እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሰዎ!
የጌታችን በዓለ ልደት መቼ ተጀመረ? መድኃኒታችን የተወለደበት ቀን ይታወቃልን?
የልደት በዓል የሚከበርበትስ ቀን በምዕራባውያንና በእኛ ቤተ ክርስቲያን ለምን ተለያየ? የእኛ ቤተ ክርስቲያን ልደትን ለምን ታኅሣሥ 29 ቀን ታከብራለች? ምዕራባውያንስ የልደትን በዓል ለምን December 25 ያከብራሉ? ምዕራባውያን የጌታን ልደት ከእኛ ሁለት ሳምንት ያህል ቀድመው December 25 (በእነርሱ አቆጣጠር ታኅሣሥ ፳፱) ያከብራሉ። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ደግሞ ታኅሣሥ ፳፱ ነቀን ታከብራለች። የዚህ ልዩነት መንሥኤ ምንድን ነው? የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ልደትን በዚህ ቀን ለማክበሯ መሠረቷ ምንድን ነው? የምዕራባውያንስ መሠረ ታቸው ምንድን ነው? ከሁለቱስ የትኛው ቀዋሚና ትክክል ሆኖ ይታያል? በመጀመሪያ የኢትዮጵያን ቤተ ክርስቲያን በዓለ ልደትን የምታከብረው ታኅሣሥ ፳፱ ቀን የሆነበት ምክንያት ካየን በኋላ ምዕራባውያኑ በዓለ ልደትን የሚያከብሩበትን ቀን ምንጭና የትመጣ በአጭሩ እንዳስሳለን። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተወለደበት ቀን በመጽሐፍ ቅዱስ በቀጥታ ካለመገለጹ የተነሣ ትክክለኛውን ቀን ለማግኘት ታሪክን ተከትለው ብዙ የደከሙ አሉ። ከዚሁም የተነሣ ዕለተ ልደቱን በተመለከተ የቀናት ልዩነቶች ተከሥተዋል። ሆኖም ግን ምንም እንኳ መጽሐፍ ቅዱስ ቀኑን ይህ ነው ብሎ በግለጽ ባይናገርም አመልካቺ የሆነ ፍንጭ ሳይሰጥ ግን አልቀረም። ይህንን ለመረዳት በሉቃስ ወንጌል በምዕራፍ አንድ ከቁጥር ፰-፲፬ የተጻፈውን መመልከት ያስፈልጋል። “በይሁዳ ንጉሥ በሄሮድስ ዘመን ከአብያ ክፍል የሆነ ዘካርያስ የሚባል አንድ ካህን ነበረ። ሚስቱም ከአሮን ልጆች ወገን ነበረች። ስምዋም ኤልሳቤጥ ነበር። . . . እርሱም በክፍሉ ተራ በእግዚአብሔር ፊት ሲያገለግል ወደ ቤተ መቅደስ ገብቶ ለማጠን ዕጣ ደረሰበት። በዕጣንም ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ በውጭ ቆመው ይጸልዩ ነበር። የጌታም መልአክ በዕጣኑ መሠዊያ ቀኝ ቆሞ ታየው። ዘካርያስም ባየው ጊዜ ደነገጠ፤ ፍርሃትም ወደቀበት። መልአኩም እንዲህ አለው፦ ዘካርያስ ሆይ ጸሎትህ ተሰምቶልሃልና አትፍራ፣ ሚስትህ ኤልሳቤጥ ወንድ ልጅ ትወልድልሃለች፣ ስሙንም ዮሐንስ ትለዋለህ። ተድላና ደስታም ይሆንልሃል፣ በመወለዱም ብዙዎች ደስ ይላቸዋል።” /ሉቃ፩፥፭፣ ፰፥፲፬/ በዚህ ክፍለ ምንባብ በጣም አስፈላጊ የሆነ አመልካቺ (ጠቋሚ) ነገር ተመልክቶ እናገኛለን። ሆኖም ይህን አሳብ ፈልፍሎ ለማግኘት ከቅዱሳት መጻሕፍት ቃልና አሳብ ጋር ተዛምዶ ሊብራራና ሊተረጎም ያስፈልገዋልና ነገሩን በጥንቃቄና በማስተዋል መከታተልን ይጠይቃል። ዋናው አመልካቺ ፍሬ ነገር መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ለዘካርያስ ስለ መጥምቁ ዮሐንስ መወለድ ያበሠረበት ቀን በዕብራውያን ዘንድ “በዓለ ሥርየት” ተብሎ ይከበር የነበረው ቀን መሆኑ ነው። በዓለ ሥርየት የሚባለው በዓል በዕብራውያን አቆጣጠር በሰባተኛው ወር ማለትም በታስሪን (በጥምቀት) አሥረኛ ቀን የሚውል ታላቅ በዓል ነበር። ይኸውም በዓል በኦሪት ሕግ “በሰባተኛው ወር፣ በእግዚአብሔር ፊት ከኃጢአታችሁ ሁሉ ትነጻላችሁ። ታላቅ ሰንበት ይሆንላችኋል . . .” ተብሎ የታዘዘበት ታላቅ በዓል ነበር። /ዘሌ ፲፮፥፳፱–፴፤ ፳፫፥፳፯፤ ዘኁ ፳፱፥፯-፲፩/ በዚህ በዓል ቀን ሊቀ ካህናቱ የተቀደሰ ልብሰ ተክህኖውን ለብሶ ወደ መቅደስ ይገባል። በእግዚአብሔር ፊት ባለው መሠዊያ የእሳት ፍህም አምጥቶ ጥናውን ይሞላል። እንዳይሞት የጢሱ ደመና በምስክሩ ላይ ያለው መክደኛ (ማስተሥረያ) ይሸፍን ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት ዕጣኑን በእሳቱ ላይ ያደርጋል። ፲፮፥፲፪-፲፫። እንዲሁም ካህኑ ለማስተሥረይ ወደ መቅደሱ በሚገባበት ጊዜ መጀመሪያ ለራሱ፣ ከዚያም ለሕዝቡ ሁሉ አስተሥርዮ እስኪወጣ ድረስ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ሌላ ማንም ሰው አይኖርም ነበር። ዘሌዋ ፲፮፥፲፯። እንግዲህ ዘካርያስ ወደ ቤተ መቅደስ በገባ ጊዜ እነዚህ ድርጊቶች መፈጸማቸውን ቅዱስ ሉቃስ በወንጌሉ ገልጾአቸዋል። “እርሱም (ዘካርያስ) በክፍሉ ተራ በእግዚአብሔር ፊት ሲያገለግል ወደ ቤተ መቅደስ ገብቶ ለማጠን ዕጣ ደረሰበት። በዕጣንም ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ በውጭ ቆመው ይጸልዩ ነበር።” ይላል። ስለዚህ ዘካርያስ ወደ ቤተ መቅደስ የገባበት ቀን የተጠቀሰው ሥነ ሥርዓት በሚፈጸምበት በበዓለ ሥርየት ቀን ሲሆን ይህም በዕብራውያን አቆጣጠር በጥቅምት አሥረኛ ቀን ነው። ስለዚህ ቅዱስ ሉቃስ ይህን ቀን በተለየ ሁኔታ ጌታችን ለተወለደበት ቀን ታሪካዊ የአኀዝ መነሻና የመሠረት ድንጋይ መሆኑን ጠቁሞ አመልክቶአል ማለት ነው። ይህ ዘካርያስ የተበሰረበት ቀን የአይሁድ በዓለ ሥርየት የዋለበት በዕብራውያን የዘመን አቆጣጠር ጥቅምት አሥረኛ ቀን መሆኑን ብዙ ጥንታውያን የቤተ ክርስቲያን አባቶች መተርጉማን ገልጸው እናገኛለን። ለምሳሌም ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅና ማር ዮሐንስ ወንጌለ ሉቃስ ምዕራፍ አንድን ሲተረጉሙ ሰፋ ባለ ሐተታ ገልጸውት እናገኛለን። የኢትዮጵያ መተርጉማንም በተወራረሰ የሊቃውንት ትርጓሜ “ዘካርያስ ወደ ቤተ መቅደስ ገባ” ከሚለው ላይ በታሪክ ሲያትቱ “የጥቅምት ጨረቃ ሠረቅ ባደረገች በአሥር ቀን ነው፤ ዕለቱም ዕለተ ዮሴፍ (በዓለ ሥርየት) ነው፤. . . ተሰብስበው ይጸልያሉ፣ ወበይእቲ ዕለት አሕምምዋ ለነፍስክሙ (በዚያች ዕለት ራሳችሁን ታዋርዳላችሁ) እንዲል” ብለው አስረድተዋል። (ትርጓሜ ወንጌል፣ ገጽ 324) እስከዚህ ድረስ ዘካርያስ ዮሐንስን እስከሚወልድ የተበሠረበት ቀን በዓለ ሥርየት በሚባል በዕብራውያን አቆጣጠር ታስሪን (ጥምቀት) አሥር ቀን ለመሆኑ የተገናዘበበትን ትምህርታዊና መጽሐፍ ቅዱሳዊ መንገድ አይተናል። አሁን ደግሞ ይህን አቆጣጠር ከኢትዮጵያ የቀን አቆጣጠር ጋር ያለው ግንኙነት እንዴት እንደሆነና መቼ እንደሚያርፍ እንመልከት። በዕብራውያን አቆጣጠር በዓለ ሥርየት የዋለው በጨረቃ አቆጣጠር ጥቅምት አሥር ቀን ስለነበር ይህንን ወደ ኢትዮጵ ያውያን የቀን አቆጣጠር መልሶ ዕለቱን ለማግኘት ወደ ዘመን አቆጣጠር መግባት ግድ ይሆናል። ነገር ግን ወደዚህ የቀን አቆጣጠር ዝርዝር ብንገባ የያዝነውን ጉዳይ እንዳያወሳስበው ዝርዝር ሐተታውን ትተን እንዲሁ ዕለቱ የሚውልበትን ብቻ እንመልከት። በዕብራውያን አቆጣጠር ወርኀ ታስሪን (ጥምቀት) አሥር ቀን በኢትዮጵያ አቆጣጠር የዋለው መስከረም ፳፯ ቀን ነበር። ይኸውም የጨረቃ የቀን አቆጣጠር ሲለወጥ የሚገኝ ነው። ይህም ማለት በጨረቃ አቆጣጠር ፲ ቀን የነበረው በዓለ ሠርቅ በፀሐይ የቀን አቆጣጠር መስከረም ፳፯ ቀን ነበር ማለት ነው። ስለዚህ ዘካርያስ የተበሠረው መስከረም ፳፯ ቀን ሆኖ እናገኘዋለን። በዓሉ ወዲያው እንዳበቃ ዘካርያስ ወደ ቤቱ ገባ፤ መጥምቁ ዮሐንስ ተፀነሠ። ቅዱስ ወንጌል “የማገልገሉ ጊዜ ሲፈጸም ወደ ቤቱ ገባ። ሚስቱ ኤልሳቤጥም ፀነሠች” ሲል ያስረዳል። ቅዱስ ያሬድ ይህን መሠረት በማድረግ “ወእምድኅረ ክልዔ መዋዕል ፀንሠት ኤልሳቤጥ ብእሲቱ ከሁለት ቀንም በኋላ ፀነሠች” ብሏል። ስለዚህ ዮሐንስ መጥምቅ የተፀነሠው መስከረም ፳፱ ቀን ነው ማለት ነው። መጥምቁ ዮሐንስ ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ መንገድ ጠራጊና በፊቱ የሚሄድ መልእክተኛ መሆኑ በነቢያት ትንቢት ተነግሮ ቆይቷል። ኢሳ ፵፥፫-፭፤ ሚል ፫፥፩። እንደ ትንቢቱም ቃል ሁሉ ዮሐንስ ከፅንሠቱ ዕለት ጀምሮ በተፈለገው መንገድ ለጌታችን ጎዳናውን እያቀና የሚሄድ የፊቱ መልእክተኛ ሆኖ ተገኝቶአል። ሉቃ ፩፥፸፮-፸፱። መጥምቁ ዮሐንስ የተፀነሠበትና ለተወለደበት ቀን ከዚህ በላይ እንደተመለከትነው መነሻ አብነት ሆኖ ይገኛል ማለት ነው። እንግዲህ በዚህ ታሪካዊ ቁርጠኝነትና ትስስር መሠረት ኤልሳቤጥ በፀነሰች በስድስተኛ ወሯ ለዘካርያስ ያበሠረው መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ወደ ቅድስት ድንግል ማርያም ተልኮ “ትፀንሻለሽ፣ ትወልጃለሽ” በማለት መድኃኒታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን እንደምትፀነስና እንደምትወልድ ነገራት። ይህም መጥምቁ ዮሐንስ ከተፀነሰበት ጊዜ ፳፱ ቀን) አንሥቶ ሲቆጠር መጋቢት ፳፱ ቀን ይሆናል። መልአኩ እመቤታችንን ሲያበስራት “መካን ትባል ለነበረችው (ለኤልሳቤጥ) ይህ ስድስተኛ ወር ነው” ሲል የተናገረው የፅንሰትዋን ጊዜ የሚያመለክት አይደለምን? ሉቃ ፩፥፴፮-፴፰። ስለዚህ መጋቢት ፳፱ ቀን ቃል ሥጋ የሆነበትና በድንግል ማኅፀን የተፀነሰበት ዕለት ነው ማለት ነው። ከዚህ ከመጋቢት ፳፱ ቀን ጀምሮ ወንድ ልጅ በእናቱ ማኅፀን የሚቆይባቸውን ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀናት (225 ቀናት) ስንቆጥር ጳጉሜን ጨምሮ ዕለተ ልደቱ ታኅሣሥ ፳፱ ቀን ላይ ይውላል። ስለዚህም መጋቢት ፳፱ ቀን የተፀነሰው ጌታችን ከኃጢአት በቀር የሰውነትን ሥራ ሁሉ ፈጽሟልና ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በእናቱ ማኅፀን ቆይቶ ታኅሣሥ ፳፱ ቀን በቤተልሔም ዘይሁዳ ተወለደ። ስለዚህም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱሳዊ የታሪክና የትውፊት ማስረጃዎችን መሠረት አድርጋ የመድኃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስን በዓለ ልደት ታኅሣሥ ፳፱ ቀን በታላቅ ምስጋና ታከብራለች። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተወለደው ታኅሣሥ ፳፱ ቀን መሆኑን ከጻፉ አበው መተርጉማንና የሐሳበ ዘመን መምህራን መካከል የተወሰኑትን ከዚህ ቀጥሎ እንመልከት።
፩. ይቤ ወልደ መነኰስ፦ “ውእቱ ተወልደ ለጸቢሐ ሠሉስ በሌሊት አመ እሥራ ወተስዑ ለወርኃ ታኅሣሥ በተፍጻሜተ ሃምሳ ወኃምስቱ ምዕት ዓመተ ዓለም። - እርሱ ጌታችን ወደ ማክሰኞ አጥቢያ በሌሊት በታኅሣሥ ፳፱ ቀን ፭ ሺሕ ፭፻ ዓመተ ዓለም ሲፈጸም ተወለደ” ይላል። (ማር ዮሐንስ መተርጕመ፣ ትርጓሜ ወንጌል ዘማቴዎስ ገጽ ፹፰
፪
. ይቤ
ሰዒድ
ወልደ
በጥሪቅ፦
“በሠላሳ
ወሠለስቱ
ዓመተ
መንግሥቱ
ለሄሮድስ.
. . አመ
እሥራ
ወተስዑ
ለወርኃ
ታኅሣሥ
ተወልደ
እግዚእ
ኢየሱስ።
- ሰዒድ
ወልደ
በጥሪቅ
በሄሮድስ
፴፫
ዓመተ
መንግስት.
. . በታኅሣሥ
፳፱ኛ
ቀን
ጌታ
ኢየሱስ
ተወለደ”
ይላል።
፫.
ይቤ
ጊዮርጊስ
ወልደ
ዓሚድ፦
“ወኮነ
ድሙረ
ሃምሳ
ወኃምስቱ
ምዕተ
ዓመት
እስከ
ልደተ
እግዚእነ
ኢየሱስ
ክርስቶስ.
. . ወተፀንሠ
አመ
እሥራ
ወተስዑ
ለመጋቢት
በዕለተ
እሑድ።
ወተወልደ
አመ
እሥራ
ወተስዑ
ለታኅሣሥ
በዕለተ
ሠሉስ።
- እስከ
ጌታችን
ኢየሱስ
ክርስቶስ
ልደት
የተደመረው
ቁጥር
፭
ሺሕ
፭፻
ዓመት
ነው።
መጋቢት
፳፱
ቀን
እሑድ
ዕለት
ተፀነሠ፤
ታኅሣሥ
፳፱
ቀን
ማክሰኞ
ዕለት
ተወለደ”
ብሎአል።
(ጊዮርጊስ
ወልደ
ዓሚድ፣
ገጽ
፲፯-
፲፰።)
፬.
