አብያተ ክርትያናትና ዓለም አቀፍ ጉባኤያት
ቅድስት
ቤተ ክርስቲያን ለመሠረተ እምነቷ መሠረት መጽሐፍ ቅዱስን ትውፊትን አባቶች የወሰኑትን የጉባኤያት ውሳኔዎችን እንዲሁም ጉባኤያቱን
ታደርጋለች፡፡ አንድ የነገረ መለኮት ተማሪም ይህንን የአባቶችን ትምህርት በመገንዘብ ስለጉባኤያቱ በቂ እውቀት ሊጨብጥና ከሌሎች
ቤተ እምነቶች ጋር ያሉትን የዶግማ ልዩነቶች በመገንዘብ ሊኖር ይገባል፡፡ ዘመኑ የቴክኖሎጂ በመሆኑ አያሌየመገናኛ ብዙኃን የጥንት
መናፍቃንን ትምህርት በማሰራጨት እንደ አዲስ መስበካቸው ስለማይቀር ጉባኤያቱን በደንብ መረዳት ይህንን ችግር ሁሉ እንደሚቀርፍ እገነዘባለሁ፡፡
በዚህ የትምህርት ምዕራፍ ዓለም አቀፍ ጉባኤያት በአብያተ ክርስቲያናት ምን እንደሚመስል
ማሳየትና ማስገንዘብ ነው፡፡ በዚህ ምዕራፍ ከተካተቱት ነጥቦች መካከል






የሚሉ ነጥቦች ተካተዋል፡፡ ይህ ምዕራፍ ላይ የተነሱት
ነጥቦች ያለቀላቸውና ሁሉንም ነጥቦች ያካተቱ ስላልሆኑ ተማሪዎች የተሰጣችሁን ዋቢ መጽሕፍት በመጠቀም እውቀታችሁን ማስፋት ይገባችኃል፡፡
አብያተ
ክርስቲያናት እስከ አራተኛው ክፍለ ዘመን ድረስ አንድ ነበሩ፡፡ መሠረተ እምነትን(ዶግማን) የሚቃረኑ የመናፍቃን ትምህርት በሚገጥሙ
ጊዜ የአብያተ ክርስቲያናት መሪዎች እየተሰበሰቡ ውሳኔዎችን ይደነግጉ ነበር፡፡ ይህም ሥርዓት የተጀመረው በሐዋርያት ዘመን ነው
51 ዓ.ም. ይህም እስከ አራተኛውመቶ ክፍለ ዘመን የቀጠለ ነው፡፡
የኢየሩሳሌም
ጉባኤ[1]
የመጀመርያው ጉባኤ ነው፡፡ አረማዊያን ወደ ክርስትና በቅዱስ በርናባስ አማካኝነት ከተመለሱና በአንጾክያ ቤተ ክርስቲያን ከመሠረቱ
በኃላ አንዳንድ አማኞች በመነሳት የሙሴን ሕግ መፈጸም ይገባል በማለት ሁከት ባስነሱ ጊዜ ይህን በተመለከተ ውሳኔ ለመስጠት ሐዋርያት
ተሰብስበዋል፡፡[2]
የተላለፉ
ውሳኔዎች
1.
ለጣዖት በመሠዋቱ ምክንያት ረከሰ
ምግብ አትብሉ
2.
ታንቆ የሞተ እንስሳ አትብሉ
3.
ከዝሙት ተጠበቁ የሚሉ ናቸው
ይህ ጉባኤ በሙሴ ሥርዓተ ሕግ ላይ ያተኮረና በወቅቱ ለነበረው ጥያቄ መልስ የሰጠ ነበር፡፡ከዚህ
በኃላ የተደረጉ ጉባኤያት ግን መሠረተ እምነት ላይ መሠረት ያደረጉ ነበሩ፡፡ በተለያዩ ጊዜ የተነሱ መናፍቃንን ትምህርታቸውን በመመርመር
በጉባኤያቱ ትምህርታቸው እንዲቀርብ በራሳቸው አንደበት ጭምር በመጋበዝ ከመጽሐፍት ከጌታችን ትምህርት ልዩ የሆነውን በመለየት ውሳኔዎችን
አሳልፈዋል፡፡
በጉባኤውም የመናፍቃኑን ትምህርት ከማውገዝ ከመለየት በተጨማሪ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ላይ
ውሳኔ በማሳለፍ ክርስቲያኖች በተደነገገው ሕግና ሥርዓት እንዲመሩ አስችለዋል፡፡ ጉባኤያቱ ፍጹም ከፖለቲካ ነጻ የነበሩ ቢሆኑም አንዳንድ
ጉባኤያት ግን በነገሥታቱ ጫና የተደረገባቸውና በፖለቲካዊ ቅኝት የተቃኙ ስለነበሩ በስተመጨረሻ ለአብያተ ክርስቲያናቱ መለያየት ምክንያት
ሆኖል፡፡
የጉባኤያት ቁጥር በአብያተ ክርስቲያናት
የጉባኤያት በጥንት ኦርቶዶክሳዊ አብያተ ክርስቲየናት
(oriental orthodox church)
የተደረጉበት ዓመት
|
ጉባኤያቱ
|
የተወገዘውትምህርት
|
325 ዓ.ም.
|
ጉባኤ ኒቂያ
|
አርዩስ
ወልድ ፍጡር ነው
|
381 ዓ.ም.
|
ቁስጥንጥንያ
|
አቡናርዩስ
አውሳብዮስ
መቅዶንዩስ
|
431 ዓ.ም.
|
ኤፌሶን[3]
|
ቢላግዩስ
ንስጥሮስ
|
ሁለተኛው የኤፌሶን ጉባኤ በ449
ዓ.ም የአውጣኬን ትምህርት ለማውገዝ በፍላፕያኖስ ዘቁስጠንጥንያ የተጠራና የተደረገ ቢሆንም እንደ ዓለም አቀፍ ጉባኤ የሚታይ ባለመሆኑ
እነዲሁም የተወገዘው በሁለት ባሕርይና ሁለት ፍቃድ አለው በሚሉ ሰዎች በመሆኑ(ፍላፕያኖስ ዘቁስጥንጥንያ በመሆኑ ቤተ ክርስቲያን
ከቁጥር የምትቆጥረው አይደለም፡፡ነገር ግን ቅዱስ ዲዮስቆሮስም ይህን ትምህርት አውግዞታል፡፡
የጉባኤያቱ ቁጥር በካቶሊክ አብያተ ክርስቲያናት
የተደረጉበት
ዓመት
|
ጉባኤያቱ
|
የጉባኤው
መግለጫ
|
325
ዓ.ም.
|
ጉባኤ ኒቂያ
|
አርዩስ
ወልድ ፍጡር ነው
|
381
ዓ.ም.
|
ቁስጥንጥንያ
|
አቡናርዩስ
አውሳብዮስ
መቅዶንዩስ
|
431
ዓ.ም.
|
ኤፌሶን
|
ቢላግዩስ
ንስጥሮስ
|
451
|
ኬልቄዶን
|
ምንታዌ
|
553
|
ሁለተኛ ቁስጥንጥንያ
|
ምንታዌን ያጸና ጉባኤ
|
681
|
ሦስተኛው ቁስጥንጥንያ
|
ምንታዌን ያጸና ጉባኤ
|
787
|
ሁለተኛው ኒቅያ
|
ስለጌታና ስለቅዱሳን ስዕላዊ አገላለጽ
|
870
|
አራተኛው ቁስጥንጥንያ
|
መንፈስቅዱስ ከአብና ከወልድ የሚሰርጽ
መሆኑ የወሰነበት ጉባኤ[4]
|
1123
|
የመጀመርያው ላተርን
|
የቤተ ክርስቲያኒቱ መሪ በራሱ
ሥልጣን ጳጳሳትን ይሾም ሥርዓት የተሰራበት
|
1139
|
ሁለተኛው ላተርን
|
|
1179
|
ሦስተኛው ላተርን
|
የፖፕ አመራረጥ ሥርዓትን በተመለከተ
ቀኖና የተሰራበት
|
1215
|
አራተኛው ላተርን
|
የእምነቱ ተከታይ የሆነ ሰው
በትንሣኤ ንስሐን እንዲቀበልና ቁርባን አንዲቆርብ የተደነገገበት ነው፡፡ቁርባን መታሰቢያ እንደሆነም የወሰኑት
|
1245
|
የመጀመርያው ልዩን
|
በጉባኤው 22 ምዕራፍ ያካተተ
ውሳኔ ተላልፉል፡፡
|
1275
|
ሁለተኛው ልዩን
|
በዚህ ጉባኤ ላይ ከግሪክቤተ
ከርስቲያን ጋር በመስማማት ወደ ቀደመ አንድነታቸው ለመምጣት ጥረት የተደረገበት ነው
|
1312
|
ጉባኤ ቫን
|
በአስተዳደራዊ ጉዳዩች ላይ
የተወያየ ጉባኤ
|
1414
|
ኮንስታንስ
|
የፖፑን ሥልጣን በሚመለከት
የተካሄደ ጉባኤ
|
1442
|
ባስል ፍራር ላተርን
|
የፖፑን ሥልጣን በሚመለከት
የተካሄደ ጉባኤ
|
1512-1517
|
አምስተኛው ላተርን
|
ስለሰው ልጅ ነፍስ የተወሰነበት
|
1531-65
|
ተራንት
|
ስለቅዱሳን አማላጅነትና የመጽሐፍ
ቅዱስ ቀኖናን
|
1870
|
ቫቲካን አንደኛ
|
የካቶሊክን እምነት ምንነት የፖፑን ሥልጣንና ፖፑ ፍጹም ከስሕተት የጸዳ መሆኑን በዚህ
ጉባኤ ላይ ውሳኔ አሳልዋል
|
1962-1965
|
ቫቲካን ሁለተኛ
|
እነዚህ የካቶሊክ አብያተ ክርስቲያናት
የሚቀበሏቸው ጉባኤያት ብዛት በቁጥር 21 ሲሆኑ በተለያዩ ርዕሰ ጉዮች ላይ ውሳኔዎችን
አሳልፈዋል፡፡
የጉባኤያቱ ቁጥር በምዕራባዊያኑ ፕሮቴስታንቶች
የፕሮቴስታንቱ
ዓለም የመጀመርያዎቹን ሰባት ጉባኤያት ወይም የመጀመርያዎቹን አራት ጉባኤያት ይቀበላሉ፡፡ይህ ማለት ግን ለውሳኔዎቹ ሁሉ ተገዥ ናቸው
ማለት ይቸግራል፡፡ ጠለቅ ያለ ነገረ መለኮትን ትምህርት ግንዛቤው ስለለላቸው በአብያተ ክርስቲያናቱ መካክል እንኳን ተራ ነው ብለው
የጽፉም አልጠፉም፡፡ ይህን ለመገንዘብ የሚያበቃ በቂ እውቀት የላቸውም፡፡ ሌላው ውሳኔዎቹን ሁሉ ያከብራሉ ወይ ብለን ብንጠይቅ መልሳችን
የሚሆነው አይደለም ነው ምክንያቱም ውሳኔዎቹና መሠረተ እምነታቸው ጭምር በእጅጉ የሚለያይ ሆኖም ስለምናገኝ ነው፡፡
የሉተርያን
መቶዲስትስ ፕሮቴስታንት(luteran and Methodists)
የፕሮቴስታንቱ
ዓለም የመጀመርያዎቹን ሰባት ጉባኤያት ወይም የመጀመርያዎቹን አራት ጉባኤያት ይቀበላሉ፡፡ይህ ማለት ግን ለውሳኔዎቹ ሁሉ ተገዥ ናቸው
ማለት ይቸግራል፡፡ እንደኦርቶዶክሱ ወይም እንደካቶሊኩ ዓለም ባለ አተረጓገም ጉባኤያቱን በዝርዝር አይጠቀሙባቸውም እንደውም የራሳቸው
ድምዳሜ ጋር ተስማሚ ካልሆነ ይሰሩዞቸዋል፡፡
የተደረጉበት
ዓመት
|
ጉባኤያቱ
|
የጉባኤው
መግለጫ
|
325
ዓ.ም.
|
ጉባኤ ኒቂያ
|
አርዩስ
ወልድ ፍጡር ነው
|
381
ዓ.ም.
|
ቁስጥንጥንያ
|
አቡናርዩስ
አውሳብዮስ
መቅዶንዩስ
|
431
ዓ.ም.
|
ኤፌሶን
|
ቢላግዩስ
ንስጥሮስ
|
451
|
ኬልቄዶን
|
ምንታዌ
|
553
|
ሁለተኛ ቁስጥንጥንያ
|
ምንታዌን ያጸና ጉባኤ
|
681
|
ሦስተኛው ቁስጥንጥንያ
|
ምንታዌን ያጸና ጉባኤ
|
787
|
ሁለተኛው ኒቅያ
|
ስለጌታና ስለቅዱሳን ስዕላዊ አገላለጽ
|
ሌሎች የፕሮቴስታንቱ ዓለም
እነዚህ የፕሮቴስታንት ክፍሎች ጳጳሳት ቀሳውስት ዲያቆናት የሚባል የሥልጣነ ክህነት ደረጃ የሌላቸው በመሆኑ በዚህም የቀኖና ሥርዓት ስለማያምኑ የጉባኤያቱም ውሳኔ ባራስ የመወሰንና መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ የሚለውን ትምህርት ስለሚከተሉ ጉባኤያቱን አይቀበሏቸውም፡፡ በእነዚህ ጉባኤያት የተወሰኑ እንደመጽሐፍ ቅዱስ ቁጥር ቀኖና ጭምር የሚቀበሉት አይደለም፡፡
በምሥጢረ ሥላሴ የማያምኑ ፕሮቴስታንቶች
እነዚህ ቤተ እምነቶች እንደጆቫ ዊትነስ ያሉ ዘመን አመጣሽ እምነቶች ጉባኤያቱን የሰው ልጅ ሐሳቦች የተንጸባረቁባቸው ‹‹ተራ ፍልስፍናዎች›› ናቸው እንጂ አባቶች በመጽሐፍት ተመርኩዘው እግዚአብሔርን አጋዥ አድርገው የተሰሩ ሕግና ሥርዓቶችን እንዳልሆኑ ያምናሉ፡፡[5]
የመለከዊያን(የምሥራቅ) ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን
የክርስቶስን
አምላክነትና ሰውነት በትክክል ለመረዳት በ451 ዓ.ም. በኬልቄዶን የተደረገውን ጉባኤ ማስታወስ ያሻል፡፡ ስብሰባው እንደሌሎቹ ጉባኤያት
ሁሉም ተሳታፊዎች የሚስማሙበትን ውሳኔ ማሳለፍ አቃተው፡፡ በኃይል የተላለፈውም ውሳኔ የቅዱስ ቄርሎስን (በጉባኤ ኤፌሶን) የተወሰነውን
ውሳኔ የሚቃረን ስለነበር የእስክንድርያና አንዳንድ አብያተ ክርስቲያናት አልተቀበሉትም፡፡
ምንጮች
እንደሚሉት የንጉሡ ወገኖች የእስክንድርያን ቤተ ክርስቲያን የወከለውን የቅዱስ ቄርሎስ ደቀ መዝሙር በነበረው ታላቅአባት በቅዱስ ዲዮስቆሮስ ላይ መከራ ስላጸኑበት ይህን መከራ ለመቀበልና ከእውነት ጋር ለመተባበር ያልቻሉት መለካዊያን የንጉሱንና የሊዩንን ውሳኔ ተቀበሉ፡፡
እስክንድርያ ላይ የግብጽ ምዕመናን ያልተቀበሉት የንጉሡ ወገኖች ግን የተቀበሉት ፕሮቴርዩስ የሚባል ሰው ሾሙ፡፡ በዚህም ምክንያት የእስክንድርያ ቤተ ክርስቲያን ለሁለት
ተከፈለች የተዋሕዶ አማኞችና የንጉሣዊያን(መለካዊያን MELKIES) የንጉሣዊያኑ ቁጥር ትንሽ ነበር አሁንም ግን አሉ፡፡
የተደረጉበት ዓመት
|
ጉባኤያቱ
|
የጉባኤው መግለጫ
|
325
ዓ.ም.
|
ጉባኤ ኒቂያ
|
አርዩስ
ወልድ ፍጡር ነው
|
381
ዓ.ም.
|
ቁስጥንጥንያ
|
አቡናርዩስ
አውሳብዮስ
መቅዶንዩስ
|
431
ዓ.ም.
|
ኤፌሶን
|
ቢላግዩስ
ንስጥሮስ
|
451
|
ኬልቄዶን
|
ምንታዌ
|
553
|
ሁለተኛ ቁስጥንጥንያ
|
ምንታዌን ያጸና ጉባኤ
|
681
|
ሦስተኛው ቁስጥንጥንያ
|
ምንታዌን ያጸና ጉባኤ
|
787
|
ሁለተኛው ኒቅያ
|
ስለጌታና ስለቅዱሳን ስዕላዊ አገላለጽ
|
የምሥራቅ
አብያተ ክርስቲየናት ሰባቱን ጉባኤያት ቢቀበሉም በሦተኛው ቁስጥንጥንያ ጉባኤና በሁለተኛው ኒቅያ ጉባኤ መካከል የተደረገ አንድ ጉባኤ አላቸው ነገር ግን ይህ ጉባኤ መሠረተ
ሥርዓት(ቀኖና) የተደነገገባቸው ናቸው ስለዚህም በካቶሊካዊያኑ ዘንድ ተቀባይነት የለውም ብለው ያስቀምጣሉ፡፡[6]
መለካዊያኑ በቅድመ ስማቸው የቀጠሉ ሲሆን በ1054 ዓ.ም. ከምዕራባዊያኑ ካቶሊካዊያን ተገንጥለዋል፡፡ ይህም የሆነበት ምክንያት በዋነኝነት ካቶሊካዊያኑ መንፈስ ቅዱስ ከአብና ከወልድ የሰረጸ ነው የሚለውን ትምህርት በማስተማራቸው ይህንንም የቁስጥንጥንያ ቤተ ክርስቲያን በመቃወሟ ነው፡፡ ነገር ግን እስካሁን ድረስ ሁሉት ባሕርይ የሚለውን ትምህርት የሚቀበሉ በመሆናቸው ከጥንት ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት በመሠረተ እምነት ደረጃ ልዩ ብያደርገንም በነገረ መለኮት አረዳድ ባሕል ግን በብዙ የምንቀራረብ ነን፡፡
[1] በ51
ዓ.ም.
[2] ከአይሁድ
ወደ ክርስትና የመጡት
ከአእዛብ ወደ ማመን
የመጡትን የሙሴን ሕግ
መፈጸም ይገባቹኃል እያሉ
ዘወትር ክርክር ያነሱ
ስለነበር ለዚህ እልባት
ለመስጠት ሕዋርያት ተሰበሰቡ[3] ሁለተኛው
የኤፌሶን ጉባኤ በ449
ዓ.ም የአውጣኬን
ትምህርት ለማውገዝ የተደረገ
ነው፡፡በፍላፕያኖስ ዘቁስጠንጥንያ
እንደተለመደው የቤተ ክርስቲያን
መሪዎችን ሳይጠራና ኤጵስ
ቆጶሳትን ሰብስቦ በ
431 አወገዛው፡፡ ይህም የሆነበት
ምክንያት ፍላጵያኖስ ሁለት
ባሕርይና ሁለት ፍቃድ
አለው ከሚሉ ሰዎች
በመሆኑ በችኮላ በመሆኑ
ዳግመኛ ቅዱስዲዮስቆሮስ በ449
ኤፌሶንን ጉባኤ አደረገ
ነገር ግን አውጣኪ
አንድ ባሕርይ በመጠፋፋት
ካለው ትምህርት ለጊዜውም
ገሸሽ ብሎ እምነቴ
የሠለስቱ ምዕትና የቅዱስ
ቄርሎስ ነው በማለቱ
ከእስራቱ ፈጠውታል፡፡ በኃላ
ላይ ግን ይህን
ትምህርት መልሶ በማስተማሩ
ዳግመኛ ተወግዞል፡፡[4] Pop Nicholas l say I had refused to
recognize Patriarch I of Constantinople who attached the pop as a
heretic.because the pop teach the concept of Filioque(holy sprit emanating from
God the father and the son
[5] Nontrinitaran churches such us The church
of jusus Christ of latter day saints The church of God(sevevth day) unitarians
and Johovah witnesses
[6] Qunisext/penthekte council or the council
in Trullo (696) mostly administrative councils that raised some local canons to
ecumenical status and established principles of clerical discipline. The
council accepted by the Eastern Orthodox Church as a part of the six council.
(orthodox wiki)
No comments:
Post a Comment