Thursday, 15 June 2017

የቅዱሳን ሕይወት ከሞት በኋላና አማልጅነት ክፍል ሁለት



    የቅዱሳን አማላጅነት በአጸደ ሥጋ -


ቅዱሳን በሕይወተ ሥጋ ሳሉ እንደሚያማልዱና እግዚአብሄርም ስለእነርሱ ምህረትንና ይቅርታን እንደሚያደርግ ቅዱሳን መጻህፍ ይናገራሉ፡፡‹‹እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል ወይን በዘለላው በተገኘ ጊዜ በረከት በእርስዋ ላይ አለና አታጥፋት እንደሚባለው ሁሉን እንዳላጠፋ ስለባሪያዎቼ እንዲሁ አደርጋለሁ፡፡››( ኢሳ658) ስለወዳጆቹ ሲል እንደሚምር ራሱ እግዚአብሔር ምሳሌውን ከነትርጉሙ አስረድቶናል፡፡ ከወይን ዛፍ ዘለላ ፍሬ በተገኘ ጊዜ ሊቆረጥ የነበረው ዛፍ ስለፍሬው ሲባል ይቆይ ተብሎ ከጥፋት እንደሚድን ሁሉ ቅዱሳን ያሉበትን ሕዝብና ሀገርም እግዚአብሔር ስለእነርሱ ሲል ከጥፋት ይታገሳል፡፡ የሚከተሉትም ይህን የሚያስረዱ ናቸው፡፡
 አጸያፊና የረከሰ ነገር በመስራት ያሳዘኑትን የሰዶምና የገሞራን ሕዝብ ሊያጠፋቸው እንደሆነ እግዚአብሔር ለአብርሃም ገለጸለት፡፡ ‹‹እኔ የማደርገውን ከአብርሃም እሰውራለሁን›› አብርሃምም ይምራቸው ዘንድ ደጋግሞ እግዚአብሔርን ለመነ፡፡‹‹በውኑ ጻድቁን ከኃጥኡ ጋር ታጠፋለህን ሃምሳ ጻድቃን በከተማይቱ ውስጥ ቢገኙ በውኑ ሁሉን ታጠፋለህን ከተማይቱንስ በእርስዋ ስለሚገኙ ሃምሳ ጻድቃን አትምርምን›› በማለት እግዚአብሔርን በጸሎት ጠየቀ ፡፡እግዚአብሔርም ‹‹በሰዶም በከተማይቱ ውስጥ አምሳ ጻድቃን ባገኝ ስፍራውን ሁሉ ስለ እነርሱ እምራለሁ፡፡›› በማለት ለአብርሃም መለሰለት አብርሃምም ደግሞ ‹‹ከአምሳው ጻድቃን አምስት ቢጐድሉ ከተማይቱን ሁሉ በአምስቱ ምክንያት ታጠፋለህን?›› አለው፡፡ እግዚአብሔርም ‹‹ከዚያ አርባ አምስት ባገኝ አላጠፋትም አለ። ›› አብርሃምም ደግሞ ‹‹ምናልባት ከዚያ አርባ ቢገኙሳ?››ብሎ ጠየቀ፡፡ እግዚአብሔርም ‹‹ለአርባው ስል አላደርገውም›› አለው። አብርሃምም ‹‹ከዚያ ሠላሳ ቢገኙሳ?›› አለ። እግዚአብሔርም ‹‹ከዚያ ሰላሳ ባገኝ አላጠፋም አለ።›› አብርሃምም ‹‹ከዚያ ሀያ ቢገኙሳ?›› በማለት ለአራተኛጊዜ አብርሃም ማማለዱን ቀጠለ። እግዚአብሔርም ‹‹ከዚያ ሀያ ቢገኙ ስለ ሀያው አላደርገውም›› በማለት ለወዳጁ ለአብርሃም መለሰለት አብርሃምም ለመጨረሻ ጊዜ ስለ ሰዶም ይለምን ጀመር ‹‹ከዚያ አሥር ቢገኙሳ?›› በማለት ጠየቀ። እግዚአብሔርም ‹‹ስለ አሥሩ አላጠፋትም›› በማለት የአብርሃምን ጸሎት ተቀበለ፡፡ በሰዶም ግን ከአራት ሰው በቀር ጻድቅ አልተገኘም፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔር ከተማይቱንና ሕዝቦችዋን አጠፋ፡፡(ዘፍ181723)
 እስራኤላውያን አሮንን ፊት ፊታችን እየሄዱ ጠላትን የሚያጠፉልን ጣዖታት ስራልን ብለው ለጣዖቱ ሰገዱ፡፡ ሙሴም ከደብረሲና አስርቱ ቃላት የተጻፉበትን ጽላት ይዞ ሲወርድ አምልኮ ጣዖት ጀምረው ስለነበር እግዚአብሔር ተቆጥቶ ‹‹ቍጣዬ እንዲቃጠልባቸው እንዳጠፋቸውም ተወኝ አንተንም ለታላቅ ሕዝብ አደርግሃለሁ፡፡›› አለው፡፡ ሙሴም ‹‹በእግዚአብሔር በአምላኩ ፊት ጸለየ፥ አለም……. ከመዓትህ ተመለስ፥ ለሕዝብህም በክፋታቸው ላይ ራራ።›› እግዚአብሔርም ‹‹በሕዝቡ ላይ ሊያደርግ ስላሰበው ክፋት ራራ።›› (ዘጸ32714)

