ክርስቶስ ከሊቃውንት መካከል አልተነሣም፡፡ በሊቃውንትም አልተመረጠም፡፡ ደግሞም እንደ ሃይማኖት መሪዎች አልሄደም፡፡ ለምሳሌ ከኃጢአተኞች ጋር ይበላ ነበር፡፡ ሰዎች በእርሱ ሕይወትና ትምህርት ሲደነግጡ ባየ ጊዜ ሕግን ሊፈጽም እንደመጣ ገለጸ፡፡
ክርስቶስ ሕግን እንዴት ፈጸመ?
በራሱ ሕይወት የሕግን ትእዛዝ ሁሉ በመፈጸም፡፡ ከሕግ በታች ሆኖ በመኖር፡፡ /ገላ 4÷4/
በራሱ ሞት መሥዋዕትን ሁሉን በመፈጸም፡፡ /ዕብ 9÷25-26/
የፈሪሳውያንን አተረጓጎም በማፈራረስና ትክክለኛውን ትርጓሜ በማስተማር፡፡ /ማቴ 5÷21-48/
የእግዚብሔርን ቃል ኪዳን በመግለጥ፡፡ ለምሳሌ ምሥጢረ ጥምቀትንና ቅዱስ ቁርባንን በመመሥረት፡፡ ሕግን በፊደል ብቻ ሳይሆን በመንፈሳዊ መንገድ በመግለጥ ሕግን እንድንፈጽም መንፈስ ቅዱስን በመስጠት፡፡ /ሮሜ 8÷2-4/
ፈሪሳውያን ከሕዝብ የተለዩ የሃይማኖት መሪዎች ናቸው፡፡ የአባቶችን ወግ በጥብቅ ይጠብቁ ነበር፡፡ በሃይማኖታቸውም ይኮሩ ነበር /ሉቃስ 19÷9-14/ ሆኖም በእግዚአብሔር ፊት በቂዎች አልነበሩም፡፡
የፈሪሳውያን ዓይነት
- የትከሻ ፈሪሳዊ፡- መልካም ሥራውን እንደ ባጅ ሠርቶ በትከሻው ይይዛል፡፡
- የቆይታ ፈሪዊ፡- መልካም ሥራውን ሰዎች እንዲያዩለት ሰዎችን የሚያስቆም፡፡
- ዕውር ፈሪሳዊ፡- ሴቶችን እንዳያይ ዓይኑን ሸፍኖ የሚሄድ፡፡
- ምግባር ቆጣሪ ፈሪሳዊ፡- ሁልጊዜ መልም ሥራውን እየደመረ ከኃጢአቱ ጋር የሚያወዳድር፡፡
- መፍቀሬ እግዚአብሔር ፈሪሳዊ፡- እንደ አብርሃም ያለ ነው፡፡
ፈሪሳውያን ስህተታቸው ምን ነበር?
ሃይማኖታቸው ልብ ወደ መለወጥ አያደርስም ነበር፡፡ ማር 7÷14-23
ሥነ
ሥርዓት እየሰበኩ ሌላ ሕግንና ትዕዛዝን ይረሱ ነበር፡፡ ማቴ 23÷23
በእግዚአብሔር ትዕዛዝ ላይ የራሳቸውን ትዕዛዝ ይጨምሩ ነበር፡፡ ማቴ 5÷43
እግዚአብሔርን ሳይሆን እራሳቸውን ያመሰግኑ ነበር፡፡ ሉቃስ 18÷9-14
No comments:
Post a Comment