Saturday, 18 February 2017

‹‹በመንፈስ ድሆች የሆኑ ብፁዓን ናቸው መንግስተ ሰማያት የእነርሱ ናትና››(ማቴ 5÷3)



ክፍል አንድ
‹‹ሕዝቡንም አይቶ ወደ ተራራ ወጣ፤ በተቀመጠም ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ወደ እርሱ ቀረቡ፣ አፉንም ከፍቶ አስተማራቸው እንዲህም አለ››(ማቴ. 5 1÷1) ወርእዮ ብዙኃነ አእዛበ ዓረገ ውስተ ደብር ወነበረ ብዙ ሰዎችን ባየ ጊዜ ከተራራ ወጥቶ ተቀመጠ፡፡ ምነው አእዛብ አላቸው  እስራኤላዊያን አይደሉምን ቢሉ ብዛታቸውን ለመግለጽ ነው፡፡ ግብራቸው የአእዛብ ነውና አእዛብ አላቸው፡፡ ሰው ሲበዛ ከመርከብ ከተራራ ተቀምጦ ማስተማር ልምድ ነውና፡፡ መምህር ከፍ ባለ ቦታ ሰማዕያን ዝቅ ባለ ቦታ የሆኑ እንደሆን ትምህርት ለሰምዕያን ይረዳልና፡፡ ወይረድ ከመ ጠል ነቢብየ ቃሌ እንደ ጠል ይወርዳል እንዲል በደብረ ሲና(በሲና ተራራ) ሕግን ለሙሴ የሠጠው እኔ ነኝ ለማለት ሰባርዮስ የተባለው መናፍቅ እግዚአብሔር ፍጹም አንድ ገጽ(አንድ አምላክ) እንጂ ሦስትንት የለበትም አለ ይህንንም ሲያብራራ አንዱ አምላክ በተለያየ ወቅት በተለያየ ሁኔታ ተገለጠ እንጂ ብሏል (እንደ አብ በብሉይ እንደወልድ በሐዲስ እንደ መንፈስ ቅዱስ በዘመነ ሐዋርያት) ይህ የአምላክ አባባል አንድ ገጽ ነን ወደሚያስብል ትንታኔ የሚገፋ አይደለም ይልቁንም በፍቃድ አንድ መሆናቸውን የሚያስገነዝብ ነው፡፡አንድም ወደ ተራራ የወጣው ልዑለ ባሕርይ መሆኑን ለመግለጽ ሲሆን በተጨማሪም ከሁሉ ባላይ የሆነች ከሁሉ በላይ ልዕልት ሕግ ሠራው ሲል ነው፡፡
እስካሁን የአምስት ገበያ ሕዝብ ሲከተለው ነበር፡፡ ይህ የአምስት ገበያ ሕዝብ ገሚሱ(አንዱ ገበያ) ቃሉን ለመስማት ገሚሱ መልኩን ለማየት ገሚሱ ከእጁን ተዓምራት ሽተው ገሚሱ እክለ በረከት ፍለጋ ገሚሱም መንግስቱን ያወርሰናል በለው ይከተሉት ነበር፡፡  ከእንግዲህ ወዲህ በብፁዓን አዋጅ ይለያቸዋል፡፡ንጉሥ መንግስቱ እስኪደላደል ድረስ ሌባውን ወንበዴውንም ያስከትላልና ከተደላደለ በኋላ ግን ሕግ ሰርቶ ያጠፋውን ቀጥቶ እንዲኖር እንዲሁ ነው፡፡