 ሙሴም ይህን ሲገልጽ ‹‹ስለ ሠራችሁት ኃጢአት ሁሉ እርሱንም ለማስቈጣት በእግዚአብሔር ፊት ክፉ የሆነውን ነገር ስላደረጋችሁ እግዚአብሔር ሊያጠፋችሁ ከተቈጣባችሁ ከቍጣውና ከመዓቱ የተነሣ ስለ ፈራሁ እንደ ፊተኛው በእግዚአብሔር ፊት አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ወደቅሁ እንጀራ አልበላሁም፡፡ውኃም አልጠጣሁም። እግዚአብሔርም በዚያን ጊዜ ደግሞ ሰማኝ።››( ዘዳ91819) ጻድቁ ቅዱስ ዳዊት በመዝሙሩ ‹‹እንዳያጠፋቸው ቍጣውን ይመልስ ዘንድ የተመረጠው ሙሴ በመቅሠፍት ጊዜ በፊቱ ባይቆም ኖሮ ያጠፋቸው ዘንድ ተናገረ።›› (መዝ10523) ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት እንè የሙሴን አማላጅነት መሰከረ  ‹‹በፊቱ ባይቆም ኖሮ ያጠፋቸው ዘንድ ተናገረ።›› ማለቱ ሙሴ በአማላጅነቱ ባይኖር ያጠፋቸው እንደነበር ሲገልጽ ነው፡፡
እስራኤላውያን በኃጢያታቸው መከራ በከበባቸው ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ በአንድነት ተሰብስበው ነቢዩ ኤርሚያስን እንዲህ አሉት ፡፡‹‹ዓይኖችህ እንዳዩን ከብዙ ጥቂት ቀርተናልና ልመናችን  እባክህ  በፊትህ ትድረስ አምላክህም እግዚአብሔር የምንሄድበትን መንገድና የምናደርገውን ነገር ያሳየን ዘንድ ስለ እኛ ስለዚህ ቅሬታ ሁሉ ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ጸልይ፡፡›› ነቢዩ ኤርሚያስም ‹‹እነሆ  እንደ ቃላችሁ ወደ አምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር እጸልያለሁ፡፡›› አላቸው፡፡ 10 ቀን ከጸለየላቸው በኃላ እግዚአብሔር ጸሎቱን ሰምቶ ‹‹ስላደረግሁባችሁ ክፉ ነገር ተጸጽቻለሁና በዚህች ምድር ብትቀመጡ እሠራችኋለሁ፡፡እንጂ አላፈርሳችሁም፡፡እተክላችኋለሁ እንጂ አልነቅላችሁም። ከምትፈሩት ከባቢሎን ንጉሥ አትፍሩ አድናችሁ ዘንድ ከእጁም አስጥላችሁ ዘንድ እኔ ከእናንተ ጋር ነኝና አትፍሩ  ይላል እግዚአብሔር››( ኤር42211)
ኢዮርብዓም የተባለው የእስራኤል ንጉሥ ጣዖት በማምለኩ ይገስጸውና ይመክረው ዘንድ የተላከው ነቢይ በትዕቢት ለመያዝ የተዘረጋው እጁ ስለደረቀ ጨነቀውና መልሶ ያን የእግዚአብሔር ነቢይ ‹‹አሁን የአምላክህን የእግዚአብሔርን ፊት ለምን እጄም ወደ እኔ ትመለስ ዘንድ ስለ እኔ ጸልይ›› አለው፡፡ ያም ነቢይ እግዚአብሔርን ለመነ የንጉሱም እጅ እንደቀድሞ ሆነች፡፡ (1ነገ1310)
ሌሎች ማስረጃዎች፡
የአብርሃም አማላጅነት፡ -በአቤሜሌክ ምግባረ ደካማነት እግዚአብሔር ሲቆጣ  ደንግጦ የእግዚአብሔርን ገጸምሕረት መፈለጉና በቅዱሳን ጸሎት መረዳቱና መጠቀሙ፡፡( ዘፍ207)
የኢዮብ አማላጅነት፡-ልዩ ልዩ ፈተና ደርሶበት በሕመም ሲሰቃይ እሱ አምላኩን ሳያማር የማይገባ ቃል አምላክን  የማይገባ ቃል የተናገሩት ስቱ ደኞቹ  የእግዚአብሔር ቁጣ እንደነደደባቸው  ኢዮብ ወደእግዚአብሔር ጸለዮ ምሕረት እንዳገኙ፡፡ ( ኢዮ42711 )
   የሙሴ አማላጅነትና የፈርዖን ልመና፡፡ ( ዘጸ 8615 )               

No comments:

Post a Comment