሩትን እንዲያስተምሩ እና መረቦቻቸውን በምዕመናን እንዲሞሉ አዟቸዋል(ማቴ28፡19)፡፡ ሐዋርያትም ህይወታቸውን በመስጠት ቃሉን ፈጽመዋል አልጫውን ዓለም አጣፍጠዋል፡፡ በክርስቶስ ቤተክርስቲያንም ከ እመቤታችን ቀጥሎ የሚከበሩ ናቸው፡፡
ቤተክርስቲያን በምን በምን ክብራቸውን ትገልጣለች ያሉ እንደሆነ አንደኛ በቅዳሴዋ ነው፡፡ ከሥነ ፍጥረት እንደምንረዳው የሰው ልጆች ሊያመልኩ የተፈጠሩ ናቸው ይህም ማለት ለማገልገል እና ዓለምን ሁሉ በአንድነት ወደ ጌታ ለማቅረብ ብሎም ራሳቸውን መሥዋዕት ለማድረግ ተፈጥረዋል በዚህም ጽድቅን አግኝተው ከቅድስት ሥላሴ ጋር ተጣብቀው ይኖራሉ ይህ አላማ በአዳም በደል ምክንያት ተቋርጦ ሳለ ወልደ እግዚአብሔር ሰው ሆኖ ራሱንም ዓለምንም ፈጽሞ አንዴ ወደ አባቱ አቀረበ ወደ ቅዳሴአችንም መለሰን ከእንግዲህም እንግዶች አይደላችሁም ተባለልን የቅዱሳንም ቤተሰብ ሆንን (ኤፌ 2፡19) በኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ቅዳሴ ሰማያዊያን እና ምድራዊያን የሚገናኙበት ታላቁ ጸሎት ነው ቤተክርስቲያን በቅዳሴዋ ሐዋርየት ያስተላለፉትን ትዕዛዝ ታሰማለች ለዚህም ሁለት ምሳሌዎችን መጥቀስ በቂ ነው አንደኛው በመግቢያ ጸሎታችን ሐዋርያት በአብጥሊስ መጽሐፋቸው እንዳስተማሩን በቅዳሴ ሰዓት ሥጋውን ደሙን ያልተቀበለ በአምላኩ ፊት መቆምን አቃሏልና ይለይ እንላለን ሁለተኛው ዲያቆኑ በይፋ የሚያውጀው ‹‹ይህ የአባቶቻችን የሐዋርያት ትዕዛዝ ነው ሰው በልቦናው ቂም እና በቀልን ቅናት እና ጸብን ማንም በማንም ላይ አይያዝ›› የሚለው ነው ከዚህም በተጨማሪ የሥርዓተ ቅዳሴው አብዛኛው ክፍል ከሐዋርያት የሲኖዶስ ቀኖናት የተገኘ ነው የመሥዋዕቱ ዝግጅትም ቢሆን በዚሁ መጽሐፍ የሚመራ ነው፡፡ ከአሥራ አራቱ ቅዳሴያት አንዱ የሆነው እና በግጻዌ መጽሐፋችን በብዛት እንዲያከብር ሥርአት የተሠራለት ቅዳሴ ሐዋርያትም ከዚሁ መጽሐፍ እንደተገኘ መምህራን ይናገራሉ፡፡ በቅዳሴ መሀል ሐዋርያት የጻፏቸውን መጽሐፍት እናነባለን ይልቁንም ዜናቸውን የሚናገረውን ግብረ ሐዋርያት ዓመቱን ሙሉ ሳናቋርጥ እናነባለን፡፡ ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያናችን ከእነዚህ ምንባባት በፊት እና በኋላ ክብራቸውን የሚገልጡ ምስጋናዎች አዘጋጅታ ታመሰግናቸዋለች፤ ትማፀንባቸዋለች፡፡
ወደ እነዚህ የአምልኮ ህብረት ሰማያዊ ማዕድ ፍጥረትን ሁሉ ይጠሩ ዘንድ የተሸሙ በጌታቸው ፈጥነው የተተኩት ሐዋርያት ናቸው እነርሱም የጌታን ፍለጋ በመከተል ራሳቸውንም ዓለምንም በምስጋና በአምላካቸው ፊት አቅርበዋል ለዚህም ነው በአማልኮ ሥርአቶቻችን ሁሉ የምናነሣቸው
