ዶግማ ክፍል ሁለት
ሰላም በዛሬዉ የነገረ ሃይማኖት ትምህርት የዶግማ ምንነት እንዲሁም የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ዶግማ(መሠረተ እምነት) ምንጮች ምን እንደሆኑ እናያለን መልካም ንባብ- መጽሐፍ ቅዱስ
መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔርን መገለጥ በጽሑፍ የምናገኝበት መጽሐፍ ነው፡፡ ይህ መጽሐፍ ከብዙ ሺህ ዓመታት በፊት በተለያየ ጊዜ በተነሱ ቅዱሳን አበው የተጻፈ መጽሐፍ ነው፡፡ በሁለት ኪዳኖችም የተከፈለ ነው በብሉይና በሐዲስ፡፡ ኪዳን ማለት ውል ስምምነት ማለት ነው ይህም የእውነት መጽሐፍ የሕግ የትንቢት የታሪክ የመዝሙር የጸሎት የመልእክት ክፍል ያለው ነው፡፡
የብሉይ ኪዳን መጽሐፍት በአምስት ክፍሎች የተከፈሉ ናቸው፡፡ የሕግ(የኦሪት) ክፍል መጻሕፍት የታሪክ ክፍል መጻሕፍት የትምህርት ክፍል መጻሕፍት የመዝሙርና የጥበብ ክፍል መጻሕፍት የትንቢት ክፍል መጻሕፍት የሐዲስም መጽሐፍት እንዲሁ የወንጌል ክፍል የታሪክ ክፍል የሥርዓት ክፍል የመልዕክት ክፍል የትንቢት ክፍል በማለት እንከፍላቸዋለን፡፡
ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችን ትምህርቷ የሚቀዳው ከዚህ መጽሐፍ እውነት ነው፡፡ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት የተመሩት አበው የጻፉትም ስለሆነ በመንፈስ ቅዱስ የምትመራው ቤተ ክርስቲያን ይህንን መጽሐፍ መሠረት በማድረግ ታስተምራለች፡፡ ሁላችንም ልናውቅና ልንረዳው የሚገባው እውነት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር የሚቃረን ትምህርት ጋር የሚቃረን ትምህርት አታስተምርም፡፡ የዘወትር ዝማሬዋ ቅዳሴዋ ውዳሴዋ መጽሐፍ ቅዱስ ነው፡፡
- ሥርዓተ አምልኮ
ከቤተ ክርስቲያን የሚለው ቃል ሦስት ዓይነት ሰዋስዋዊና ዘይቤአዊ ትርጕም አለው /አባ ጐርጐርዮስ (ሊቀ ጳጳስ)፣ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ በዓለም መድረክ፣ ገጽ 12-17/፡፡ የመዠመሪያው የተወሰነ ቦታን ያመለክታል፡፡ ይኸውም የክርስቲያኖች ቤት፣ መኖሪያ ማለት ነው /1ኛ ቆሮ.11፡18/፡፡ “ቤተ ክርስቲያን እንሒድ” /መዝ.121፡1/ ሲባልም ይኽን ፍቺ የያዘ ነው፡፡ በመጻሕፍትም ቤተ ክርስቲያን ብዙ ጊዜ የእግዚአብሔር ቤት ተብላለች /ዘፍ.18፡27፣ መዝ.5፡7፣ መዝ.26፡4፣ መዝ.83፡4፣ መዝ.92፡5፣ ሉቃ.2፡49፣ 1ኛ ጢሞ.3፡15፣ ዕብ.10፡21/፡፡ኹለተኛው ደግሞ ክርስቲያኖች ራሳቸው ቤተ ክርስቲያን ይባላሉ /1ኛ ቆሮ.3፡16፣ 1ኛ ቆሮ.6፡19/፡፡ ይኸውም በመንፈሳዊና በምሥጢራዊ ልደት ከክርስቶስ የተወለዱ፥ ርሱ አድሮባቸው የሚኖሩ፥ ከቅዱሱ ቅባት /1ኛ ዮሐ.2፡20/ እና ከሥጋ ወደሙ የተካፈሉ ምእመናንን ለማመልከት