በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
እንደምን አላችሁ በዛሬው ቅዱሳን አበው ዓምዳችን ስለቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ታሪክ ይዘን ቀርበናል።
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በ347ዓ/ም የሶርያ ዋና ከተማ በነበረችው ከአሕዛብ ወደ ክርስትና የሚገቡ ክርስቲያኖች መነኃርያ ማዕከል በነበረችውና ክርስቲያኖች መጀመሪያ ‹‹ክርስቲያን›› ተብለው በተጠሩባት በአንጾኪያ ከተማ ተወለደ፡፡አንጾኪያ የምስራቁ ሮም ግዛት ሁለተኛ ከተማ (ቁስጥንጥንያ ቀጥላ) ነበረች፡፡አራተኛው መቶ ዓመት የተለያዩ መናፍቃን (መነናውያን፤ግኖስቲኮች፤አርዮሳውያን አቡሊናርዮሳውን ወዘተ) እንዲሁም አይሁዶችና መምለክያነ ጣዖታት የሆኑት ሁሉ በአንጾያ ከተማ ሁሉም የየራሳቸውን እምነት ለማስፋፋት ይሯሯጡ የነበረበት ዘመን ነው፡፡ ኦርቶዶክሳውያኑ ደግሞ በጳጳስ መላጥዮስና በጳጳስ ጳውሊኖስ መካከል በነበረው ልዩነትና ክፍፍል ምክንያት ለሁለት ተከፍለው ነበር፡፡ስለዚህ የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የወጣትነት ዘመን ቤተ ክርስቲያን በአስቸጋሪ ሁኔታ ላይ በነበረችበት ጊዜ ላይ ነበር፡፡
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ አባቱ አስፋኒዶስ የታወቀ የጦር መኮንን የነበረ ቢሆንም ነገር ግን ቅ/ዮሐንስ አፈወርቅ ገና ሕጻን እያለ ነበር የሞተው ፡፡እናቱ አትናስያ ትባላለች ፤በሃይማኖትና በምግባር እጅግ በጣም የተደነቀችና የተመሰገነች ክርስቲያናዊት ሴት ነበረች፡፡ገና በሃያ ዓመቷ ባለቤቷ በሞት ቢለያትም ማንኛውንም ሁለተኛ ጋብቻ ጥያቄ ሁሉ ባለመቀበል አባታቸው ጥሏቸው የሞቱትን ሁለቱን ልጆቿን ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅንና ታላቅ እኅቱን በማስተማር ላይ አተኮረች፡፡
አንቱዛ ልጇ ዮሐንስ አፈወርቅ ፍልስፍናንና ሕግን እንዲሁም የንግግርን ጥበብ በዘመኑ ከነበሩት ታላላቅ መምህራን እንዲማር አደረገች፡፡እንዲሁም በልጇ አዕምሮ ውስጥ ከልጅነቱ ጀምሮ የእምነትን ዘር ጥሩ አድርጋ ዘራችበት፡፡ይህ የእምነት ዘርም ለራሱና ለቤተ ክርስቲያን እጅግ ጠቃሚ የሆነ ብዙ ፍሬ አፍርቷል፡፡በእናቱ ተግሳጽና በመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ በዘመኑ ተንሰራፍቶ ከነበረው አሕዛባዊ ነገረ ዘርቅና ከንቱ አስተሳሰብ ተጠበቀ፡፡ሆኖም