ነዳያነ መንፈስ


በመንፈስ ድሆች(ነዳያነ መንፈስ) የሆኑ ማለት የዋሐን ትሑት የሆኑ ማለት ነው፡፡ እንዲህ ያሉ ሰዎች ራሳቸውን ችሎታ እንዳላቸው አድርገው አይቆጥሩትም፡፡ በራሳቸው ዘር፣ ጠባይ፣ ተፈጥሮ፣ ሀብት፣ አቅምና ችሎታ ተስፋ አያደርጉም፡፡
ነዳያን በመንፈስ ማለት ያልተማሩ ማለት አይደለም፡፡ ነገር ግን ማንነታቸውን አውቀው በፈቃዳቸው ሁሉን የተዉ ማለት ነው፡፡ ነዲያን በመንፈስ በእግዚአብሔር ፊት የተሰበረና የተዋረደ ልብ ይኖራቸዋል፡፡ ይህን የሚያደርጉት ከእነሱ እጅግ የሚበልጥ ሁሉን የሚያውቅ አምላክ መኖሩን በማሰብ ነው፡፡
አንድ ሰው ራሱን ዝቅ ካላደረገ የትኅትናም ሥራ ካልሰራ አምላካዊ ጸጋን አያገኝም እርሱም አይፈልገውም፤ ሁሉ ያለው ይመሰለዋልና፡፡ ክርስቲያን የሆኑ ሁሉ ግን ይህን የትሩፋት ሥራ መንገድ መከተል ራስን ከመውደድ መራቅ እያለውም እንደሌለው ሆኖ መታየት ተገቢው ነው፡፡
መኮንነ ተሰሎንቄ ዮሐንስ አፈ ወርቅን እንደጠየቀው ብፁዓን ከበቁ በኋላ ነዳያነ አእምሮ መሆናቸው እንደምንድነው? አለው ዮሐንስም ‹‹አንተ በሃገርህ እንደምን ትኖራለህ›› አለው ‹‹ከሁሉ በላይ ነኝ›› አለው እልፍ ብለህ ‹‹በቂሳርያሳ›› ‹‹የምበልጣቸውም የሚተካከሉኝም አሉ›› አለው ዝቅ እያለ ሄደ፡፡ ‹‹አንጾክያስ አለው›› ‹‹የሚያውቀኝ የለም›› አለው ቅዱሳንም በአእምሮ ነዳይ የሆኑት ከበላላቸው ያለውን ፈጣሬ መጋቤ ዓለማትን እያዮ ራሳቸውን ዝቅ ያደርጋሉ እንጂ አይታበዩም፡፡ በምግባር በሃይማኖት በንስሐ ድሆች ነን ብለው የሚያዝኑ የሚተክዙ ንዑዳን ክቡራን ናቸው፡፡
ጌታችን በመንፈስ ድሆች  ያላቸው ሰዎች ራሳቸውን ችሎታ እንዳላቸው አድርገው አይቆጥሩትም፡፡ በራሳቸው ዘር፣ ጠባይ፣ ተፈጥሮ፣ ሀብት፣ አቅምና ችሎታ ተስፋ አያደርጉም፡፡
ነዳያን በመንፈስ ማለት ያልተማሩ ማለት አይደለም፡፡ ነገር ግን ማንነታቸውን አውቀው በፈቃዳቸው ሁሉን የተዉ ማለት ነው፡፡ ነዲያን በመንፈስ በእግዚአብሔር ፊት የተሰበረና የተዋረደ ልብ ይኖራቸዋል፡፡ ይህን የሚያደርጉት ከእነሱ እጅግ የሚበልጥ ሁሉን የሚያውቅ አምላክ መኖሩን በማሰብ ነው፡፡
አንድ ሰው ራሱን ዝቅ ካላደረገ የትህትናም ሥራ ካልሰራ አምላካዊ ጸጋን አያገኝም እርሱም አይፈልገውም፤ ሁሉ ያለው ይመሰለዋልና፡፡ ክርስቲያን የሆኑ ሁሉ ግን ይህን የትሩፋት ሥራ መንገድ መከተል ራስን ከመውደድ መራቅ እያለውም እንደሌለው ሆኖ መታየት ተገቢው ነው፡፡
የምንመካበት ምንነታችን የእኛ አይደለም፡፡ የምንመካበትን ዕውቀት ሐብት  ጉልበት ሥልጣን የሰጠን አምላካችን ነው፡፡ ነዳያነ መንፈስ ይህንን መመልከት የሚችሉ ናቸው፡፡ የእነርሱን ዕውቀት ከአምላክ ፍጹም እውቀት ጋር እያነጻጸሩ ኢምንትና ትንሽ መሆኑንን ይገነዘባሉ፡፡ ሐብታቸውን ጉልበታቸውንም ከሁሉ ኃያል ሁሉ በእጁ ከሆነው አምላክ ጋር እያነጻጸሩ ራሳቸውን በጌታ ፊት ያዋርዳሉ፡፡ መንግስቱን የሚርሱ እንደነዚህ ያሉት ናቸው፡፡ መመካታቸውን በአምላክ ላይ ያደረጉ በራሳቸው የማይመኩ የመንግስቱ ወራሾች ናቸው፡፡
ይቆየን

No comments:

Post a Comment