Monday, 1 January 2018

የቤተ ክርስቲያን ሐኪም ፤ ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ




በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ከሐዋርያት ቀጥሎ የቅዱስ አትናቴዎስን ያህል ስለ ሃይማኖት የተዋጋ ቅዱስ ፈልጐ ማግኘት አይቻልም፡፡

ቅዱስ አትናቴዎስ ማን ነው?

ቅዱስ አትናቴዎስ በቤተ ክርስቲያን ትውፊት መሠረት በዘመነ ሰማዕታት መጠናቀቂያ 296/300 ዓ.ም አከባቢ እስክንድርያ ግብፅ ውስጥ ነው የተወለደው:: ወላጆቹ አረማውያን በመሆናቸው ክርስትናን አልተማረም ነበር:: አሞጽን ከእረኝነት ሐዋርያትን ከአሳጥማጅነት የጠራግዚብሔርምላክትናቴዎስን ከጨዋታ ሜዳ ጠርቶ የቤተክርስቲያን ወርቃማ ልጅድርጎታል፡፡ ሕጻን እያለ ለጫዋታ ከቤቱ ሲወጣ የክርስቲያን ልጆች ሃይማኖታዊ ጨዋታ ሲጫወቱ ተመለከተ:: ሊቀላቀላቸው ቢፈልግም ክርስቲያን ባለመሆኑ ከለከሉት:: አትናቴዎስም ክርስቲያን ልሁንና አጫውቱኝ ቢላቸው እሺ ስላሉት ሕጻናቱ ዕጣ ተጣጣሉ:: ላንዱ ቄስ: ላንዱም ዲያቆን መሆን ሲደርሳቸው ለአትናቴዎስ ፓትርያሪክ መሆን ስለ ደረሰው ሌሎቹ ሕጻናት ይሰግዱለት ጀመር:: በአጋጣሚ ሕጻናቱ ይሕንን ሁሉ ሲያደርጉ የወቅቱ ፓትርያሪክ ቅዱስ እለ እስክንድሮስ በመገረም ያያቸው ነበርና ለሕጻኑ አትናቴዎስ ትንቢት ተናገረለት:: ከዚያም የአትናቴዎስ አባቱ ሲሞት ሊቀ ዻዻሱ ከእናቱ ወስዶ አጥምቆ የሚገባውን መንፈሳዊ ትምሕርት ሁሉ በልቡናው ላይ ቀረጸበት:: ከዚህ በኋላ ዲቁናን ሹሞ አስተምር አለው:: ምንም ሕጻን ቢሆንም ከሊቅነቱ: ከአመላለሱና ከአንደበቱ ጣፋጭነት የተነሳ የሰማው ሁሉ ይደነቅ ነበር:: ጸጋ እግዚአብሔር በእርሱ ላይ አድራለችና::ቅዱስ አትናቴዎስ ሊቀ ዲቁና በተሾመ ወራት አርዮስ ቤተ ክርስቲያንን በመረበሹ ኒቅያ ላይ 318 ሊቃውንት ሲሰበሰቡ ጸሐፊ አድርገው ሾሙት:: በጊዜውም በዕድሜ የስንት ጊዜ ትልቁ የሚሆነውን አርዮስን ተከራክሮ ምላሽ አሳጣው::
 ቅዱስ አትናቴዎስ ከሊቃውንቱ ጋር ሆኖ ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ ወልደ አምላክ: እግዚአብሔር መሆኑን በአደባባይ መሠከረ:: ጸሎተ ሃይማኖትንም ያረቀቀው እርሱ ነው::
ፓትሪያሪክ አለ እስክንድሮስ ባረፈ ጊዜ በመንበሩ አትናትዮስን ይሾሙት ዘንድ አሳስቧቸዉ ነበር ህዝቡም ጸጋ እግዚአብሔር የበዛለት እንደሆነ ስለ ተረዱ ሊሾሙት ወሰኑ ቅዱሱ ግን እኔ ምናምንቴ ነኝ ለዚህ ክብር የምገባ አይደለሁም ሲል እራሱን በተራራዎች ስር ደበቀ፤ ህዝቡ ግን ፈልገዉ አመጡት፤ ከዚህ በኃላ በ33 ዓመቱ በ328 ዓ/ም የእስክንድርያ (የግብፅ) 20 ፓትርያሪክ ሆኖ ተሾመ:: ከቅዱስ እንጦንስ ምንኩስናን የተቀበለ የመጀመሪዉ ፓትርያሪክ ነዉ፡፡ የምንኩስና ልብሱንም የጳጳሳት ዩኒፎርም እንዲሆን አድርጓል፡፡ ቤተ ክርስቲያንን በመልካም እረኝነት 48 ዓመታት ሲመግብ ብዙ መከራዎችን ተቀብሏል::