ግን እስኪያድግ ድረስ አልተጠመቀም ነበር፡፡ቤተ ክርስቲያን ልጆቿ ከአህዛብነት ወደ ክርስትና በሽግግር ላይ በነበረበት በዚያን ዘመን የንዑሰ ክርስቲያን ተጠማቂዎች ብዛት ብዙ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት (እነ ቅዱስ ቄርሎስ ጳጳስ ዘኢየሩሳሌም ፤ራሱ ቅ/ዮሐንስ አፈወርቅ እና ሌሎቹም) ለንዑሰ ክርስቲያኖች ከመጠመቃቸውና ወደ ቅዱስ ቁርባን ከመቅረባቸው በፊት የሚማሯቸው ወጥና መሠረታዊ ትምህርቶችን አዘጋጅተዋል፡፡አንዳንድ ክርስቲያን ቤተ ሰብች ሳይቀሩ የልጆቻቸውን ጥምቀት ካላቸው ከፍተኛ ከበሬታ የተነሳና ቶሎ መጠመቅ የጥምቀትን ጸጋ መልሶ የማጣት ሥጋት አለው ከሚል በዘመኑ ከነበረ የፍርሃት አስተሳሰብ የተነሳ ነበር፡፡ይህም ዛሬ ብዙች ንስሃ መግባትንና መቁረብን ሊሞቱ እስኪጣጣሩ ድረስ እንደሚያዘገዩት ዓይነት ያ አስተሳሰብ ነው፡፡ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በኋላ ላይ ይህ ልማድ ትክክል አለመሆኑን በመግለጥ አጥብቆ ይኮንናል፡፡

ቅ/ዮሐንስ አፈወርቅ በዘመኑ የነበረውን የንግግር ጥበብ ትምህርት ከሊባንዮስ ከተባለው መምህር ተምሯል፡፡ፍልስፍናንም በዘመኑ አሉ ከተባሉ መምህራን ተምሯል፡፡በአጠቃላይ ዕውቀቱና ማስተዋሉ አብረውት ከሚማሩት ሁሉ በላይ የነበረ ትጉህ ተማሪ ነበር፡፡እንዲያውም መምህሩ ሊባንዮስ ሊሞት ሲል ‹‹ማን ቢተካህ ትወዳለህ ;›› ብለው ቢጠይቂት ‹‹ክርስቲያኖች ከእኛ ሰርቀው ባይወስዱት ኖሮ የሚተካኝ ዮሐንስ ነበር›› ማለቱ ይነገራል፡፡ቅ/ዮህንስም ትምህርቱን እንደጨረሰ ለትንሽ ጊዜ ጠበቃ ሆነ፡፡ይህም ሥራ ለመንግሥት ሹመትና ሥልጣን ዋና በር ከፋች ነበር፡፡ቤቶች ውስጥ የንግግር ክህሎትንና ልዩ ተሰጥዖን ማሳየት ለታላላቅ ሹመቶች ከሚኒስትርነት እስከ ጠቅላይ ሚኒስትርነት ድረስ ሊደርስ የሚችል ዋና ጥርጊያ ጎዳና ነበር፡፡በፍርድ ቤት የሚያደርጋቸው ንግግሮቹ በሰማያኑና በመምህሩ በሊባንዮስ ሳይቀር ከፍተኛ አድናቆትን አስገኝቶ ነበር፡፡ሆኖም ግን እርሱ በነዚህ ነገሮች ሆሉ ደስተኛ አልነበረም የልቡ ምኞትና ሐሳብ ቤተ ክርስቲያን ነበር፡፡ለክርስትናው ትልቅ ፍቅር ነበረው፡፡ ከዚያም ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብቶ መማር ጀመረ፤ቅዱሳት መጻሕፍትን ተማረ ፤በተለይም ከጳጳሱ መላጥዮስ ጋር ተዋወቀ በጊዜውም ካደጉ በኋላ ከሚጠመቁበት የ3ት ዓመት ትምህርት ተምሮ በ23 ዓመቱ በ370ዓ/ም በጳጳሱ መላጥዮስ እጅ ተጠመቀ፡፡