ቤተመቅደሶቻችንም እነርሱን በሚያዘክሩ ቅዱሳት ሥዕላት የተመሉ ናቸው፡፡ ዜና ትሩፋታቸውን በሚያዘክር ሁኔታ እና መጽሐፍትን ይዘው የምስክርነት ህይወታቸውን እንዴት እንደፈጸሙ በሚገልጽ መልኩ እንሥላቸዋለን፡፡ ይህም ብቻ አይደለም ወልደ ማርያም ኢየሱስ ክርስቶስ የሥጋወደሙን ምሥጢር በምሴተ ሐሙስ በቤተ አልዓዛር ሲያሳይ ሐዋርያት በዙሪያው እንደ ነበሩ አድርገን በሥዕላት እንገልጣቸዋለን፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ጌታችን ሥራውን ፈጽሞ በአረገ ጊዜ ከ እርሱ ጋር አይናቸውን አቅንተው ትኩር ብለው የወልደ እግዚአብሔርን ከፍ ከፍ ማለት ሲመለከቱ የሚገልጠውን (ሐዋ1፡10) ቤተክርስቲያን በነገረ ዕርገት ሥዕሏ ከትባ ትጸልይበታለች ታጥነዋለች፤ታስተምርበታለች፡፡ ከጠቀስናቸው ሌላ እጅግ በበለጠ መልኩ ሐዋርያት እመቤታችን ባለችበት ጌታ ባረገ በ አሠረኛው ቀን በጽርሐ ጽዮን ሁሉም ሐዋርያት ማትያስን ጨምሮ የመንፈስቅዱስን ፀጋ ሲቀበሉ እና ሲሾሙ ፀጋ መንፈስቅዱስም በእነርሱ ሲያድር የሚያሳየው ሥዕል እጅግ የተወደደ ነው፡፡
በከቅዳሴያችን ውጭ በማኅሌት እና ሰዓታት ጸሎቶቻችንም ተገቢውን ስፍራ ይዘው ደምቀው ይታያሉ፡፡ ለአብነትም በጾመ ማርያም በሁሉም አብያተ ክርስቲያናት በሚደርሰው የሰዓታት ጸሎታችን ውስጥ እንዲህ የሚል ምስጋና አለ ‹‹ ሰአሉ ለነ ሐዋርያት አስራብ ዘወርቅ ወሐይዝተ ጽድቅ ወዘ ሐረገ ወይን አዕጹቅ›› የጽድቅ ፈሳሾች የወርቅ ጎርፎች የምትሆኑ ሐዋርያት ሆይ ለምኑልንና የወይን ሐረግ ጫፎች ናችሁና ፈጽማችሁ ለምኑልን ›› እንደ ቅዳሴው ሁሉ በሠዓታት የሐዋርያት መልዕክታት ግብረ ሐዋርያትን ጨምሮ በሚነበብበት ጊዜም መግቢያው እና መጨረሻው በእነርሱ ውዳሴ የተሞላ ነው፡፡ በእነርሱ ስም በታነፁ አብያተ ክርስቲያናት የሚዘመረው ስብሐተ ፍቁር ዘሐዋርያትም 12ቱ ሐዋርያት ከአርድዕቶች ጋር ጭምር የሚመሰገኑበት ነው ፡፡ መልክዕ እና ገድላት ተጽፎላቸዋል፡፡ አብያተ ክርስቲያናትም በስሞቻቸው ታንፀዋል ምዕመናንም ልጆቻቸውን በስሞቻቸው በመሰየም ፍቅራቸውን ይገልጣሉ፡፡ ለኦርቶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያት መሠረት ናቸው ማለታችን ከላይ ከተጠቀኩት ነገሮች የላቀ ነው፡፡ ለአዲስ ኪዳን ምዕመናን ሁሉ ሕይወታቸውን ፋና ወጊ ነው፡፡ ክርስቶስን በመሸከም ዓለምን ዞረዋል (2ቆሮ4፡10) ለሰማዕትነት(ለምስክርነት) አብነት