ቅዱስ አትናቴዎስ ለኢትዮጵያ

328 .. ቅዱስ ፍሬምናጦስ በእስክንድርያ ቤተክርስቲያን ፓትርያሪክን ለኢትዮጵያ ለማሾም በመጠባበቅ ላይ እያለ 19ኛው የእስክንድርያ ፓትርያርክስክንድሮስርፎ በምትኩ ስክንድርያ መንበር ቅዱስትናቴዎስ ተተካ፡፡በዚህ ጊዜ ፍሬምናጦስ የተላከበትን ጉዳይ ለቅዱስትናቴዎስቀረበ ፓትርያሪክትናቴዎስም በጉዳዩ ተደስቶ ትዮጵያ ክርስቲያኖች ቋንቋቸውንና ባህላቸውን የሚያውቅ ሌላ ባለመገኘቱ ራሱን ቅዱስ ፍሬምናጦስን ‹‹ጳጳስ ክሱም ወዘኩሉትዮጵያ›› ብሎ የመጀመሪያዉን ጳጳሳችንን በቅብትና ንብሮተ እድ ሹሞ ላከው፡፡

መከራዉና ስደቱ

የቅዱስ አትናቴዎስን መከራዉንና የስደት  ሕይወቱን ማወቅና መረዳት በተለይ የአራተኛውን መቶ ዓመት፣ በአጠቃላይ ደግሞ በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ የተመሠረተችውን የቤተ ክርስቲያንን የዚህ ዓለም የመስቀል ጉዞ መረዳት ነው፡፡ ይህ አራተኛው መቶ ዓመት ደግሞ ምንም እንኳን ሁሉም ነገር በእግዚአብሔር እጅ ቢሆንም እንደ ሰው ስንመለከተው ግን የቤተ ክርስቲያንን መሠረታዊ አቅጣጫ ሊያስለውጡ የደረሱ ከባድ ኑፋቄያዊ ፈተናዎች የተነሡበት ዘመን ነበር፡፡