ቅ/ዮሐንስም ከጊዜ ወደ ጊዜ ሃይማኖቱና ምግባሩ ተወዳጅነትን አገኘ በተለይም ለጳጳሱ መላጥዮስ ይህንንም አይቶ የአናገጉንስጢስነት(የአንባቢነት ማዕረግ) ሾመው፡፡እርሱ ግን ፍላጎቱ የነበረው በገዳም ገብቶ በምንኩስና ሕይወት መኖር ነበር፡፡ትንሽ ትንሽ እያለም የጾምና የጸሎት ሕይወትን አጠንክሮ ያዘ፡፡ለስጋው ምቾትና ድሎትን ነፈገውም የገዳማዊ ሕይወትን መኖር ጀመረ፡፡በቤተ ክርስቲያንም የሚያገለግሉ ካህናትና ሕዝብ እርሱንና ጓደኛው የነበረውን ባስልዮስን ጵጵስና ሊሾሟቸው ፈለጉ፡፡እርሱ ግን እኔ ለዚህ ከባድ የቤ/ክ ኃላፊነት የሚያበቃውና የሚጠቅመው ወንድሜ ባስልዮስ ነው፡፡በማለት ባስልዮስ እንዲሾ ለማድረግ እርሱ ተደበቀ፡፡ባስልዮስ ይህንን ሹመት የተቀበለው ጓደኛው ቅ/ዮሐንስም አብሮ የሚሾም መስሎት ነበር፤ባስልዮስም ጳጳስ ተደርጎ ተሾመ ፡፡
ዮሐንስ ‹‹አፈወርቅ›› ስለመባሉ
ዮሐንስ ‹‹አፈወርቅ›› ብላ ስም ያወጣችለት ቤተ መቅደስ የነበረች ስዕለማርያም ናት ፡፡በቁስጥንጥንያ እያለ በዚያ የሁለት ባህርይ ምንፍቅና ትምህርትን በልቡ የቋጠረ ንስጥሮስ ነበር፡፡ንስጥሮስ ምንፍቅናውን ሊቀ ጳጳስ ሆኖ እስኪሾምበት ጊዜ ድረስ አልገለጣትም፡፡ከጊዜያትም በአንዱ በዓል ዕለት ምዕመናኑ ቅርባን ሲቀበሉ አንዲት በወር ግዳጅ(የወር አበባ) ላይ ያለች ሴት ሳትነጻ ልትቀበል ቀረበች፡፡ሕዝቡም የመንፈስ ቅዱስ ጥላ ከእርሷ ሲርቅ አዩ፡፡የጸሐይ ጮራም በራሷ ላይ አላረፈም፡፡ሕዝቡም ፓትርያርክ ወደሆነው ንስጥሮስ ፊት አቆሟት ፡፡አንቺ ሴት ንገሪኝ የመንፈስ ቅዱስ ጥላ ካንቺ እስኪጠፋ ድረስ ኃጢአትሽ ምንድር ነው፡፡ንስጥሮስም ተቆጥቶ የሥጋዋ ዕርቃን እንደተገለጠ ቁልቁል ይሰቅሉት ዘንድ አዘዘ፡፡ እግዚአብሔር በዚህ ስጋ ከማርያም ከተወለደ መንፈስ ቅዱስ ይህችን ሴትእንደምን ናቃት፡፡እግዚአብሔር ከሴት ከተወለደ በማርያም ምክንያት ሴቶች ሁሉ ርኩሰታቸው በተቀደሰ ነበር አለ፡፡ሕዝቡም ሁሉ ወደርሷ ቀርበው እግዚአብሔር በዚህ ሥጋ ከሴት እንደተወለደ የሚያምን የተለየ ይሁን እግዚአብሔር በመወለጃ ማኅጸን እደተወሰነ የጡት ወተት በመመገብ በሴቶች የመወለድ ሥርዓት ነው ሁሉ ሕጻናትን እንደመሰላቸው የሚያምን የተረገመ ነው እያሉ በአፍረተ ሥጋዋ ላይ ምራቅ እንዲተፉ አዘዘ፡፡ ያንጊዜ ሊቁ ዮሐንስ አፈወርቅ ጠርዜቤጤር(ቀሲስ) በዚያ ነበር፡፡እንዲህ አለ‹‹እኔ እግዚአብሔር በድንግልና ወተት እንዳደገ በሕጻናትም ሥርዓት ሕጻናትን እንደመሰላቸው ከብቻዋ ከኃጢአትም በቀር የሰውን ሕግ ሁሉ እንደፈጸመ አምናለሁ›› ብሎ ኃፍረተ ስጋዋን በአፉ ሳመ፡፡በቤተ መቅደስም የነበረ የእመቤታችን ስዕል ‹‹አፈወርቅ›› ብላ ጠራችው፡፡ከዚያን ጊዜም በኋላ ‹‹ዮሐንስ አፈወርቅ›› እየተባለ የተጠራው፡፡
