ሀቢብ ጊዮርጊስ ማነው?
ሀቢብ ጊዮርጊስ በ1976 ዓም በካይሮ ከተማ ተወለደ፡፡ አባቱ በሕጻንነቱ ስለሞተበት እናቱ ለብቻዋ በፍቅረ ቤተ
ክርስቲያን አንጻ አሳደገችው፡፡ ትምህርቱን የተከታተለው አቡነ ቄርሎስ አምስተኛ በመሠረቱት ትምህርት ቤት ውስጥ
ነው፡፡ በዚያውም ዲቁና ተቀብሎ ማገልገል ሲጀምር ዕድሜው አሥራ ሰባት ብቻ ነበር፡፡
ሊቀ ዲያቆናት ሀቢብ ጊዮርጊስ
በወቅቱ ፓትሪያርኩም በኮፕቲክ ቤተ ክርስቲያን የተከሰቱትንና የቤተክስቲያኒቱን አገልግሎት እጅጉን የጎዱ እንቅፋቶች በማስወገድ ወደ ለውጥ መንቀሳቀስ የጀመሩበት ጊዜ ነበር፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥ ደግሞ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ሆኖ የተገኘው የሰለጠኑ ካህናትን የሚያፈራ ተቋም መክፈት ስለነበር ለዚህ ወሰኝ ተልዕኮ የሚመጥን ይሆናል የሚሉትን ሰው ሲፈልጉ ምርጫቸው ያረፈው በወጣቱን አገልጋይ ሀቢብ ጊዮርጊስ ላይ ሆነ፡፡
ሀቢብ ጊዮርጊስ ኃላፊነቱን እንደተቀበለ ትኩረቱን ያደረገው ለተቋሙ ግንባታ የሚያስፈልገውን ገቢ ማሰባሰብ ላይ ነበር፡፡ በውጤቱም ከሀገር ሀገር እየተዘዋወረ ባደረገው ቅስቀሳ የምእመኑን የታመቀ ፍቅር ማቀጣጠል የቻለ ሲሆን በጥቂት ቀናት ውስጥ የተገኘው ድጋፍም በቂ ሆኖ ስለተገኘ ኮሌጁ እንደታሰበው ተገንብቶ ለአገልግሎት በቅቷል፡፡
ኮሌጁ ተከፍቶ ማስተማር ሲጀምር ደግሞ ሀቢብ ጊዮርጊስም ከመጀመሪያዎቹ ተማሪዎች አንዱ ለመሆን የቻለ ሲሆን በወቅቱ የተከሰተውን የመምህራን እጥረት መቅረፍ ግድ ሲሆን ደግሞ ተማሪ በሆነበት ዓመታት መምህርነትንም ደርቦ ያዘ፡፡
የሀቢብ አስደናቂ አገልግሎት በስፋት የተገለጠው ከተመረቀ በኋላ ሲሆን በሰባኪነት ተሰማርቶ የሰበካቸው ስብከቶች በወቅቱ ሰማዕያኑን የመሰጡ ብቻ ሆነው አልቀሩም፡፡ ይልቁንም ብዙዎች ከሞተ በኋላ እንኳ ሳይቀር የሚያስተውሷቸው እንዲሁም ታትመው የብዙዎችን ሕይወት ሲለውጡ የሚኖሩ ሆነዋል፡፡
ለመሠረተው ኮሌጅ ማደግ ከፍተኛ ራእይ የነበረው ሀቢብ ጊዮርጊስ በዚያ ወቅት ከሠራቸው ሥራዎች መሀከልም ጉልህ የነበረው በኮሌጁ ዙሪያ የነበሩ ቦታዎችን ባገኘበት አጋጣሚ ሁሉ በግል ገንዘቡ እየገዛ ለኮሌጁ ማስፋፊያ ይሆን ዘንድ ማበርከቱ ይጠቀሳል፡፡ በዚህና መሰል ወደር የለሽ ተግባራቱና ከፍ ያለ ትጋቱ የተደሰቱት ፓትሪያርኩ አቡነ ቄርሎስ የሊቀ ዲያቆንነት ማዕረግን ሰጡት፡፡
የሀቢብ ጊዮርጊስ ቀጣይ የአገልግሎት ምዕራፍ የኮሌጁ ርዕሰ መምህር በሞት በተለየ ጊዜ እርሱን በመተካት የርዕሰ መምህርነትን ኃላፊነት ሲጨምር የሚጀምረው ነው፡፡ በዚህ ወቅት ከሠራቸው ተግባራት መሀከልም ዋነኛው ኮሌጁን ከውጪ ተጽእኖ የተጠበቀ እንዲሆነ ማድረጉ የመጀመሪያው ሲሆን በመከላከል ብቻ ላይም ሳይወሰን ተቋሙ የኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያንን ትምህርት በምልዓት የሚያንጸባርቅ መብራት ማድረግ መቻሉ ደግሞ ሌላው ዘለዓለማዊ ስኬቱ ነው፡፡
