Saturday, 24 June 2017

‹‹ሚድያና የክርስትና ሕይወት በትውልዱ መካከል›› ክፍል አንድ


                                                                                                                                   በዳዊት ደስታ
                                                                                                              dawitdesta126@gmail.com

መግቢያ


21ኛው .. መገባደጃ አንስቶ ባሉት ጥቂት አስርት አመታት የአለምን ምስል ፈጽመው የለወጡ ሁለት አስደናቂና ቅጽበታዊ የሆኑ ለውጦች በተመሳሳይ ጊዜ ተከስተዋል፤ አንደኛው ለውጥ ለማመን በሚያዳግት ሁኔታ የሰውልጅ ያስመዘገበው ‹‹የቴክኖሎጂ›› ምጥቀት ሲሆን፤ ሌላኛው ደግሞ በአለም አቀፍ ደረጃ በስነምግባር፣ በሃይማኖትና በሰብአዊ እሴቶች ዙሪያ እየተስተዋለ የመጣው ሁለንተናዊ ‹‹ዝቅጠት›› ነው፡፡
እነዚህ ሁለት እርስ በርስ ተመጋጋቢ ነገር ግን ፍጹም ተጻራሪ የሆኑ ክስተቶች ያለንበት ትውልድ መገለጫዎች ለመሆን በቅተዋልም ማለት ይቻላል፡፡

እያሳደሩ ያሉት ተጽዕኖዎች


በዘመኑ ትውልድ በተለይም በወጣቱ ማሕበረሰብ ላይ የሚስተዋለው ስርአት አልበኝነት፣ ግለኝነት፣ አመጻና ጠብ፣ከፍተኛ የሱስ ተጠቂነት፣ የግብረሰዶም መስፋፋት፣ ለማሕበረሰባዊና ግለሰባዊ የስነምግባር እሴቶች ደንታ የሌለውለገንዘብ ሕሊናውን የሸጠናለቀኑ ብቻ የሚኖር ሰው ቁጥር መበራከት፣ የውርጃ የፍቺ እንዲሁም የሴትና የወንድ አዳሪነት ቁጥር ማሻቀብወዘተ እኒህ ወገኖች ላለንበት ዝቅጠት እንደ ማስረጃ የሚያቀርቡትን ከጥቂት ማብራርያ ጋር እንመልከታው፡

 ፖርኖግራፊ pornography)ፊልሞች


ፖርኖግራፊ ፊልሞች በሕሊናችን ውስጥ ልክ እንደቆሻሻ መጥቶ ከተዘረገፈ ሕሊናችን አስተሳሰቡ ሁሉ ይበከልና የጤናማ ሃሳብ ችግር እጦት ስቃይ ውስጥ እንድንገባ ያደርጋል።
2014 (..) ትኩረቱን በመላው ዓለም ያደረገ ጥናት በእንግሊዛውያን የጥናት ባለሙያዎች ተደርጎ ነበር፡፡ በርካታ ወንድ እና ሴት በጎ ፈቃደኞችን ያሰባሰበው ፕሮጀክት ‹‹Sex›› የሚለው ቃል በስፋት በኢንተርኔት የሚፈለግ ቃል መሆኑን አረጋግጧል፡፡
የቅርቡ የአሜሪካውያን ጥናት ደግሞ 68 ፐርሰንት የሚሆኑት ጎረምሶች እና 18 ፐርሰንት የሚገመቱት ሴት ኮረዶች በትንሹ በሳምንት አንድ ቀን የኮምፒዩተር መስኮት ላይ የሚገኙት የወሲብ ቪዲዮዎችን እና ምስሎች ለመመልከት እንደሆነ አሳይቷል፡፡
በሚዲያዎች በሚዘወተሩ ዝሙት ቀስቃሽ ትእይንቶች ላይ ያተኮሩ በርካታ ጥናቶች እንደሚጠቁሙት እኒህ አጸያፊ ትእይንቶች በታዳጊዎችና በወጣቶች ብሎም በአጠቃላይ የዘመኑ ትውልድ ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ተጽእኖ በማስከተል ላይ ይገኛሉ፡፡ አስነዋሪ ትእይንቶች በትውልዱ ላይ እያስከተሉት ያለውን ተጽእኖ ካጋለጡ ጥናቶች መካከል የተወሰኑትን እንደ ማስረጃነት ለአብነት እንመልከት፡-
• … የአየር ሰአቱን ከተቆጣጠሩት የቴሌቪዥን ፕሮግራሞች ሁለት ሶስተኛ (64%) የሚሆኑት ለዘብ ያሉ ዝሙት ቀስቃሽ ትዕይንቶች፣አንድ ሶስተኛ (32%) የሚሆኑት ልቅ የፍትወት ተግባራት፤አንድ ሰባተኛ (14%) የሚሆኑት ደግሞ ግልጽ ጾታዊ ተራክቦ ሲፈጸም ይታይባቸዋልከይዘር ፋሚሊ ፋውንዴሽን
• … ከአንድ ሰአት ላነሰ ጊዜ የኤም ቲቪ የሙዚቃ ፕሮግራሞችን እንዲመለከቱ የተደረጉ 7 እና 9 ክፍል ታዳጊዎች፤ ካልተመለከቱት ታዳጊዎች በተለየከትዳር በፊት ጾታዊ ግንኙነት ማድረግ ምንም ችግር የለውምየሚል አመለካከት ለማዳበር ይበቃሉግሪንሰን እና ዊሊያምስ
ካልፊን፣ ካሮልና ሽሚድት ባዘጋጁት ጥናታዊ ሪፖርት በተመሳሳይ አንድ የሙዚቃ ቪዲዮ እንዲመለከቱ የተደረጉ የኮሌጅ ተማሪዎች ካልተመለከቱት በላቀ ሁኔታ ቅድመ- ትዳር ለሚደረግ ጾታዊ ግንኙነት በጎ አመለካከት አንጸባርቀዋል፡፡
ግሪን በርግ የተሰኘ ተመራማሪ እንዲሁ በሁሉም አይነት የቴሌቪዥን ፕሮግራሞች ላይ በአማካይ በሰአት ሶስት ዝሙት ቀስቃሽ ትእይንቶች እንደሚተላለፉ በመረጃ በተደገፈው ጥናቱ ጠቁሟል፡፡ በዚህም መሰረት ሰዎች በአዘቦት ቀናት በአማካይ በቀን አንድ ሰአት በእረፍት ቀናት ደግሞ በአማካይ ለሁለት ሰአታት ቴሌቪዥን ይመለከታሉ በሚል እሳቤ (ይህ ስሌት እንግዲህ በአመዛኙ ቴሌቪዥን የማየት ሱስ ለተጠናወተው የምዕራቡ አለም ተመልካች እጅግ ዝቅተኛ መሆኑን ልብ ይሏል) ያሰላው ግሪን በርግ አንድ ተመልካች በአማካይ በሳምንት 27 ዝሙት ቀስቃሽ ትእይንቶችን በአመት ደግሞ 1400 ትእይንቶችን በትንሹ እንደሚመለከት ዘግቧል፡፡
 