ታላቁ ሊቅ ኢትዮጵያዊው ዮሐንስ አፈወርቅ የተሰኘ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ስለርሱ ሲያደንቁ ‹‹እኔም ስለርሱ እላለሁ በእውት አፈወርቅ ፤አፈ ዕንቁ፤አፈ ጳዝዮን በድርሰቱ ቤተ ክርስቲያንን የሚያጌጣት አፈ ባህርይ በእውነት አፈ መዓር በቃ ጣፋጭነት ምዕመናንን የሚያለመልማቸው አፈ ሦከር በእውነት በትምህርቱ መዓዛ የምስጢር በጎችን ደስ የሚያሰኛቸው አፈ ሽቱ አፈ ርኄ ነው፡፡በእውነት በውግዘቱ ሥልጣን ከሃዲዮችን የሚቆርጥ አፈ ሰይፍ ፤አፈ መጥባህት ነው፡፡በእውነት የማይነዋወጥ ዓምድ የማይፈርስ መሠረት በእውነት ከሞገዶች መነሳት የሚዋኝ ዋናተኛ ነው በእውነት የማይፈርስ ግንብ በጠላት ፊት የሚጸና አዳራሽ ነው›› መጽሐፈ ምስጢር ገጽ 37
ተአምኖ ቅዱሳን በተባለው መጽሐፉት

የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የጵጵስና ሹመት
ቅ/ዮሐንስ ምንም ከባስልዮስ ጋር ለጊዜው ባይሾም በኋላ ግን ለመቀበል ችሏል፡፡በ347 ዓ/ም የቁስጥንጥንያ ፓትርያርክ የነበረው ኔክታርርዮስ ዐረፈ፡፡በዚያን ጊዜ ክፍት በሆነው በሮም ምስራቃዊ ግዛት ወዋና ከተማ በቁስጥንጥንያ መንበር ላይ ለመሾም በገሃድም ሆነ በስውር አጠቃላይ የሆነ ሽኩቻ ነበር፡፡ሆኖም ከትንሽ ወራት በኋላ በመንበሩ ላይ ለመተካት ሲናፍቁ ሆኖም ከትንሽ ወራት በኋላ በመንበሩ ላይ ለመተካት ሲናፍቁ የነበሩትን ጳጳሳት የሚያስደነግጥ ነገረ ተሰማ የአንጾኪያ ምዕመናን አባታችንን አንሰድም ብለው ረብሻ እንዳያስነሱና ሁከት እንዳይፈጠር ከእርሱ በከራሱም ሆነ ሌላ የሚመጣውን ተቃውሞ ዋጋ ቢስ ለማድረግ በዘዴ ከከተማው እንዲወጣ ከተደረገ በኋላ ከቤተ መንግስት በተላከ አጃቢ በአስቸኳይ ወደ ቁስጥንጥንያ ተወሰደ፡፡የአንጾኪያው ገዢ የነበረው ሰው የንጉሡ ትእዛዝ እንደደረሰው ቅ/ዮሐንስ አፈወርቅን ከከተማ ውጪ ወደሚገኝ አንድ ቤተ ክርስቲያን አብሮት እንዲሄድ ጠየቀው፡፡በእርሱ ሠረገላ ላይ እንደ ተቀመጠለትም ወዲያውኑ በፍጥነት ወደ ቁስጥንጥንያ ሊወስዱት ተዘጋጅተው የሚጠብቁ መኳንንትንና ወታደሮች ወደ ነበሩበት ወደ ቁስጥንጥንያ ወደሚወስደው ጎዳና ይዞት ሄደ፡፡በቤተ ክርስቲያን ታሪክና በቅዱሳን መዝገብ የጎላና ደማቅ ስምና ክብር ሊያሰጡት ወዳሉት የፈተናዎችና የተጋድሎዎች መድረክ በዚህ ዓይነት ድንገተኛ ሁኔታ ተወሰደ፡፡ወዴትና ለምን እንደሚወስዱት ያወቀው ቁስጥንጥንያ ከደረሰ በኋላ ነበር፡፡እንዲያ ባለ ሁኔታ ያለ ፈቃድና ያለ ውዴታው