ልዩንዐሥረኛ(1513-1521) የተባለው ፖፕ በሮም ከተማ ለሚገኘው ለታልቁ የቅዱስ
ጴጥሮስ ቤተክርስቲያን የእድሳት ሥራ ማስፈጸምያ የሚሆን ገንዘብ ስለፈለገ በጀርመን የመንዝ ሊቀጳጳስ አልበርት ቀደም ሲል ሦስት
ሀገረ ስብከቶች ላይ ሲሾም ሹመቱን ላሰጠው ለሮም ፖፕ በግብርና በገጸ በረከት መልክ አውግስበርግ ከነበረው ፉገር ከተባለው ድርጅት
ገንዘብ በአራጣ ተበድሮ ነበር፡፡ ስለዚህም ለእዳው የሚከፍለው ገንዘብ ስላስፈለጋው ዮሐንስ ቴትዝል የዶሚኒካም መነኩሴ‹‹ኢንደልጀንስ››
የተባለውን የኃጢያት ማስተሰርያ ጽሑፍ በመሸጥ ለእዳው ክፍያ ከምእመናን እንዲከፈል አዘዘ፡፡
ኢንድጅንስ ምንድር ነው?
ኢንድጅንስ ከፖፑ የተላከ
ኃጢያት ማስተሰርያ ጽሑፍ በመግዛት ዋጋውን በሙዳይ ምጽዋት ውስጥ ስትጥሉ የሞተ(የሞተች) ዘመዳችሁ የተኮነነች ነፍስ
በቅስበት ከፐርጋቶሪ(ከመካነ ንስሐ) ነጻ ሆና ወደ መንግስተ ሰማያት ትገባለች፡፡ የራሳቸሁም ነፍስ ትማራለች ብሎ
በመስበክ የዋሐን ክርስቲያኖችን ያታልል ነበር፡፡
ፐርጋቶሪ(መካነ ንስሐ) ምንድር ነው?
ይህ መካነ ንስሐ የሙታን መቆያ
ሲሆን እንደካቶሊክ ትምህርት ይህ ቦታ መቆያ ሆኖ የሙታኑ ዘመዶች ወዳጆች በሚገዙት የኃጢያት ማስተስርያ ሰርተፍኬት
ከነበሩበት መቆያ ወደ መንግስተ ሰማያት ይገባሉ የሚል ትምህርት ነው፡፡
ይህ የካቶሊካዊያን ትምህርት
በኃላ ለተነሱ የፕሮቴስታንት ተሐድሶያዊያን መነሻና የምዕራብ ቤተ ክርስቲያን ለሁለት መከፈል ምክንያትና ምንጭ
ሆኖል፡፡ የተሐድሶያዊየኑ መሠረት ይህ ይሁን እንጂ ይህን ትምህርት በመጥላትና በመጸየፍ ምክንያት ሌሎች ተጨማሪ
የማይገቡ ትምህርቶችን በማምጣት ብዙዎችን አስቷል፡፡
ፐሪጋቶሪ (purgatory) የሚለው ቃል <<putgare>> ከሚለው የላቲን ቃል የመጣ
ሲሆን ትርጉሙም ማጽዳት(ማንጻት) ማለት ነው፡፡ ይህ እንደሮም ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ ጊዜያዊ ቅጣት መቀበያ ቦታ
ነው፡፡ የመካነ ደይን ጽንሰ ሐሳብ የተጀመረው እ.ኤ.አ. በ1215 በላተርን በ1274 በሊዮን 1431 በፍሎሬንስ
በ1554-1563 ደግሞ በትሬንት በተደረጉ የካቶሊክ ጉባኤያት ነው፡፡ በአጠቃላይ ከ13 መቶክፍለ ዘመን እስከ 15
መቶ ክፍለ ዘመን ድረስ ተፈጻሚ የሆነ አስተምህሮ ነው፡፡
የሮም ካቶሊክ እምነት
የሮም ካቶሊካዊያን ኃጢአት