ቤተ ክርስቲያን ከግማሽ ምዕተ ዓመት ለሚበልጥ ዘመን ከአርዮሳውያን ጋር ላደረገችው እልህ አስጨራሽ ትግል መለያ ግርማና ወካይ መገለጫው ቅዱስ አትናቴዎስ ነው፡፡ ዘመን ገጠሙ የነበረው ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናንዙ የቅዱስ አትናቴዎስን ተጋድሎ በተመለከተ ሲናገር‹‹ አትናቴዎስን ሳመሰግን የማመሰግነው የመልካም ተጋድሎ ሕይወትን ነው፤ ስለ እርሱ መናገርና ስለ መልካም ተጋድሎ ሕይወት መናገር አንድ ናቸውና፣ ምክንያቱም እርሱ የመልካም ተጋድሎ ሕይወትን በምልዓት ገንዘብ አድርጓልና ›› ያለው ለዚህ ነበር፡፡
ቅዱስ አትናቴዎስ በዘመኑ 5 ጊዜ ከመንበሩ አፈናቅለው ወደ በርሃ እንዲጋዝ አድርገዉታል፡፡ (በስደት 15/16 ዓመታት በላይ አሳልፏል)፡፡ ቅዱሱ በተሰደደባቸው ቦታዎች መከራን እየተቀበለ ያላመኑትን አሳምኗል:: በጎቹ እንዳይባዝኑበት ደግሞ በጦማር (በደብዳቤ) ይጠብቃቸው ነበር:: ዛሬ በሃይማኖተ አበው የምናገኘው ቃለ ሃይማኖት በዚህ ዘመን የተጻፈ ነው::
·         የቅዱሱ የመጀመሪያ ስደቱ መንስኤ የአርዮሳዊያን መናፍቃን የሐሰት ክሶች ነበሩ አትናቴዎስም በጉባኤ መዓል ሐሰተኝነታቸዉን አጋልጦ ንጽሕናዉን አስመስክሩዋል፡፡ በዘመኑ የነበረዉ ንጉስ ቆስጠንጢኖስ ንጽህናዉን ቢረዳም እነዚህ መናፍቃን እርሱን ለማጥፋት ቆርጠዉ እንደተነሱ ስለተረዳ ከነሱ ሊሰዉረዉ ሲል ወደ ትሬቬሬ እንዲጋዝ አደረገዉ::
·         ሁለተኛ እና ሶስተኛ ስደቱ ደግሞ (ትንሹ ቆስጠንጢኖስ) የአባቱን (ታላቁ ቆስጠንጢኖስን) ዕረፍት ተከትሎ ነገሠ:: ወዲያውም አርዮሳዊ መናፍቅ ሆነ:: ሃይማኖታቸው የቀና አባቶችንም ያሳድድ ገባ:: ከአበው ቅዱሳን መካከል ግን የዚህ መከራ ቀዳሚው ገፈት ቀማሽ ታላቁ ሊቅ ቅዱስ አትናቴዎስ ነበር:: ከ መንበሩም ሁለት ጊዜ አፈናቅሎታል፡፡ በተለይ አንድ ጊዜ ቅዱሱን ወደ በርሃ አግዞ: መናፍቅ ዻዻስ በግብጽ ሹሞ: ብዙ ክርስቲያኖችን በግፍ ሲያስገድል: ቅዱሱን 6 ዓመታት አሰቃየው:: የወገኖቹ (የልጆቹን) ስቃይ የሰማው ቅዱስ አትናቴዎስ ግን በድፍረት ወደ ቤተ መንግስት ገብቶ ተናገረው:: ሁለት አማራጭን አቅርቦ "ወይ ግደለኝና እንደ አባቶቼ ሰማዕት ልሁን: ካልሆነ ግን ወደ መንጐቼ (ምዕመናን) መልሰኝ" አለው:: መናፍቁ ንጉሥም ቢገድለው ብጥብጥ እንደሚነሳ ስለሚያውቅ በስልት ሊያጠፋው ወሰነ:: ቀዛፊ መቅዘፊያ ምግብና ውሃ በሌላት ጀልባ ውስጥ ከቶም ሜዲትራኒያን ባሕር ውስጥ ጣለው:: ድንገት ግን ከሰማይ ጌታችን መላእክቱን አስከትሎ ወረደ:: ሚካኤልና ገብርኤል ባሕሩን እየቀዘፍ: ሌሎች መላእክት እየመገቡት እስክንድርያ (ግብጽ) አድርሰውት ተሠውረዋል:: ሕዝቡም በታላቅ ሐሴት እየዘመሩ አባታቸውን ተቀብለውታል::
·         ቀጥሎም ንጉሡ አረማዊዉ ዮልዮስ ሲነግስ ቅዱሱ ጣኦት አምላኪዎችን እያሳመነ ያጠምቅ ነበርና በዚህ ስራዉ ተናዶ ሊያሲዘዉ ትእዛዝ አዘዘ በዚህም ንጉሱ እስኪሞት ድረስ በስደት ቆየ፡፡
·         በመጨረሻም ንጉስ ጁቪያን ሲነግስ አሪዮስያዊ ነበርና 30 ጳጳሳትን አስገደለ አትናትዮስም በመቃብር ቤት ተሸሸገ ነገር ግን ንጉሱ የሕዝቡንና የጳጳሱን ጽናት ሲመለከት አትናትዮስን ወደ መንበሩ መለሰዉ፡፡ አትናትዮስ በዚህ ጊዜ 72 ዓመት ሞልቶት ነበር በብዙ እንግልትም ደክሞ ነበር ቢሆንም ግን ለሕግ የቆመ ጠንካራ የቤ/ክ ታላቅ ጠበቃ ነበር፡፡
·         ቅዱሱ ብቻዉን የሮማዉያን ቄሳሮችን ዛቻና ኃይል ያለ ምንም ፍርሃት የተጋፈጠ ልዩ ጀግና ነዉ፡፡ በዚያ ዘመን የነበረዉ በቅዱስ አትናትዮስና በ አሪዮስያዊያን መካከል የተካሄደዉ ተጋድሎ ‹‹አትናቴዎስ ከዓለሙ ጋር፤ ዓለሙም በአትናቴዎስ ላይ›› "Athanasius against the world." ብለዉ ገልጸዉታል፡፡



