ዳዊት ደስታ
/dawitdesta126@gmail.com/
ዘመናዊ ስልኮች
• ዘመናዊ ስልኮችን (smart phone)መግዛትና መጠቀም ከጊዜ ወደ ጊዜ በብዛት እየጨመረ ይገኛል::ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ከሆነ ስልክ እየተጠቀሙ መተኛት ወይም ደግሞ ከመኝታ አንድ ሰዓት በፊት ዘመናዊ ስልኮችን መጠቀም በሀይለኛው የእንቅልፍ ጥራትን እንዲሁም ባጠቃላይ ጤንነትን ዘላቂ በሆነ ሁኔታ ይጎዳል::በቂ እንቅልፍ አገኘንም አላገኘን ከመተኛታችን አንድ ሰዓት በፊት ዘመናዊ ስልኮቻችንን የምንጠቀም ከሆነ አእምሯችን "ሜላቶኒን" የተሰኘውን ሆርሞን ከማመንጨት ይታቀባል::ይህ ሆርሞን እንቅልፍ መተኛት ሲያስፈልገን ለሰውነታችን አስፈላጊውን ምልክቶች የሚያስተላልፍ ነው::• የዚህ ሆርሞን አለመመረት ወይም በበቂ ሁኔታ አለመገኘት ታዲያ ለተለያዩ የጤና ችግሮች ያጋልጣል::
• የእንቅልፍ ሰዓት ማነስ
• የማስታወስ አቅም መቀነስ
• የደከመ እንቅስቃሴ (reflex)
• አላስፈላጊ ውፍረት
• ከባድ የሆነ ድብርት እና በስተመጨረሻም
• ለካንሰር በሽታ ሊያጋልጠን ይችላል::
• በመሆኑም ከመተኛታችን አንድ ሰዓት በፊት ስልካችንን መጠቀም ማቆም ብንችል የተመረጠ ይሆናል::ምንጭ: http://wonderfulengineering.com
የሆሊውድ ዘፈኖች
• በሙዚቃው ኢንዲስትሪ ውስጥ ለምሳሌ“Stairway to Heaven” በሮክ ዘፈን ታሪክ በጣም ከተሰሙና በኤፍ ኤም ሬዲዮኖች በብዛት ከተደመጡ ዘፈኖች አንዱ ነው፡፡ በሃይማኖት ሽፋን የዝሙት አስተሳሰብ የሚያነሳሳ ነው፡፡• “ጎትስ ሄድ ሱፕ” የፍየል ራስ ሾርባ በ1973 የሙዚቃ አልበም “Sympthy for the devil፤ሲምፒቲ ፎር ዘዴቭል” የተሰኘው ሙዚያ የሠይጣን ማምለኪያ ቦታ ለሆነው መዝሙሮች አንዱ ነው፡፡
• በ2005 ዓ.ም. የተደረገ አንድ ጥናት እንደሚያመለክተው እድሜያቸው ከ14-35 ዓመት የሚሆኑ ወጣቶች በ Pornography ህይወት ከመጠመዳቸው በፊት 78% የሚሆኑት ከዘፈን ጋር ልዩ ወዳጅነት እንደነበራቸው ጥናቱ ጠቁሞል፡፡
• የ666፣ የቀንድ ምልክት፣ የሦስት ጎን በአንድ አይን ምልክቶች በብዙ ፊልሞች ላይ እያየን ነው፡፡
• Hymn to Lucifer(ለዲያብሎስ ውዳሴ) ይገባል በሚል /Alcister crowley/ዘፍኖአል፡፡ ሌዲ ጋጋ” በ2009ለ MTV VMA የአዋርድ ዝግጅት ሽልማቷን በተቀበለችበት ወቅት “Thanks for God and for gays” ብላለች፡፡
ክርስትናን ማንቆሸሽ
• በምዕራቡ ዓለም ጸረ ክርስትና የክርስቲያኖችን አስተምህሮና የአምልኮት መገለጫዎችን ለማንቋሸሽ፣ ጭቃ ለመቀባትና ለማስነወር የመዝናኛ ኢንዱስትሪው ለሕጻናት የሚዘጋጁ ፊልሞችን እንኳ ከመጠቀም ወደ ኋላ አላሉም፡፡የክርስትና አስተምህሮዎችን፣ ቀኖናዎችን፣ ባህላዊና ትውፊታዊ እሴቶችን እንዲሁም ግብረገባዊ መርሆዎችን የሚተቹና የሚያንቋሽሹ መምጣት ለትውልዱ ትልቅ ፈተና ነው፡፡
• ክርስቲያኖችን ደም የጠማቸውና ስለ ስልጣኔ አንዳችም ግንዛቤ የሌላቸው ቡትቶ ለባሽ ደንቆሮዎች አድረጎ የሚስለው ‹‹አጎራ›› የክርስቲያን ምእመናን እንደ ወሮበሎች ቤተመጻሕፍትን ሲያፈርሱ፣ መጻሕፍትን ሲያቃጥሉ፣ ፈላስፎችና ተመራማሪዎችን በሐይማኖት ስም ሲጨፈጭፉ ያሳያል፡፡
• በዚህ የሙዚቃ ቪዲዮ ላይ ክርስቶስና ደቀመዛሙርቱ ሐዋርያት ሞተር ሳይክል እንደሚነዱ ጋንግስታሮች ተደርገው ቀርበዋል … ሌዲ ጋጋም ሴተኛ አዳሪ ሊያስመስላት በሚችል መልኩ ተቀርጻ ክርስቶስን እንዲወክል ካስቀመጡት ሰው ጀርባ ተቀምጣትታያለች (ይህም ሆሊውድ እያቀነቀነው የሚገኘው … ክርስቶስና ማርያም መግደላዊት ጾታዊ ግንኙነት ነበራቸው የሚለው ስድብ አካል ነው)
• በአጠቃላይ የክርስትናን አስተምህሮ ከሚያንቋሽሹ፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮችና በቅዱሳን አባቶች ላይ ከሚያላግጡ ፊልሞችና የሙዚቃ ቪዲዮዎች መካከል እጅግ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡
ይቀጥላል፡፡
ስብሐት ለእግዚአብሔር
No comments:
Post a Comment