አጸያፊ ምስሎች
እነዚህ አጸያፊ ምስሎች በማስታወቂያዎች፣ በፋሽኖች፣ በፊልሞች፣ በሙዚቃዎች፣ በመጽሔቶች አልፎ ተርፎም በቴሌቪዥን፣ በቪዲዮ ጨዋታዎች፣ በዘመናዊ ሞባይሎች፣ በተንቀሳቃሽ የኤሌክትሮኒክ መሣሪያዎችና በድረ ገጾች፣ አሁን አሁን ደግሞ በኢንተርኔት የፎቶ መለዋወጫዎች ጭምር ሊገኙ ይችላሉ።ተመራማሪዎችና ሐኪሞች፣ የብልግና ምስሎች ከባድ ሱስ የሚያስይዙ በመሆናቸው ኮኬይን ከሚባለው ኃይለኛ ዕፅ ጋር ያመሳስሏቸዋል።
የፖርኖግራፊ ምስሎችን በተመለከተ መረጃ
በየሴኮንዱ፦ ወደ 30,000 የሚጠጉ ሰዎች የፖርኖግራፊ ምስሎችን የያዙ ድረ ገጾች ይመለከታሉ።
በየደቂቃው፦ ኢንተርኔት ተጠቃሚዎች 1.7 ሚሊዮን የሚበልጡ የፖርኖግራፊ መልእክቶችን በኢ-ሜይል ይልካሉ።
በየሰዓቱ፦ በዩናይትድ ስቴትስ ወደ ሁለት የሚሆኑ እጅግ አስጸያፊና ዘግናኝ የፖርኖግራፊ ፊልሞች ይለቀቃሉ።
በየቀኑ፦ በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ብቻ በአማካይ ከሁለት ሚሊዮን የሚበልጡ የፖርኖግራፊ ፊልሞች ይከራያሉ።
በየወሩ፦ በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ 10 ወጣት ወንዶች 9 ገደማ የሚሆኑት፣ 10 ወጣት ሴቶች ደግሞ 3 ገደማ የሚሆኑት የፖርኖግራፊ ምስሎችን ይመለከታሉ።
በየዓመቱ፦ በዓለም አቀፍ ደረጃ የፖርኖግራፊ ምስሎች ኢንዱስትሪ 100 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ገቢ ያስገኛል። (በአዲስ ጉዳይ(ሮዝ) መጽሔት)



 ፊልሞች


ፊልም፦ሊዮድ ኩፍማንፊልም ጥበብ ነው የፊልሙ መንፈስ በሰሪዎቹ አመለካከት ላይ የወደቀ ነው፡፡” (Movies are art and the spirit of the movie depends on the creators) ይላል፡፡ጥናቶች እንደሚጠቁሙት የፊልም ኢንዱስትሪው ዋነኛ ሸማቾች ከሆኑት መካከል በግምባር ቀደምትነት የሚገኙት 12-18 የእድሜ ደረጃ ላይ የሚገኙ ታዳጊ ወጣቶች ናቸው፡፡
ቤተክርስቲያንን የማይወክሉ ፊልሞች መሰራት
• THE ABODE OF GOD በኢትዮጵያ የሚል ስያሜ አለው በፊልም ውስጥ ክርስቶስ እና ይሁዳ ከንፈር ለከንፈር ይሳሳሙበታል ፣እየሱስ ክርስቶስ አልተሰቀለም በእሱ ፋንታ ሌላ መልአክ ነው የተሰቀለው ይላል ፣ክርስትያን ያልሆኑ ተዋናዮች መኖራቸው ታውቋል፡፡
• ‹‹የእግዚአብሔር ቤት››/The abode of God/በሚል ርእስ በጀርመናዊቷ ሚስስ ብሪጅት ማሪያ ማየር ተዘጋጅቶ በተወሰኑ ኢትዮጵያዉያን አርቲስቶች የተሠራው የኢየሱስ ክርስስቶስ የስቅለት ፊልም ከቤተ ክርስቲያን ቀኖና እና ትውፊት ውጭ እንደሆነ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሊቃውንት ጉባኤ ኅዳር 28 ቀን 2004 . የሰጠው መግለጫ ያስረዳል፡፡

                                                                                                          ይቀጥላል

ስብሐት ለእግዚአብሔር

No comments:

Post a Comment