በእግዚአብሔር ፊት እኩል እንዳልሆነና በየዕለቱ ሰው በድካሙ የሚሠራቸው ኃጢአቶች ሀሉ የእግዚአብሔርን ጽኑ ትእዛዝ
የሚጥሱ እንደሚቀጡበት ያለ ብርቱ ቅጣት አያጋጥመውም በማለት ያምናሉ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ..‹‹ ዓይኖችህ ክፉ እንዳያዩ ንጹሐን ናቸው.››(ዕንባ. 1፥13) በሚለው ጽኑ ሐሳብ ምክንያት ወደ እርሱ የሚቀርብ ሁሉ ፍጽም ይሆናል የሚል አመለካከት አላቸው፡፡
በዚህ አስተምህሮ መሠረት ለሙታን ሦስት ስፍራ እንዳላቸው ያስቀምጣሉ
1. የቅዱሳን ሥፍራ ይህ ቦታ በምድር ላይ በቅድስና ለሚኖሩ ሰዎች የተሰናዳ ነው ስለዚህም በቀጥታ እነዚህ ነፍሳት ወደ ብሔረ ብፁአን ይገባሉ
2. በሞት ኃጢአት(moral sin) ወይም በጥንተ አብሶ ኃጢአት እንደተያዙ የሞቱ ነፍሳት ወደ ዘለዓለማዊ ቅጣት ይገባሉ
3. ከተጠመቁ በኋላ የበደሉ
በእውነት ንስሐ የገቡ ኃጢአታቸውን የተናዘዙ ነገር ግን ይቅርታን የሚያስገኝ የንስሐ ፍሬ ያላፈሩ ነፍሳት ወደ
በመካነ ደይን ቆይተው እንደኃጢአታቸው ደረጃ በፍጥነት ወይም ዘግይተው በመንጽሔ እሳት (purgatorial fire) ይነጻሉ፡፡ ከዚያም ወደ ብፁአን ዓለም ይገባሉ፡፡ይህም የሚሆነው በምጽአት በጸሎተ ፍትሐት በስሙ በሚፈጸም መላካም ሥራ መሆኑን ያስተምራሉ
የትሬንት ጉባኤም ኃጢአት
ከወንጀል ጋር ያለ ከሆነ እግዚአብሔር ሁሉ ነጻ አያደርግም ይላል፡፡ እግዚአብሔር አጥጋቢ(አርኪ) ነገርን ይፈልጋል
ኃጢአትንም ይቀጣል፡፡ስለዚህ በዚህ የሃይማኖት ትምህርት በዚህ ዓለም ሕይወቱ ለተቀበለው ቀኖና(ለንስሐ የሚሆን
ቅጣት) የሌላውም ዓለም ደግሞ ቅጣት መቀበሉ ግድ የሚያስፈልግ እንደሆነ የሚታመንበት ነው ይላሉ፡፡ ከዚህም በኋላ
ከእግዚአብሔር ተለይቶ ለዘለዓለም የማይጣል ይሆናል፡፡
በመንጽሔ እሳት (purgatorial fire) ምንድን ነው
እውነተኛ የፍርድ እሳት እንዳለ
በሁሉም ክርስቲያኖች ዘንድ የሚታመን ነው፡፡ ነፍስ ከእግዚአብሔር ከመለየቷ በተጨማሪ ያጠፍች ነፍስ በዘለዓለም
እሳት ትቀጣለች፡፡ ከዚህ ዓለም በኋላ ጉድለታቸው በመንጽሔ እሳት የሚያካከክሱ ነፍሳት ስቃይ ከዚህ ይልቅ የበለጠ
የማይታገሱት(የማይቻል) ነው፡፡ የመንጽሔ እሳት ቅጣት ጊዜያዊና የሚያበቃ ነው፡፡ ሁሉም ግን ከመጨረሻው ፍርድ ቀን
በፊት የሚሆኑ ናቸው፡፡
በዚህ ዓለም ያሉ አማኞች
በመካነ ደይን ላሉ ነፍሳት ስለ እነርሱ መሥዋዕትና ጸሎት ያቀርቡላቸዋል፡፡ እግዚአብሔር በደላቸውን ሁሉ ይቀር
ያላቸዋል በአብርሃም እቅፍ ይቀበላቸው ዘንድ ለዘለዓለማዊ ደስታ ያልበቁ ነገር ግን ጸሎትና ቁርባን የቀረበላቸው
እነዚህ ነፍሳት ግን ወደ መካነ ደይን ገብተው ለአጭር ጊዜ ብቻ ከእግዚአብሔር እይታ ይሰወራሉ፡፡
ካቶሊኮች ለዚህ ትምህርት የሚያቀርቡት የመጽሐፍ ቅዱስ ማስረጃ
‹‹ማንም ሥራ የተቃጠለበት ቢሆን ይጎዳባታል እርሱ ራሱ ግን ይድናል ነገር ግን በእሳት እንደሚድን ይሆናል፡፡››
(አንደኛ ቆሮ 3፥15)
በእርግጥ ቅዱስ ጳውሎስ ይህንን
ቃል የተናገረው ስለቅጣትና ስለፍርድ ሳይሆን ስለአገልግሎትና አገልጋዮች ባስተማረ(በተናገረ) ጊዜ ነው፡፡
የእርሱንና አጵሎስን አገልግሎት ከእርሻና ከግንበኛነት ጋር እያስተያየ ይናገር ነበርና፡፡ (1ኛ ቆሮ 3፥12-15)
እሳቱም ለሥራው እንጂ ለሠራተኛው አይደለም፡፡ በዚህ ክፍለ ንባብ የተገለጸው ቅጣት ለእያንዳንዱ ሰው መሆኑን
አስተውል፡፡መካነ ደይን ግን ለተወሰኑ ሰዎች ነው፡፡
እሳቱ ለመፈተኛ እንጂ
እንደመካነ ደይን ለቅጣትና ለመከራ እንደሆነ አስተውል፡፡ እሳቱ በገለባ በእንጨት ወይም በሣር የተሠራውን
ያቃጥላል፡፡ በመካነ ደይን አለ የሚባለው መንጽሔ እሳት ግን አንድን ሰው ንጹሕ የሚያደርገው እና ወደ ተሻለ ቦታ
የሚገባበት ነው ይባለል፡፡ ስለዚህ አብሮ ሊሔድ አይችልም፡፡
‹‹እግዚአብሔርም ሰይጣንን ሰይጣን ሆይ እግዚአብሔር ይገሥጽህ ኢየሩሳሌምን የመረጠ እግዚአብሔር ይገሥጽህ በውኑ ይህ በእሳት የተጠበቀ ትንታግ አይደለምን? አይደለምን›› (ትን. ዘካ. 3፥2)
በዚህ የመጽሐፍ ክፍል የተጠቀሰው ቃል ከመንጽሔ እሳት አስተምህሮ ጋር የተገናኘ አይደለም፡፡ ኢያሱ በምድር ላይ
‹ዳነ›› የሚለው ቃል ባግባቡ ባለማገልገሉ የሚጸጸትና ንስሐ የሚገባ ከሆነ የሚያገኘውን እድል የሚያመለክት ነው፡፡
‹‹በሰው ልጅ ላይ ቃል የሚናገር ሁሉ ይሠረይለታል በመንፈስ ቅዱስ ላይ ግን የሚናገር ሁሉ በዚህ ዓለም ቢሆን ወይም በሚመጣው አይሠረይለትም››(ማቴ 12፥32)
የካቶሊክ ሊቃውንት ‹‹በሚመጣው›› የሚለውን ቃል መካነ ደይን ስለሚፈጻመው ይቅርታ እንደሆነ ያስተምራሉ፡፡ ነገር ግን ጌታችን በሚመጣውም ብሎ የገለጠው ጊዜን ሳይሆን ቦታን የሚገልጽ ነው፡፡