ናቸው፡፡ ለዚህም ብቻ አይደለም ራስን ለክርስቶስን ለመለየት አብነት ናቸው፡፡ ለተባሕትዎ ህይወትም አብነት የሚሆኑ ሐዋርያትም አሉ:: 12ቱ ከዋክብት ለእኛ የሚነበቡ መጽሐፍት ናቸው፡፡ የሰው ክብር የት ድረስ እንደሆነ ከምንረዳባቸው ቅዱሳን ዋነኞቹ ሐዋርያት ናቸው፡፡ ይህን ግባራቸውን እንከተል ዘንድ ነው በእንተ ቅድሳት በተባለው ጸሎታችን ‹‹ እነርሱ ደስ እንዳሰኙት ደስ እናሰኘው ዘንድ እግዚአብሐር ማገልጉን ይሰጠን ዘንድ ዕድል ፈንታቸውንም ያድለን ዘንድ አገልጋዮቹ ስለሚሆኑ ሐዋርያት እንማልዳለን›› የምንለው
ቅዱስ ኤፍሬምም በውዳሴ ማርያም ድርሰቱ ‹‹ ለሐዋርያትም እስከ ዓለም ዳርቻ በስሙ ያስተማሩለትን ወልዳላቸዋለችና ብሏል›› አባቶቻችንም ይህን ሲተረጉሙ ሐዋርያት አስበ ስብከታችንን ይሰጠናል ብለው ጽንፍ እስከ ጽንፍ ዞረው ያስተማሩትን ወልዳላቸዋለችና ኄርት ይእቲ ንስአል ኀቤሃ ብለዋል አባ ህርያቆስም እመቤታችንን የሐዋርያት ሞገሳቸው ብሏታል

ከአራቱ የቤተክርስቲያን ፀባያት አንዱ ሐዋርያዊነት የሚለው ነው ‹‹ከሁሉም በላይ በምትሆን ሐዋርያት በሰበሰቧት
በአንዲት ቅድስት ቤተክርስቲያን እናምናለን›› እንዲል ጸሎተ ሀይማኖት፡፡ ይህ ቃል ብዙ ነገሮችን ያመለክታል
እነዚህንም ቃላት የምንረዳቸው ቤተክርስቲያን በሐዋርያነት ቅብብሎሽ(apostolic successions) እና
በሐዋርያት ትምህርት ጸንታ መቆየቷን ነው ፡፡ የቤተክርስትያናችን ዶግማ ቀኖና ትውፊት በጌታ የተሰበከ በሐዋርያት
የተብራራ በመንፈስ ቅዱስ የተገለጠ ነው፡፡ ትምህርቶቻቸው ከግብረ ሐዋርያት የተገኙ እና በገድለ ሐዋርያት እና
በመጀመሪያዎቹ ክፍለ ዘመናት ከተጻፉ ድርሳናት ማግኘት የምንችለው ነው፡፡ አሁን አሁን ብቅ ብቅ ያሉ ሰዎች ግን
ከዚህ ሐዋርያዊ ቅብብሎሽ ውጭ ሆነው ትምህርቶቻቸውን ስለሚያላምጡ ወደ መረዳት ለመድረስ ይቸገራሉ፡፡ ሐዋርያት
በሰማይ ባለች መቅደስ አምሳል ቤተክርስቲያንን ሰርተዋታልና ከክህነት ቅብብሎሽ እና ትውፊት ውጭ ለሆኑት
ትምህርቶቻቸው የማይዋጡ፤ በዘመን የተገደቡ የሚመስሉትም ከህብረቱ ቀድመው ራሳቸውን ስለለዩ ነው፡፡ እነዚህም መጽሐፍ
እንደሚናገር የሞቱ ናቸው ‹‹አአምር ግብርከ ከመ ስምከ ህያው ወምዉት አንተ›› ‹‹ስምህ ሕያው እንደሆነ አንተ
ግን የሞትክ እንደሆን በሥራህ አውቃለሁ››
ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስና ቀደም ተብሎ እንደተገለጠው ሐዋርያት በዚህ በሱባኤ ማርያም ወቅት የሚዘከሩ ናቸው፡፡ ጾሙን በመጾም አንድም የእመቤታችንን ሥጋ በመቀበል፤በመገነዝ ፤ በአባት እና እናቷ ርስት በጌቴሴማኒ በክብር በማሳረፍ የክብሩ ተካፋይ ናቸውና ‹‹ሰላም ለግንዘተ ሥጋኪ በእደ ሐዋርያት አርጋብ›› በሐዋርያት እጅ ለተገነዘው ንጹሕ ሥጋሽ ሰላምታ ይገባል እንዳለ የመልክዐ ማርያም ደራሲ በመጽሐፈ ዚቃችንም ውስጥ ‹‹ተጋብዑ በቅፅበት ለግንዘተ እሙ ቅድስት ብፁዓን ሐዋርያት ቦኡ ኀቤሃ በሰላም አምኁ ኪያሃ በስብሐት ገነዙ ሥጋሃ ለማርያም ድንግል ›› የሚል አብነትም ይገኛል ዚቅ ዘጥር 21 ይህም ብቻ አይደለም ለአለም ሁሉ የሚያስደንቀውን ፍልሰቷን(ዕርገቷን) ቀድመው ያዩትም ሐዋርያት ናቸው ስታርግ ሲያዩ ያመሰገኑበት ቃልም ለእኛ ተፅፎልናል ‹‹ እም ጌቴሴማኒ ፈለሰት ኀበ ዘሉዓሌ መካን ውስተ ቤተመቅደስ ረባቢ ዘመሳክዊሁ ብርሃን አንቀጸ አድኅኖ ማርያም ጽላተ ኪዳን ኩሉ ይቤልዋ በአኅብሮ ዘበዕብራይስጢ ልሳን ዕፀ ጳጦስ ይእቲ ቅድስተ ቅዱሳን›› ‹‹ ከጌቴሰማኒ ከፍ ወዳለው መቅደስ ፈለሰች (አረገች) ይኸውም ረብቦ የሚታይ ብርሃን መፍለቂያ ነው ሁሉም በአንድነት በዕብራይስጥ ቋንቋ በእውነት ዕፀ ጳጦስ እና ቅድስተ ቅዱሳን ነች እያሉ አመሰገኗት›› ዚቅ ዘነሐሴ 16 በመጀመሪያው የሱባኤአቸው ወቅት ከሐዋርያ ቶማስ በቀር ሁሉም ሥጋዋን ተቀብለው በክብር አሳረፏት እንጂ ፍልሰቷን አላዩም ነበር ለ ቶማስም ይህን ወንድሞቹ ያላዩትን ምሥጢር እንዲያስረዳ ሰበኗን ተቀበለ ይኸውም አብነት ሊሆን በቅዳሴ ሰዓት ሰራዒው ዲያቆን በሚይዘው መጾር መስቀል ላይ የሚደረግ ነው ይህም ምዕመናንን ለንፅህና እና ለቅድስና ህይወት የሚያተጋ ምልክት ነው በትጋት ለፀኑት እና የእመቤታችንን ህይወት ለመከተል ለሚፈልጉ ሁሉ በምልጃዋ እርሷ ከገባችበት መንግስተ ሰማያት እንድታገባን የተገባላት ቃልኪዳንም ማሳያ ነው፡፡
አባ ጊዮርጊስ በአርጋኖን ጸሎቱ እመቤታችንን እንዲህ እያለ ይማፀናታል ‹‹ ድንግል ሆይ የቃልን ካንቺ ሰው መሆን ሥጋ መልበሱንም ጽንፍ እስከ ጽንፍ ካስተማሩ በልጅሽም ዕርፈ መስቀል የአሕዛብን ምድር ካረሱ የቃሉንም ድልብ በምድር ሁሉ ከዘሩ ሐዋርያት ጋር ወደ እኔ ነይ›› አርጋኖን ዘአርብ አሜን እመቤታችን ከሐዋርያት ጋር ወደ እኛ ትምጣ ወደ እነርሱ ህብረትም ትቀላቅለን አሜን ሰው ሆኖ ካዳነን ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኝልን ማወቁን ማስተዋሉን በልቡናችን ሳይብን አሳድሪብን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ቃለ ሕይወትን ያሰማልን
ReplyDeleteደስ የሚል ኦርቶዶክሳዊ ሳይት
ReplyDelete