በተለይ ኦርቶዶክሳዊያን ደቀመዛሙርት ወደ አንግሊካን የትምህርት ተቋማት ሄደው የከፍተኛ ትምህርት እንዲከታተሉ የሚል ግፊት ሲነሳና እንዲሁም የአንግሊካን ምሁራን በኮፕቲክ የሥነ መለኮት ኮሌጅ እንዲያስተምሩ ሐሳብ ሲመጣ ይህን በመቃወም ግፊቱ ከሐሳብ አልፎ በተግባር እንዳይውል ማድረግ መቻሉ ነበር፡፡ የሀቢብ ልዩ ችሎታ የነበረው በመቃወምና በመከላከል ላይ ብቻ አለመወሰኑ ይልቁንም ከተቃወመው ሐሳብ የተሻለ አማራጭ እንዲኖር መሥራቱ ነው፡፡ በዚህም የተነሣ በኦርቶዶክሳዊው የትምህርት ተቋም ውሰጥ የአንግሊካን ሊቃውንት እንዳያስተምሩ በማለት አጥብቆ ሲቃወም በምትኩ ደግሞ ኦርቶዶክሳዊውያን አስተምህሮ በጥልቀት የተረዱ ቀሳውስት እንዲኖሩ አጥብቆ ይሠራ ነበር፡፡
ሌላው የሀቢብ ጊዮርጊስ ጅምር የነበረውና ባለፉት ቅርብ ዓመታት ውሰጥ ለግብጽ ቤተ ክርስቲያን መነቃቃት መንስኤ የሆነው ተግባር ደግሞ ኮሌጁ የማታ የትምህርት መርሐ ግብር እንዲጀምር ማድረጉ ነው፡፡ የዚህ አዲስ መርሐ ግብር መከፈት በርካታ ምሁራንና ወጣቶች ወደ ቤተክርስቲያን እንዲመጡና በትምህርተ ሃይማኖት እንዲታነጹ እድል ከመስጠቱም በላይ በዚህ ምክንያትነት የግብጽ የትምህርት ሚኒስቴር ለኮሌጁ እውቅና ሊሰጠው ችሏል፡፡ በማታው መርሐ ግብር ተካፍለው ከነበሩ ወጣት ምሁራን መካከል ፖፕ ሺኖዳ ሣልሳዊ አንዱ ናቸው፡፡
ከዚህ ሁሉ በላይ ለኮሌጁ እድገት ዕድሜውን ሁሉ የተጋው ሀቢብ ጊዮርጊስ ኮሌጁን በማሳደግ ዓለም አቀፍ ደረጃውን እንዲጠብቅ ማድረግ የቻለ ሲሆን መደበኛው የሥነ መለኮት ትምህርት በፍልስፍናና በሥነ ልሳን ትምህርቶች የታጀበ እንዲሆንና እንዲሁም በብቁ መምህራን የተሞላ በማድረግ የምርጥ አገልጋዮች መፍለቂያ እንዲሆን ስላደረገው በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ በቤተ ክርስቲያን ክህነት የሚቀበሉ ሁሉ የኮሌጁ ዲፕሎማ እንዲኖራቸው የሚያስገድድ ሕግ ተሠራ፡፡
ሀቢብ ጊዮርጊስ በሕይወት ኖሮ የኮሌጁን አርባኛ ዓመት ለማክበር የበቃ ሲሆን በዚያው ዓመትም ‹‹የነገረ መለኮት ኮሌጅ ትናንትናና ዛሬ›› የሚለውን መጽሐፉን ለሕትመት አብቅቷል፡፡
የሰንበት ትምህርት ቤት ጅማሮ
ሀቢብ ጊዮርጊስ የመጀመሪያውን ሰንበት ትምህርት ቤት በማቋቋም ሥራውን ሲጀምር የ24 ዓመት ወጣት ነበር፡፡ ጊዜውም 1900 ዓም ቦታው ካይሮ ከተማ ውስጥ በሚገኙ የኮፕቲክ አብያተ ክርስቲያናት፡፡ ጅማሮው ህጻናትን ሰብስቦ በማስተማር ነበር፡፡ በእግዚአብሔር ቸርነት አገልግሎቱ ተባርኮለት ሥርዓተ ትምህርት ለመቅረጽ ማዕከላዊ ኮሚቴ አቋቋመ፡፡ ይህም ውጥን በሀገሪቱ በሞላ ተስፋፍቶ አገልጋዮች እጅግ የበዙ ሆኑ፡፡ በሀቢብ ጊዮርጊስ የተቋቋሙ ሰንበት ትምህርት ቤቶች የኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ በወጣቶች ልቡና ውስጥ መተከል እንዲችል ሕያው ምስክር ሆኑ፡፡
ከዚሁም ጋር ተያይዞ በግብጽ የመጻሕፍትና የበራሪ ጽሑፎች ስርጭት፣ ዐውደ ርእያት፣ ሴሚናሮች፣ ኮንፈረንሶች፣ ወደ አብያተ ክርስቲያናትና ወደ ገዳማት የሚደረጉ መንፈሳዊ ጉዞዎችንና የመሳሰሉ እንቅስቃሴዎች የመነጩት ከሰንበት ትምህርት ቤቶች ነው፡፡
ሊቀ ዲያቆናት ሀቢብ ጊዮርጊስሊቀ ዲያቆናት ሀቢብ ጊዮርጊስ

የሰንበት ት/ቤቱ መስፋት ምን ጠቀመ?
