Saturday, 25 February 2017

‹‹ጽድቅን የሚራቡና የሚጠሙ ብፁዓን ናቸው፣ ይጠግባሉና›› ማቴ 5÷6

ክፍል ሦስት

ጽድቅን የሚራቡ የሚጠሙ ማለት፡- ጽድቅን እንደ እህል የሚራቡ እንደ ውኃ የሚጠሙ፣ በየጊዜው የሚፈልጉ እርሱን ብቻ የሚራቡና የሚጠሙ ማለት ነው፡፡ ጽድቅን ለማግኘት ለጽድቅ ለመብቃት ሕግጋትን ለመፈጸም ሲሉ አሁንም ነገም እርሱን ብቻ የሚራቡ እርሱን ብቻ የሚጠሙ ብፁዓን ናቸው ሲል ነው፡፡

ስለጽድቅ ብለው ረኃቡንና ጥሙን ታግሰው፣ የእግዚአብሔር መንግሥት በመብል በመጠጥ አትወረስም፣ አንድም ቢፈጽማት የእግዚአብሔርን መንግሥት የምታሰጥ አትወረስም፣ አንድም ቢፈጽሟት የእግዚአብሔርን መንግሥት የምታሰጥ ወንጌል በመንፈስ ቅዱስ የሆነ እምነትን ተስፋንና ፍቅርን እንጂ መብል መጠጥን አትሰብክም አንድም ልብላ ልጠጣ በምትል ሰውነት ወንጌል አትዋሐድም /ሮሜ.14፡19/ መብል ግን ወደ እግዚአብሔር አያቀርበንም ባንበላ ምንም አይጐድልብንም ብንበላም ምንም አናተርፍም /1ኛ.ቆሮ.8፡8/፡፡ መብል ለሆድ ነው፣ ሆድም ለመብል ነው፤ እግዚአብሔር ግን ይህንም ያንም ያጠፋቸዋል፡፡ ብለው የሚጾሙ ሰዎች ብፁዓን ይባላሉ፡፡

“ጽድቅን የሚራቡና የሚጠሙ” ሲልም እውነት በሕይወታቸው ነግሣባቸው የሚኖሩትን ያመለክታል፡፡ ጾመ ሙሴ ዘዳ.9፡9፣ ጾመ አስቴር 4፡16፣ 9፡31 ጾመ ዳንኤል፣ ዳን.10፡2 ጾመ ዳዊት፣ 2ኛ ሳሙ.12፡22 መዝ.108፡24፣ ጾመ ሐዋርያት የሐዋ.13፡2 ወዘተ ተመልከት፡፡

 

 

No comments:

Post a Comment