ይኸውም በሚመጣው ዓለም በሚለው ይታወቃል፡፡ ጌታችን በዚህ ዘመን ስለሚፈጸመው ይቅርታ ሲናገር‹‹እውነት እላችኋለሁ በምድር የምታስሩት ሁሉ በሰማይ የታሰረ ይሁን በምድር የምትፈቱት በሰማይ የተፈጠ ይሆናል፡፡›› (ማቴ 18፥18) ስለዚህ በሚመጣው ዘመን
የሚሆነው ይቅርታ ማለት ንስሐ ሊገባ ነገር ግን ከንስሐ አባቱ በርቀት ተለይቶ ሳለ ወይም በድንገት ከዚህ ዓለም
በ፣ሞት በመለየቱ ምክንያት ኃጢአቱን ለመናዘዝ ከምድርም ላይ በሕይወት ሳለ ፍትሐትን ለመቀበል ላልቻለ የእርሱ ትልቅ
ምሕረት(ርኅራኄ) የአንድን ሰው ንስሐ(ጸጸት) ወደ ቅጣት(መካነ ደይን) ሳይገባ ወይም መካን ሳያደርስበት
እንዲቀበለው ያደርጋል ይቅርታና መከራ አብረው አይሄዱምና፡፡
የፐሪጋቶሪ መኖር ትምህርት ስሕተት የሆነበት ምክንያት
1. ከነገረ ድኅነት ትምህርት ጋር ይቃረናል
ቤዛነት የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሆኖ ሳለ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ቤዛነት የሚገኘው በመካነ ደይን ቦታ መሆኑ ከቤዛነትና ከሣ ትምህርት ጋር ይቃረናል(ሮሜ. 3፥24 1ኛ ዮሐ 2፥1 1ኛ ዮሐ 4፥10)
2. ከሥርየተ ኃጢአት ትምህርት ጋር ይቃረናል
ሥርየተ ኃጢአት የሚገኘው
በእግዚአብሔር ፀጋ ሰው ንስሐ ገብቶና ተጸጽቶ ሲገኝ ነው፡፡ በትምህርተ ፐሪጋቶሪ ግን ኃጢአትን በመክፈል የሞት
ኃጢአት ይቅርታን ሊያስገኝ የሚችል በማለት ንስሐ ሳይገቡ ይጸድቃሉ ማለት ከመሠረታዊው የአባቶች ትምህርት ለመዳን
ኃጢአትን መናዘዝ ጌታ እንዳለው በብርሃን መመላለስ እንደሚገባ አለማስተዋል ነው፡፡(1ኛ ዮሐ 1፥7) ይህም ከሥርየተ
ኃጢያት ትምህርት ጋር ይቃረናል፡፡
3. ከምሥጢረ ንስሐ ጋር ይቃረናል
ንስሐ ኃጢያትን ያስተሰርያል ዳግመኛም ንስሐ በገባንበት ኃጢአት አያስጠይቅም፡፡ ይህ መሠረታዊ የምሥጢረ ንስሐ ትምህርት ነው የመጽሐፍ ቅዱስም ሐሳብ ነው፡፡(ቆላ.2፥13 ኢሳ 43፥25)
ይህ ትምህርት ምንም እንኳን መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት ባይኖረውም ይህንን በሚመለከት የካቶሊክ የነገረ መለኮት ሊቃውንቱ ጥቅስ አላጡም ፡፡ በአንደኛ ቆሮንቶስ 3፡10-15 በእሳት ስለሚገለጥ ያ ቀን ይፈርዳልና የሚለውን በመጥቀስ ቀጥታ ባይገናኝም ስለ መካነ ንስሐ ይሰብካሉ፡፡
ወስብሐት እግዚአብሔር
No comments:
Post a Comment