ነው፡፡ሦስተኛው ትርጕሙ ደግሞ የክርስቲያኖችን ኅብረት (ጉባኤን) የሚያመለክት ነው /1ኛ ጴጥ.5፡13/፡፡ እኛም በዚኹ ክፍል ትኵረት የምናደርገው በዚኹ በሦስተኛው ትርጓሜ ላይ ነው፡፡ በቤተ ክርስቲያን ክርስቲያኖች በኅብረት እግዚአብሔርን ያመልካሉ ይህም ሥርዓተ አምልኮ ቤተ ክርስቲያን በሠራችው ሥርዓት የሚካሄድ ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን ክርስቲያኖች በኅብረት የሚያከናውኖቸው ሥርዓተ አምኮዎች ቢኖሩም በዋንኝነት ቅዳሴ ቀዳሚ ነው፡፡ በብሉይ የሚከወነው ሥርዓተ አምልኮ በኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ በመሰብሰብ የሚከወን ነው፡፡ ሥርዓተ አምልኮ በብሉይ ኪዳን ሥርዓተ አምልኮው ጾም ጸሎቱ በሙሴ ሕግ መሠረት የሚከወን ነበር ይህም በኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ ወይም በተለያዩ ቦታዎች በተሠሩ ምኩራቦች ይደረግ ነበር፡፡ ምኩራቦቹ በተለያየ ቦታ የሚሰሩ ሲሆን ቤተ መቅደሱ ግን አንድ እርሱም በኢየሩሳሌም የሚገኝ ነው፡፡ በሙኩራባቸው እስራኤላዊያን ለጸሎት ይሰባሰባሉ መጽሐፍትን ያጠናሉ ይሰብካሉ፡፡
በሓዲስ ኪዳን የሚካሄደው ሥርዓተ አምልኮ ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ነው ስለዚህም በብሉይ የነበረው ሥርዓተ አምልኮ በጌታችን በኢየሴስ ክርስቶስ አማናዊ ሥርዓተ አምልኮ ተተክቷል፡፡ በብሉይ የሚነበቡ መጻሕፍት የሚዜሙ መዝሙራት ክርስቶስን የሚሰብኩ ነበሩ በሐዲስ ደግሞ በጉልህ የሚሰብኩ ሆነዋል፡፡ እንዲሁም የነበረው መሥዋዕት በክርስቶስ አማናዊ ሥጋና ደም ተለውጧል፡፡
የአይሁድም የጾም ሥርዓት እንዲሁ አዲስ ትርጉም አግኝቶል፡፡ የፍሲካ ጾም የክርስቶስን ሞትና ትንሣኤ የምናስብበት የምንዘክርበትና የምናከብርበት ሆኖል፡፡ የአይሁድ ጰንጠቆስጤ በዓልም የመንፈስ ቅዱስን ለሐዋርያት መውረድ የምንዘክርበት በዓል ሆኖል፡፡
የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ምሥጢራትና ሥርዓተ አምልኮ ቀዳሚው የክርስትና መሠረተ እምነት መሠረት ነወ፡፡ ሥርዓተ አምልኮው መጽሐፍ ቅዱስና ቅዱስ ትውፊት የተረሱ ሳይሆኑ በክርስትና የዕለት ተዕለት ሕይወት ውስጥ የምናገኛቸው ያለፉ ሳይሆኑ አሁንም ያሉ የምንገለገልባቸው ናቸው፡፡ በጸሎትና በቤተ ክርስቲያን ምሥጢራት አማካኝነት የሰው ልጅ ከእግዚአብሔር መማር ይችላል ጌታችን እንዳለ ‹‹ከእግዚአብሔር ዘንድ የተማሩ ይሆናሉ››ዮሐ 6÷45 ከዚህም በተጨማሪ ሥርዓተ አምልኮን ቤተ ክርስቲያኒቱ አገልግሎትን ምሥጢራቷን የሚያጠና ሰው የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን መሠረተ እምነት ማወቅ ይችላል፡፡

ይቆየን
ወስብሐት
ለእግዚአብሔር
No comments:
Post a Comment