በዲ/ን ያሬድ መለሰ
መስከረም ፪ ፳፻፲
መስከረም ፪ ፳፻፲
መግቢያ
በዛሬው ጽሑፌ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ሐዋርያዊት ናት ማለታችን እንዴት ነው የሚለውን ለመዳሰስ እንሞክራለን፡፡ በዚህ ዘመን ኹላችንም እንደምናውቀው ኹሉም በሚባል መልኩ ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያንን የሚለውን የቤተ ክርስቲያኒቱን መለያ የሚጠቀምበት ዘመን ላይ ደርሰናል፡፡ አንዳንዶች ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያን መባል ራስን ወይም ‹‹የቤተ ክርስቲያኒቱን›› መሪ ሐዋርያ ነቢይ ብሎ በመሰየም ይመስላቸዋል፡፡ የሐዋርያትን ሥራ ሳይሰሩ ሐዋርያ የወንጌላዊያንን ሥራ ሳይሰሩ ወንጌላዊ የነቢይን ሥራ ሳይሰሩ ነቢይ መባል በተለመደበት ዘመን እውን ሐዋርያዊ ሐዋርያዊነት ለመባል መስፈርቱን መመልከት እንደሚያሻ ኹላችንም መረዳት አለብን፡፡
ሐዋርያዊነት የቤተ ክርስቲያን ባሕርያት መካከል አንዱ ባሕርይ ነው፡፡ አበው ቅዱሳን በጉባኤ ከወሰኑት የቤተ ክርስቲያን ባሕርያት መካከል የሚመደብ ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን ቅድስት አንዲት ዓለማቀፋዊት(የኹሉ) እንዲሁም ሐዋርያዊት ናት፡፡ቤተ ክርስቲያን የተመሠረተችው በቅዱሳን ሐዋርያት እምነት መሠረት ላይ ነው፡፡ሐዋርያት የመስራቿን ማንነት በሚያውቁና በሚያምኑ በዓይን ያዩ በጆሮ የሰሙ እርሱን(ክርስቶስን) ይመስላሉ፡፡ እርሱ የባሕርይው የሆነውን ኃላፊነት ለቅዱሳን ሐዋርያት በጎቼን ጠብቁ ብሎ አስተላልፎል፡፡ ስለ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ጳውሎስ ሲናገር ‹‹በሐዋርያት በነቢያት መሠረት ላይ ታንጻቹኃል ክርስቶስም ራሷ ነው፡፡›› ብሎናል (ኤፌ 2፥20) የቤተ ክርስቲያን መሠረት የቅዱሳኑ ትምህርት መሆኑን ጌታም በሥጋዌ ዘመኑ ስያስተምር ለሐዋርያው ለቅዱስ ጴጥሮስ ‹‹ አንተ አለት(መሠረት) ነህ በአንተ መሠረት ላይ ክብርት ቤተ ክርስቲያንን አንጻለሁ የሲኦልም ደጆች አይችሏትም›› ብሎ በሐዋርያው በቅዱስ ጴጥሮስ ወልደ አብ ወልደ ማርያም(ወልድ ዋሕድ ) በሚለው ትምህርት ላይ መታነጹን ነግሮናል፡፡(ማቴ 16፥17)

ሐዋርያዊት የሚለው መታወቂያ ለቤተ ክርስቲያን እንዴት ተሰጠ
አባቶቻችን ሐዋርያዊት የሚለውን የቤተ ክርስቲያን መታወቂያ ለእውነተኛይቱ ቤተ ክርስቲያን መለያ እንዲሆን ያስቀመጡበት ምክንያትን ቀድመን ለማየት እንሞክር፡፡ የእውቀት ሰዎች(ግኖስቲኮች) በነበሩበት ጊዜ ቤተ ክርስቲያን ሳይሆኑ ቤተ ክርስቲያን ብለው ስያሜ በመስጠት ብዙዎችን ያስቱ ነበር፡፡ የጌታችንን የሐዋርያትንን ትምህርት ሳይቀበሉ ሲፈልጉ እየጎረዶና እያጣመሙ በቤተ ክርስቲያኒቱ ስም መጠቀማቸው ለክርስትና ከባድ ፈተና ስለነበር በዚህ ምክንያት ሐዋርያዊት የሚለውን መለያ(መታወቂያ) ተጠቅመዋል፡፡ለዚህም ነው አበው በጉባኤ ‹‹ሐዋርያት በሰሯት(በሰበሰቧት) በአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እናምናለን›› ያሉትሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያን ለመባል መሥፈርቱ ምንድን ነው?