ትናቴዎስ ለቤተክርስቲያን

1. በስሙ የሚጠራ ቅዳሴን ደርሷል ‹‹ቅዳሴ አትናቴዎስ››
2. ጸሎተ ሃይማኖትንርቆ ጽፏል
3. የመጽሐፍ ቅዱስን ቁጥር ለይቶ ገልጿል
4. ለኑፋቄ ትምህርት መልስ ሰጥቷል
5. ብዙ መልክታትን ጽፎ ብያተ ቤተክርስቲያናትስተላልፏል
6. ስለ ነገረ ሥጋዌ ጽፏል

ረፍቱ ለቅዱስ አትናቴዎስ

አትናቴዎስ በዘመኑ ሁሉ በቤተ ክርስቲያን የተቃጣዉን ሃይማኖታዊና ፖለቲካዊ ዘመቻ ሲዋጋ የኖረ ታላቅ የቤተ ክርስቲያን አርበኛ ነዉ፡፡ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናንዙ አትናቴዎስን ‹‹ የቤተክርስቲያን ምሶሶ›› ይለዉ ነበር፡፡ አትናትዮስ ሃይማኖተኛ፤ ጀግና፤ ዘዴኛ፤ ታላቅ የትህትና አባት እና የሚያስደሰት ጥበብን አሙዋልቶ የያዘ ነበር፡፡ ቅድሱ በሕይወት ዘመኑ ብዙ ሃይማኖታዊ ሥራዎችን ሠርቶ አልፏል፡፡ ሐዋርያዊው ቅዱስ ስለ ኦርቶዶክስ ተዋግቶ: ብዙ ስቃይንም ተቀብሎ በ 75 ዓመቱ ግንቦት 7 ቀን 373 / አካባቢ አርፏል:: ቤተ ክስርቲያን "ሊቀ ሊቃውንትርዕሰ ሊቃውንትየቤተ ክርስቲያን (የምዕመናን) ሐኪም (Doctor of the Church)፤ ሐዋርያዊ፤ የሕይወት ምንጭ" ብላ ትጠራዋለች::

+"+ ስለ ጽድቅ የሚሰደዱ ብጹዐን ናቸው:: መንግስተ ሰማያት የእነርሱ ናትና:: ሲነቅፉአችሁና ሲያሳድዱአችሁ በእኔም ምክንያት ክፉውን ሁሉ በውሸት ሲናገሩባችሁ ብጹዓን ናችሁ:: ዋጋችሁ በሰማያት ታላቅ ነውና ደስ ይበላችሁ:: ሐሴትም አድርጉ:: ከእናንተ በፊት የነበሩ ነቢያትን እንዲሁ አሳደዋቸዋልና:: +"+ (ማቴ. 5:10)
የአባታችን የቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋሪያዊ በረከቱ ትደርብን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
 ወወላዲቱ ድንግል
 ወለመስቀሉ ክቡር
 ምንጭ፡-
  •         ቅዱስ አትናቴዎስ ሕይወቱ እና ትምሕርቱ
  •         የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ቁጥር 1
  •         Coptic Orthodox Synaxarium (15-May, 7-Bashans)

1 comment: