Tuesday, 3 January 2017

ቅዱሳን ሐዋርያት



ስብከት በሐዋርያትና በእነርሱ ዘመን እንዴት ነበር



ቅዱሳን ሐዋርያት ከጥሩ ምንጭ ከክርስቶስ የቀዱ ከእውነተኛው ብርሃን ከክርስቶስ የነሱ እንደ መሆናቸው የመምህራቸውን ትዕዛዝ አክብረው የተሰማሩበት የስብከት ሀገር ሩቅ ነው ቅርብነው ሳይሉ እንዲሁም ዘመድ ባዕድ ሳይለዩ ወንጌልን ለማስተማር ተበትነው ነበር መልካም ምሳሌነታቸው ለሁሉ እየሰጡ አልፈዋል ፡፡
ከሐዋርያት ውስጥ እንዳንዶቹ የሄዱበት አገር ካለመታወቁ የተነሳ የሰሩትና ያስተማሩት የሰጡትም ምሳሌ አስረጅ ግልጥ ሁኖ ሊታወቅ አልቻለም፡፡ ይሁን እንጂ ጨለማው አለም ሊበራ የቻለው አልጫው የነበረው ማህበራዊ ኑሮ ሊጣፍጥ የቻለው በመንፈሳዊ ቅንዓት ቆርጠው ተነስተው በትጋት ከማስተማራቸው የተነሳ የክስቶስንም ምሳሌነት ተከትለው የሰሩ ከመሆናቸውም የተነሳ እንደሆነ ሊታወቅ ተችሏል፡፡
ብዙዎቹም ሐዋርያት የሄዱበት አገር የሠሩትም ስራ ግልጥ ሆኖ በመታወቁ ሌሎችም እንደ እነርሱ እንደሰሩ በግልጥ ሊታወቅ ተችሏል፡፡ እነዚህም ሐዋርያት በሄዱበት አገር በቃል ብቻ አልሰበኩም አላስተማሩም ሰርቶ በማሳየት በመልእክትም ልዩ ልዩ አህጉርን ሰብከዋል አስተምረዋልም እንጂ፡፡ ከተጨባጭ ትምህርታቸው ጋር አለምን ያስደነቀው ትምህርታቸውንም ወደ መቀበል እንዲያዘነብል ያደረገው የኑሮ ቅድስናቸው ራስን በመጥላት ስለ ሰው ወገን በመስራታቸው ነው፡፡
ሐዋርያት የተሰለፉበት ስራ ከባድ የላካቸውን መምህራቸው ታላቅ ትእዛዙም ጥብቅ መሆኑን ተረድተው ሳይፈሩ ሳያፋፍሩ በየሄዱበት መስክረዋል አስተምረዋልም ሰርተዋልም ለዚህም የወንጌል መልእክት በዚያን ጊዜ የተሰለፉት ሐዋርያት ብቻ አልነበሩም ነገር ግን የነርሱን ፍለጋ የተከተሉ እነርሱንምበመመልከት በመንፈሳዊ ቅንዓት እየተነሱ ብዙዎች ክርስቲያኖች ሰርተዋል የክርስቶስን የምስራች ወንጌል አስተምረዋል፡፡
ክርስቶስ ከተነሳ በኃላ ‹‹ሁሩ ወመሀሩ ኩሎ አሕዛበ›› ያለውን ቅዱስ ቃል መመሪያ አድርገው በኢየሩሳሌም በይሁዳ በሰማርያ ከዚህም በኃላ እስከ ምድር ዳርቻ ሄደው አስተምረዋል (የሐዋ.ሥራ 1፡8) ፡፡ እነዚሁ ሐዋርያት በዓለም ቢበተኑም የዓለም ሕዝብ ቢያስተምሩም የስብከታቸው ማዕከል ኢየሱስ ክርስቶስ ነበር ማለት የክርስቶስን አዳኝነት በመግለጥ የክርስቶስን ወንጌል በመስበክ ነበር፡፡ የወንጌል ትምህርት የምስራች እንደመሆኑ ለሁሉ አስደሳች ዜና ይሁን እንጂ ማዕከል የሚያደርገው የተሰቀለውን ኢየሱስ ክርስቶስን ነው በዚህ መሰረት ሐዋርያት በዓለም ተበትነው ክርስቶስንና የአዳኝነት ሥራውን ለሁሉ አስታወቁ፡፡ ክርስቶስ እውነተኛው የዓለም መድሃኒት ሆኖ መገለጡን ለሠው ልጅ ሁሉ ቤዛ ሁኖ መሰጠቱን እርሱ ሙቶ እኛን ማዳኑን በግልጥ ሰበኩ አስተማሩ፡፡
ሐዋርያት በዚህ መልክ ያስተማሩ እንጂ ከእነርሱ የሰሙ የእነርሱ ተከታዮች የሆኑ ወንዶችም ሴቶችም የምስራች ተናጋሪዎች የወንጌል አስረማሪዎች እየሆኑ ተገኝተዋል፡፡ለዚህ ለወንጌል ትምህርት አዛዥና ታዛዥ የበላይና የበታች ሳይኖር ሁሉም የክርስቶስ ፍቅር ይዞት በመንፈሳዊ ቅንዓትም ተነሳስቶ ይሰብክ ነበር፡፡ሁሉም በሁሉ የወንጌል መልእክተኞች እውነት ተናጋሪዎች እየሆኑ በራሳቸው ፈቃድ እየሰሩ እነርሱም ‹‹የምናምነውን እንናገራልን›› በማለት የሰሙትን የተረዱትን ያመኑትን ሁሉ ይናገሩ ነበር (2ቆሮ 4፡13) ቅ/ጳውሎስ ይኽን የመሰለውን እውነት ሲያረጋግጥ ‹‹እኔም ሆንኩኝ እነርሱም ቢሆኑ እንዲሁ ይሰብካሉ እናንተም እንዲሁ አምነችሃል ሲል ፅፋል (1ቆሮ 15፡11) ሐዋርያት በስብከታቸው ተመሳቅሎ የነበረውን የጎዜውን ማህበራዊ ኑሮ ለወጡት መራራውን ሕይወት አጣፈጡት የተበላሸውን ሁሉ መልክ ሰጡት ተለያይቶ የነበረውንም ሕዝብ እገናኙት አንድነትን ሰጡት የሁሉም አባት አንድ እግዚአብሔር መሆኑን አስታወቁት አምኖም እንዲቀበል አደረጉት ሐዋርያት ይኽን ሁሉ በትክክል እንዲሰሩ የረዳቸው ራሳቸውን ክደው ለክርስቶስ ሰጥተው በመስራታቸው መስቀሉን ተሸክመው ወደፊት በመሄዳቸው ክርስቶስ ያዘዛቸውን በትክክል በመፈፀማቸው ነው፡፡ነ ከዚህም የተነሳ የሚመለከታቸው ሁሉ ፍፁምነታቸውን ተረዳ ፈፅሞም ተከተላቸው፡፡
ተላዊያነ- ሐዋርያት/ አፓሎጊቶች
ሀ. ተላዊያነ ሐዋርያት የተባሉት ከሐዋርያት ቀጥለው የተነሡ አባቶች ሲሆኑ በእርግጥም ሐዋርያትን በእግር የተከተሉ በግብር የመሰሉ እውነትን የተናገሩ አባቶች ነበሩ፡፡ እነዚህ አባቶች በሐዋርያት ጊዜ ማለት ከ1ኛው ምእት ጀምሮ የነበሩ በ2ኛው ምእት ዓመት የሠሩ ናቸው፡፡ ተላውያነ ሐዋርያትም ያሰኛቸው ከእነርሱ ቀጥለው ተነስተው የወንጌል አስተማሪዎች ከመሆናቸው ጋር ለሐዋርያት የተሰጠው መንፈስ ሳይከፈል ለእነርሱም የተሰጣቸው አባቶች ስለነበሩ ወንጌልን የበለጠ ለዓለም ያስታወቁ ቤተክርስቲያን አጽንተው የጠበቁ አባቶች ነበሩ፡፡
በዚህ በእነርሱ ዘመን መሰብሰቢያ የሚሆን አዳራሽ መቀደሻና መወዳሻ የሚሆን መቅደስ አልበነረም በየአማንያኑ ቤት እየተዘዋወሩ በመገኘት ጸሎት ይጸልዩ ማዕድን ይባርኩ ስብከትን ይሰብኩ ነበር፡፡ በዚህ ጥብቅ ስራቸው እውነተኛን ሃይማኖት ከኑፋቄ ሕዝቡን ከሐሰተኛ መምህራን ጠበቁ ለቤተክርስቲያን ጽንአትን ሰጡ፡፡
በ1ኛውና በ2ኛው ምእት ዓመት ግኖስቲሲዝም የሚባል የፍልስፍና አስተያየት ተስፋፍቶ በክርስትናው ላይ ጥርጣሪን ያሳደረ ክርስቲያኑንም ሕዝብ ያስቸግር ነበር፡፡ ይሁን እንጂ እነዚህ ተላዊያነ ሐዋርያት የተባሉ ፍጹማ አባቶች በቃልም በመልእክትም በማስተማራቸው የኑፋቄውን ማእበል ጸጥ ሊያደርጉ ክርስትናውንም በበለጠ ሊያስታዋውቁ ችለዋል፡፡
የስብከታቸው ዓይነት ግን በቤተሰብ ውይይት መልክ በቀጥተኛ አነጋገር እንጂ በስብከት ዘዴ በንግግር እቅድ አልነበረም፡፡ እነዚህ አባቶች የሐዲስ ኪዳን አስተጋብያን እንደመሆናቸው በየቦታው ሐዲስ ኪዳን እንዲነባብ በእርሱም ትምህርት እንዲሰጥ በማድረጋቸው ለሐዲስ ኪዳንና ለክርስትናው ትምህረት እውነተኛ ብርሃን ሰጪ ሁነው ሲያስታውሱ ይኖራሉ፡፡
ለ. አፓሎጊቲስ (ቃውማን) እነዚህ ሰዎች ከ120-220 ባለው ዘመን ውስጥ የነበሩና የሠሩ ናቸው ከአረማዊያንና ከአይሁዳውያን የተውጣጡ ፈላስፎችና ቴዎሎጂያያን ናቸው፡፡ ያለ ዘመናቸውን ሁሉ ለክርስቶስና ሃይማኖት መከታ በመሆን የጥብቅና ሥራ የሠሩ የተናገሩ የጻፋ አባቶች ናቸው፡፡
እንደሚታወቀው ሁሉ አይሁድ ብሉይ ኪዳን የተነቀፈባቸው አንዱ እግዚአብሔርም ቀርቶ በሦስት አማልክት የሚታመን መስላቸው ለሕጋቸውና ለአምልኮታቸው ቅንዓት ይዞአቸው አረማውያን ደግሞ ጣኦት የሚያመልከው ሁሉ ጣኦቱን እየተወ ወደ እውነተኛው እምነትና ክርስቲያናዊ ትምህርት ስለሄደባቸው እነርሱንም ምቀኝነት ያዛቸውና በአንድ በኩል አይሁድ በሌላ በኩል ደግሞ አረማውያን ክርስቲያኖችን ይከሱ ከነገስታቱ ጋርም ያጣሉ ክርስቲያኖች ምን ያሳዱድ ነበር፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ አረማውያን አገሩን የነርሱ የሚበዛውን ሕዝብ የነርሱ ነገስታቱም አረማውያን በመሆናቸው ክርስቲያኖች መንግስትን እንደሚያናውጡ ፀጥታን እንደሚነሱ እያደረጉ በመክሰሳቸው በክርስቲያኖች ላይ ብዙ ጭቆና ይደረግባቸው ነበር ነገር ግን እነዚህ ቃውማን(ጠበቆች) ሳያፍሩ ሳይፈሩም ለነግስታቱና ለሳፍንቱ የክርስቶስን አምላክነት የክርስትናውን እነተኛነት በአንድ አምላክም የሚያምኑ መሆናቸውን በግልፅ ይጽፉ ይመሰክሩ ይናገሩ ነበር፡፡
ቃሉ አፓሎጂቲስ ማለት ጠበቆች ተከራካሪዎች ማለት ነው የክርስትናውን እምነትና ትምህርት በመቃወም ለተነሱ ሁሉ ተገቢውን የመቃወሚያ መልስ በመስጠት ብዙ ፅፈዋል ሰብከዋል መስክረዋልም፡፡ ከመፃህፍቶቻቸው ጥቂቶቹ ወደልሳናችን መተርጎማቸው ያጠራጥር ይሆናል እንዲሁም የጥቂቶቹ የሰዎቹ ስምና ስራ በሰፊው ያለተገለጠ እንደሆነ እንጂ ዋና የቤተ ክርስቲያን ጠበቆች በመሆን የፃፍት አባቶች ብዙ ነበሩ፡፡

No comments:

Post a Comment