አንድን ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊት ለማለታችን መስፈርታችን ሦስት ነው፡፡
• ከሐዋርያት ሲወርድ ሲዋረድ ሳይቆረጥ ለዚህ ትውልድ ደረሰ ሥልጣነ ክህነት
• የሐዋርያትን እምነት መያዝ
• መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያንን ሲጠበቅ
እነዚህ ሦስት መሠረታዊ ነጥቦች አንዲት ቤተ ክርስተያንን ሐዋርያዊት ለማለት መሥፈርቶች ናቸው፡፡ በዝርዝር ለመመልከት ያክል
1. ከሐዋርያት ሲወርድ ሲዋረድ ሳይቆረጥ ለዚህ ትውልድ ደረሰ ሥልጣነ ክህነት
ሐዋርያት ቤተ ክርስቲያንን የመምራትና የማስተዳደር አማኞችን ከእግዚአብሔር መንገድ እንዳይርቁ የመጠበቅ ከእግዚአብሔር ጋር የማስታረቅ የመፍታትና የማሰር ሥልጣምን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰጥቷቸዋል፡፡ አንድ ቤተ ክርስቲያንም ሐዋርያዊ ለመባል ይህ ሲወርድ ሲዋረድ ከሐዋርያት ዘመን ጀምሮ የነበረ ሥልጣነ ክህነት ዛሬም በቤተ ነክርስቲያኒቱ ሲሰራ ነው፡፡ ሥልጣነ ክህነቱ መኖሩ ብቻ ሳይሆን ያ ሥልጣን ከሐዋርያት ዘመን ጀምሮ በቅብብሎሽ እኛ ጋር የደረሰ መሆኑንን ማረጋገጥ መቻል አለብን፡፡
አንዳንድ ሰዎች ምሥጢረ ክህነትን ከመዋቅራዊ ሥልጣን ጋር ብቻ ያያይዙታል፡፡ ይህ የተሳሳተ አረዳድ ነው፡፡ በቤተ ክርስቲያን እያንዳንዱ የክህነት ሥልጣን ከክህነት አገልግሎት ጋር(ከምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን ጋር) የተያያዘ ነው፡፡ ይህም የሐዋርያት ትውፊት ነው፡፡
2. የሐዋርያትን እምነት መያዝ
ሐዋርያት ከሚያስተምሩት ውጭ ሌላ ትምህርት እያስተማሩና የሐዋርያትን ሐሳብ በራሳቸው መረዳት እየተረጎሙ ሐዋርያዊ መባል አይገባም፡፡ ሐዋርያዊ ለመባል በቅድሚያ የሐዋርያትን ትምህርት መመርመር ያሻል፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ትምህርቷ ከሐዋርያት ጋር የሚቃረን ሳይሆን የሚስማማና የሚጣጣም ነው፡፡ ቀደም ሲልም እንዳየነው ‹‹አንተ የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ ነህ›› በሚለው የቅዱስ ጴጥሮስ ቃል ላይ የተመሠረተች ናት፡፡ ከዚህ ውጭ ሌላ ጨምራም ጎርዳም አታውቅም ስለዚህም ሐዋርያዊት እንላታለን፡፡3. ሱታፌ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት ላይ ሲኖር
ቤተ ክርስቲያን የጸጋው ግምዣ ቤት ናት፡፡ መንፈስ ቅዱስ ከሐዋርያት ዘመን እስካሁን ድረስ በቤተ ክርስቲያን ላይ ይሰራል፡፡ በቤተ ክርስቲያናችን ማንኛውም አገልግሎት ያለ መንፈስ ቅዱስ አጋዥነት አይከወንም፡፡ ሰው ከእግዚአብሔር የሚወለደው(ልጅነት የሚያገኘው) ምሥጢራትን የሚካፈለው መንፈሳዊ ሥራዎችን የሚሰራው በመንፈስ ቅዱስ አጋዥነት ነው፡፡ ስለዚህም ዛሬም መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያኒቱን እንዲመራት እንደሚጠብቃት በያንዳንዱ አገልግሎት ሱታፌ እንዳለው እናውቃለን፡፡ ይህንን የመንፈስ ቅዱስ ሥጦታና ጸጋ ሳይዙ ሐዋርያዊ መባል እንደማይገባም ቤተ ክርስቲያን ታስተምራለች፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
No comments:
Post a Comment