ፈቃደኝነቱን እንኳን ሳይጠየቅ በድንገት የቁስጥንጥንያ ሊቀ ጳጳሳ እንዲሆን ተደረገ፡፡የካቲት 26 ቀን 398ዓ/ም ብዙ ጳጳሳት ባሉበት በታላቅ ሥነ ሥርዓት በቁስጥንጥንያ መንበር ላይ 23ኛው የእስክንድርያ ፓትርያሊክ በነበረው በቴዎፍሎስ እጅ ፓትርያርክ ተደርጎ ተሸመ፡፡ፓትርያርክ ቴዎፍሎስም ያለውዴታው በንጉሡ በአርቃዴዎስ ትእዛዝ ቅ/ዮሐንስ አፈወርቅ ወርቅ ለመሾም ተገደደ፡፡ቴዎፍሎስም በቁስጥንጥንያ መንበር ላይ ለመሾም የራሱ ዕጩ አዘጋጅቶ የነበረ ቢሆንም ይህን ማድረግ እንደማይችል በመረዳቱ የንጉሡን ትእዛዝ ፈጸመ፡፡ ዮሐንስ አፈወርቅም ገና እንደተሸመ ያደረገው ነገር ለብዙ ጊዜ ዘልቆ የነበረውን የአንጾኪያ ቤተ ክርስቲያን ችግር መፍታት ነበር፡፡ዮሐንስ ‹‹አፈወርቅ›› ስለመባሉ
ዮሐንስ ‹‹አፈወርቅ›› ብላ ስም ያወጣችለት ቤተ መቅደስ የነበረች ስዕለማርያም ናት ፡፡በቁስጥንጥንያ እያለ በዚያ የሁለት ባህርይ ምንፍቅና ትምህርትን በልቡ የቋጠረ ንስጥሮስ ነበር፡፡ንስጥሮስ ምንፍቅናውን ሊቀ ጳጳስ ሆኖ እስኪሾምበት ጊዜ ድረስ አልገለጣትም፡፡ከጊዜያትም በአንዱ በዓል ዕለት ምዕመናኑ ቅርባን ሲቀበሉ አንዲት በወር ግዳጅ(የወር አበባ) ላይ ያለች ሴት ሳትነጻ ልትቀበል ቀረበች፡፡ሕዝቡም የመንፈስ ቅዱስ ጥላ ከእርሷ ሲርቅ አዩ፡፡የጸሐይ ጮራም በራሷ ላይ አላረፈም፡፡ሕዝቡም ፓትርያርክ ወደሆነው ንስጥሮስ ፊት አቆሟት ፡፡አንቺ ሴት ንገሪኝ የመንፈስ ቅዱስ ጥላ ካንቺ እስኪጠፋ ድረስ ኃጢአትሽ ምንድር ነው፡፡ንስጥሮስም ተቆጥቶ የሥጋዋ ዕርቃን እንደተገለጠ ቁልቁል ይሰቅሉት ዘንድ አዘዘ፡፡ እግዚአብሔር በዚህ ስጋ ከማርያም ከተወለደ መንፈስ ቅዱስ ይህችን ሴትእንደምን ናቃት፡፡እግዚአብሔር ከሴት ከተወለደ በማርያም ምክንያት ሴቶች ሁሉ ርኩሰታቸው በተቀደሰ ነበር አለ፡፡ሕዝቡም ሁሉ ወደርሷ ቀርበው እግዚአብሔር በዚህ ሥጋ ከሴት እንደተወለደ የሚያምን የተለየ ይሁን እግዚአብሔር በመወለጃ ማኅጸን እደተወሰነ የጡት ወተት በመመገብ በሴቶች የመወለድ ሥርዓት ነው ሁሉ ሕጻናትን እንደመሰላቸው የሚያምን የተረገመ ነው እያሉ በአፍረተ ሥጋዋ ላይ ምራቅ እንዲተፉ አዘዘ፡፡ ያንጊዜ ሊቁ ዮሐንስ አፈወርቅ ጠርዜቤጤር(ቀሲስ) በዚያ ነበር፡፡እንዲህ አለ‹‹እኔ እግዚአብሔር በድንግልና ወተት እንዳደገ በሕጻናትም ሥርዓት ሕጻናትን እንደመሰላቸው ከብቻዋ ከኃጢአትም በቀር የሰውን ሕግ ሁሉ እንደፈጸመ አምናለሁ›› ብሎ ኃፍረተ ስጋዋን በአፉ ሳመ፡፡በቤተ መቅደስም የነበረ የእመቤታችን ስዕል ‹‹አፈወርቅ›› ብላ ጠራችው፡፡ከዚያን ጊዜም በኋላ ‹‹ዮሐንስ አፈወርቅ›› እየተባለ የተጠራው፡፡