ሀቢብ ጊዮርጊስ የመሠረተው የሰንበት ትምርት ቤት እንቅስቃሴ ከተስፋፋ በኋላ በወቅቱ ቤተ ክርስቲያንን ይፈታተኑ የነበሩ ችግሮችን በእግዚአብሔር እርዳታ መፍታት የሚችል ሊሆን በቅቷል፡፡ ከነዚህም መሀከል የሚከተሉት ዐበይት ተግባራት አይዘነጉም፡፡• መጽሔቶችን በማሳተም ስብከተ ወንጌልን የማስፋፋት ሥራ በብዛት የተሠራው በዚህ ዘመን ነው፡፡
• ወደ ቤተ ክርስቲያን ሳይመጡ የቀሩ ወጣቶች ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዲቀርቡ አድርጓል፡፡
• በዘመኑ የነበሩ እንግሊዛውያን ሚስዮናውያን የቅኝ ገዢዎችን አካሄድ በመከተል ኦርቶዶሳውያንን ከእምነት ለማስወጣት ይጥሩ ነበር፡፡
• ሚስዮናውያኑ በተለይ የትምህርት ዕድል በመስጠትና በመሳሰሉ ዘዴዎች በመጠቀም ወጣቶችን ለማማለል ይሞክራሉ፡፡ ቤት ለቤት እየዞሩ ማራኪነት ባላው ጽሑፎችና ባሸበረቁ ሥዕላት ያዘጋጁዋቸውን ብሮሹሮች በመበተን የሚሠሩት የቅሰጣ ተግባር አልበቃ ብሏቸው የእናት ቤተ ክርስቲያንን ስም ጥላሸት እስከ መቀባት ደርሰው ነበር፡፡ በዚህም ተግባራቸው ብዙዎች ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን ጠፍተዋል፡፡
• ይህን ችግር ለመቅረፍ የተነሡት የዘመኑ ፓትርያርክ ከሀቢብ ጊዮርጊስና ከሌሎች ሁለት ምእመናን ጋር በመሆን ሐዋሪያዊ ጉዞ አደረጉ፡፡ በዚህ ጊዜ ነበር ሀቢብ በውጪ የሚገኙ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ወጣቶችን የሚሰበስብበትን ዘዴዎች መመልከት የቻለው፡፡ ወዲያውኑ ከጉዞው መልስም ህጻናትና ወጣቶች ተሰብስበው የሚመሩባቸውን ሰንበት ትምህርት ቤቶችን ለማደራጀትና የሚመጥናቸውን ሥርዓተ ትምህርት ለመቅረጽ መንፈሳዊ መዝሙራትንም ለማዘጋጀት አቅዶ ሥራውን ጀመረ፡፡ በዚህ ሥራውም በሌላ እምነት ተማርከው የነበሩትን መመለስ ችሏል፡፡
ሀቢብ ጊዮርጊስ ጸሐፊነትን፣ አስተዳዳሪነትን እና ሰባኪነትን በእኩል ደረጃ አሳክቶ መያዝ የቻለ ሰው ነው፡፡ በአጠቃላይ ሠላሳ መጽሐፍትን አዘጋጅቷል፡፡ በመጨረሻ ዕድሜው ሲገፋ ጤናውም እየታወከ መጣ፤ ቤቱም በደቀ መዛሙርቱ መሞላት ጀመረ፡፡ ለእርሱም የነበራቸውን ፍቅር ለመግለጽ መኝታን ከበው አብረውት ጸሎት በማድረግ ራሱ የደረሳቸውን መዝሙራትም ይዘምሩለት ነበር፡፡
በመጨረሻ ሀቢብ ጊዮርጊስ ኦገስት 22 ቀን 1951 ዓ.ም አረፈ፡፡ ዜና እረፍቱም በሀገረ ግብፅ ከዳር እስከ ዳር ተሰማ፡፡ ቀብሩም በሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች በተገኙበት ሴፕተምበር 27 ቀን 1951 ዓ.ም ተፈጸመ፡
ምንጭ፡-ምንጭ፡-
ሊቀ ዲያቆናት ሀቢብ ጊዮርጊስ እና ሥራዎቹ፣ ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
No comments:
Post a Comment