ሕይወት ከሞት በኋላ
ኦርቶዶክሳዊትቤተ ክርስቲያን እምነት መሠረት በሰዎችናበእግዚአብሔር
መካከል የማይቋረጥ ግንኙነት ግንኙነት እንዳለ ታስተምራለች፡፡ ይህም የሰው ልጅ በምድራዊ ሕይወቱ እንዲሁም ከዚህ ዓለም ከተለየም
በኋላ የሚቀበሉ ናቸው፡፡ በዚህ ዓለም ሳሉ ከእግዚአብሔር ጋር እንደሚገናኙ ሁሉ ከዚህ ዓለም ከተለዩም በኋላ ከእግዚአብሔርና በምድር
ካሉ ሰዎች ጋር ግንኙነትና ሕብረት አላቸው፡፡ ከጥንት ጀምሮ ይህ አመለካከትና አስተሳሰብ የነበረ ሲሆን በአሥራ ሥድስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተነሳው የተሐድሶ አቀንቃኙ ማርቲን ሉተር ይህንን ድርጊት በማውገዝ
ቀድሞ ሲደረግ የነበረውን እምነትና አስተሳሰብ ተቃወመ፡፡
ቤተ ክርስቲያን ቀደም ሲልም እንደገለጽነው በአካለ ሥጋ ያሉ በአካለ ሥጋ የሌሉ
ሰዎች መላእክት ቅዱሳን ሁሉም በሕብረትና በአንድነት እግዚአብሔርን የምናከብርባትና የምናመሰግንባት የምስጋና ግምጃ ቤት ናት፡፡
ይህንም የቤተ ክርስቲያን አንድነት የተገለጠና በተግባርም የምንሳተፍበት የጋራ ጸሎትና ሥርዓተ አምልኮ ነው፡፡ ይህም ጸሎተ ቅዳሴው
መስተብቁዕ ሊጦኑ ማኅሌቱ ጸሎተ ፍትሐቱና የመሳሰለው ነው፡፡ ጸሎተ ቅዳሴው የሁሉም ርዕሰ ጸሎት ነው፡፡ በጸሎትና በአምልኮውም ቅዱሳን
መላእክት የቀደሙት አበው ሊቃውንት ነቢያት ሐዋርያት ጻድቃን ሰማዕታት ሁሉም ይሳተፋሉ የጊዜና የቦታ ልዩነት አጥፍተው በሕብረት
ከእኛ ጋር ይሆናሉ፡፡ ጸሎተ ቅዳሴው ጸሎተ ቁርባን የሚባለውም በዚህ ምክንያት ነው ቁርባን አማካኝነት ሁላችን አንድ እንሆናለንና፡፡
ቅዱስ ጳውሎስም እንዳለው ለእግዚአብሔር ማደርያ ለመሆን በመንፈስ አብራችሁ ትሠራላችሁ ኤፌ 2፥21-22
በፕሮቴስታቱ ዓለም ግን ከዚህ በተለየ ይህንን አያምኑም ይህንንም አጥብቀው
ይቃወማሉ፡፡ በሥጋ ከእኛ የተለዩ ሰዎች ፈጽመው የተለዩ ናቸው ብለው ያምናሉ፡፡ ለዚህም የሚያቀርቡት መጽሐፍ ቅዱሳዊ መነሻና ጥቅስ
መዝ 115፥17‹‹ አቤቱ ሙታን የሚያመሰግኑ አይደሉም ወደ ሲኦል የሚወርዱ ሁሉ›› የሚለውን ነው፡፡ ይህ ጥቅስ አመልካችነቱ ለምድራዊው
ሞት አይደለም ሞተ ልቡና(መንፈሳዊ ሞትን) የሚያመለክት እንጂ ስለዚህም ለእነርሱ አመለካከትና እምነት የሚስማማ ጥቅስ አይደለም፡፡
አማላጅነት በመጽሐፍ ቅዱስ
ምልጃ የእግዚአብሔር ፈቃድና ትዕዛዝ እንጂ በሰው ፈቃድ የተጀመረ አይደለም፡፡ ምልጃ የታዘዘውና ያስፈለገው እግዚአብሔር ከኃጥአን ይልቅ የጻድቃንን ጸሎት የበለጠ ስለሚሰማ ነው፡፡
o ለምሳሌ፡ አብርሃም ወደ ጌራራ ተሰዶ ሳለ የሀገሪቱ ንጉሥ አቤሜሌክ የአብርሃም ሚስት ሳራን ወሰዳት እግዚአብሔርም በሳራ ምክንያት የአቤሜሌክን ቤት ማህፀኖችን ሁሉ ዘጋ፡፡ እግዚአብሔርም አቤሜሌክን በሕልም እንዲመልሳት ከነገረው በኃላ ‹‹ነቢይ ነውና ስለአንተ ይጸልያል ትድናለህም፡፡›› (ዘፍ20፡7 )በማለት የአብርሃምን ጸሎት እንደሚቀበል ነግሮታል፡፡ እግዚአብሔር አንተ ጸልይ ይቅር እልሃለሁ አላለውም ስለአንተ ይጸልይ አለው እንጂ፡፡ ስለዚህ ይህ ምልጃን እግዚአብሔር እንደፈቀደውና የቅዱሳንን ጸሎት ከሁሉ በበለጠ መቀበሉን ያሳየናል፡፡‹‹አብርሃምም ወደ እግዚአብሔር ጸለየ እግዚአብሔርም አቤሜሌክን ሚስቱንም ባሪያዎቹንም ፈወሳቸው እነርሱም ወለዱ›› (ዘፍ20፡17) ‹‹የእግዚአብሔር ዐይኖች ወደ ጻድቃን ጆሮዎቹም ወደ ጩኧታቸው ናቸውና፡፡››(መዝ33፡15 )
ሌላ ማስረጃ፡- ( ኢዮ42፡7‐9)፣ ( ያዕ5፡16)፣ ( ምሳ15፡8፣ 15፡29) ቅዱሳን ሕይወታቸው ሐሳባቸውና ልመናቸው ሁሉ እንደ እግዚአብሔር ፍቃድ ስለሆነ ጸሎታቸውና ልመናቸው በአምላክ ዘንድ የተወደደ ነው፡፡ ‹‹የጻድቃን ምኞት በጎ ብቻ ነው፡፡›› (ምሳ11፡23)
ምልጃ እግዚአብሔር ያሳየው መንገድ ነው፡፡ ስለሆነም ምግባራቸው የደከመ ጸሎታቸው እንደርሱ ፍቃድ ያልሆነ ኃጥአን የእርሱን ፍቃድ በሚያውቁና በሚፈጽሙ በምግባር በትሩፋት በበለጸጉ ጻድቃን እንዲረዱ ማድረግ የቸርነቱ መገለጫ ነው፡፡
ምልጃ የእግዚአብሔርን ፈታሒነት ወይም ፈራጅነት የሚጋፋ ሳይሆን ቸርነቱን የሚገልጽ ነው፡፡ ሁሉም እንደ ወዳጆቹ እንደ ጻድቃን ካልሆነ ሳይል ኃጥአን በጻድቃን ጸሎት እንዲጠቀሙ አደረገ፡፡ ‹‹በእኛ የማስታረቅ ቃል አኖረ እንግዲህ እግዚአብሔር እንደሚማለድ የክርስቶስ መልዕክተኞች ነን፡፡›› (2ቆሮ5፡19‐20)
No comments:
Post a Comment