ታላቁ ሊቅ ኢትዮጵያዊው ዮሐንስ አፈወርቅ የተሰኘ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ስለርሱ ሲያደንቁ ‹‹እኔም ስለርሱ እላለሁ በእውት አፈወርቅ ፤አፈ ዕንቁ፤አፈ ጳዝዮን በድርሰቱ ቤተ ክርስቲያንን የሚያጌጣት አፈ ባህርይ በእውነት አፈ መዓር በቃ ጣፋጭነት ምዕመናንን የሚያለመልማቸው አፈ ሦከር በእውነት በትምህርቱ መዓዛ የምስጢር በጎችን ደስ የሚያሰኛቸው አፈ ሽቱ አፈ ርኄ ነው፡፡በእውነት በውግዘቱ ሥልጣን ከሃዲዮችን የሚቆርጥ አፈ ሰይፍ ፤አፈ መጥባህት ነው፡፡በእውነት የማይነዋወጥ ዓምድ የማይፈርስ መሠረት በእውነት ከሞገዶች መነሳት የሚዋኝ ዋናተኛ ነው በእውነት የማይፈርስ ግንብ በጠላት ፊት የሚጸና አዳራሽ ነው›› መጽሐፈ ምስጢር ገጽ 37
ተአምኖ ቅዱሳን በተባለው መጽሐፉት
‹‹ሰላም ለዮሐንስ አፉሁ ዘወርቅ ለጳጳሳት ሊቅ
እለይነባ ከናፍሪሁ ምድራሳተ ጽድቅ -
ከናፍሮቹ የእውነት ድርሳናትን የሚናገሩ
የጳጳሳት አለቃቸው አፉ የወርቅ የተባለ(ለሆነ) ለዮሐንስ ሰላምታ ይገባል››
ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የእረፍቱን መታሰቢያ ግንቦት 12 ቀን ትዘክረዋለች፡፡
ከጻፋቸው መጻሕፍት ጥቂቶቹ
67-የትርጓሜ ድርሳናት (በኦሪት ዘፍጥረት) 59-የትርጓሜ ድርሳናት (በመዝሙረ ዳዊት)
የኢሳይያስ ትንቢት ምዕራፍ አንድ ሐተታ የመጽሐፈ ኢዮብ የተወሰኑ ክፍሎች
የመጽሐፈ ምሳሌ የተወሰኑ ክፍሎች የትንቢተ ኤርምያስና ዳንኤል የትርጓሜ ድርሳናት እና ሌሎችም
90 -የትርጓሜ ድርሳናት (በማቴዎስ ወንጌል) 88 -የትርጓሜ ድርሳናት (በግብረ ሐዋርያት)
32 -የትርጓሜ ድርሳናት ወደ ሮሜ ሰዎች 44 -የትርጓሜ ድርሳናት በ1ኛቆሮንቶስ
30 -የትርጓሜ ድርሳናት በ2ኛ ቆሮንቶስ 24 -የትርጓሜ ድርሳናት ወደ ኤፌሶን ሰዎች
15 የትርጓሜ ድርሳናት ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 12 -የትርጓሜ ድርሳናት ወደ ቆላሲስ ሰዎች
11 -የስብከት ድርሳናት በ1ኛ ተሰሎንቄ 5 -የትርጓሜ ድርሳናት በ2ኛ ተሰሎንቄ
18 -የትርጓሜ ድርሳናት በ1ኛ ጢሞቴዎስ 10 -የትርጓሜ ድርሳናት በ2ኛ ጢሞቴዎስ
6 -ስድስት የትርጓሜ ድርሳናት ለቲቶ 3 -የትርጓሜ ድርሳናት ለፊልሞን
34 -የትርጓሜ ድርሳናት ለዕብራውያን ሰዎች እና ከ600 በላይ እጅግ ብዙ መጻሕፍቶችን ጽፏል፡፡

ከቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በረከትና ረድኤት ያሳትፈን !
ወስብሐት ለእግዚአብሔር