ቅዱስ
ባስልዮስ
ዘቂሣርያ
(፫፻፴-፫፻፸፮ ዓ.ም. ) ስለ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በታኅሣሥ ፳፱ ቀን ያስተማረው ትምህርት በሳሂዲክ (Sahidic - የቅብጥ ቋንቋ ጥንታዊ ዘዬ) ይገኛል። (Coptic Encyclopedia, P. 380)
፭.
ዲድስቅልያ
አንቀጽ
፳፱፦
“ቀዳሚ
በዓል
ዘውእቱ
ዕለት
ልደቱ
ለክርስቶስ
አመ
እሥራ
ወኃሙሱ
ለታስዕ
ወርኀ
በኁልቆ
ዕብራውያን
ወበኀሳበ
ግብፃውያን
አመ
እሥራ
ወተስዑ
ለወርኃ
ታኅሣሥ
ዘውእቱ
ራብዓይ
ወርኅ
ግበሩ።
- የመጀመሪያው
በዓል
የክርስቶስ
ልደት
ነው።
ይኸውም
በዕብራውያን
አቆጣጠር
በዘጠነኛው
ወር
በ፳፭ኛ
ቀን
በግብፃውያን
አቆጣጠር
በታኅሣሥ
በ፳፱ኛው
ቀን
ታደርጋላችሁ”
ተብሎ
ተወስኖአል።
(ዲድስቅልያ
አንቀጽ
፳፱
ገጽ
፴፯)
እነዚህ
ለአብነት
ተጠቀሱ
እንጂ
የልደተ
ክርስቶስን
ዕለት
ታኅሣሥ
፳፱
መሆኑን
የጻፉና
የገለጹ
ሊቃውንትና
ጸሐፊዎች
ብዙዎች
ናቸው።
ስለሆነም
የኢትዮጵያ
ቤተ
ክርስቲያንና
የግብፅ
ኦርቶዶክስ
(ኮፕት)
ቤተ
ክርስቲያን
በዓለ
ልደትን
ታኅሣሥ
፳፱
ቀን
የሚያከብሩት
በተረዳና
በታወቀ
ማስረጃና
መሠረት
ላይ
ተመሥርተው
ነው
እንጂ
እንዲሁ
አይደለም።
የምዕራባውያን
የልደት
በዓል
ለምን
December 25 ሆነ?
ምዕራባውያኑ
የጌታችንን
በዓለ
ልደት
ለምን
December 25 እንደሚያከብሩ
የተለያዩ
አስተያየቶችና
ምክንያቶች
ይሰጣሉ።
ከነዚህም
ጎላ
ያሉት
ምክንያቶች
የሚከተሉት
ናቸው።
አንደኛው
ከዘመን
አቆጣጠራቸው
ጋር
ለማዛመድ
የተደረገ
ሂደት
ነው
የሚል
ነው።
ይኸውም
ዲያናስዮስ
ኤክሲጀስ
የተባለው
የሮም
መነኵሴ
፭፻፳፭
ዓ.ም. በቫቲካኑ ጳጳስ አነሳሽነት አዲስ የዘመን አቆጣጠር አዘጋጅቶ አቀረበ። “ታሪክን ተከትዬ ባደረግሁት ጥናት መሠረት ክርስቶስ የተወለደው ከ፩ ዓመተ ምሕረት በፊት ፯ ዓመት ቀደም ብሎ (በ፭ሺሕ ፬፻፺፫ ዓመተ ዓለም) ነው” የሚል አሳብ አቀረበ። በሁሉም የክርስትና ዓለም ጥቅም ላይ ሲውል የነበረው ዓመት ፭፻፳፭ ዓ.ም. ላይ ፯ ዓመታትን ጨምሮ በአንድ ጊዜ ፭፻፴፪ አደረሰው። ሆኖንም ይህ የአሳብ ዘመን ስሌቱ ስህተት ነበር። ስለዚህም ምሥራቃውያን አብያተ ክርስቲያናት ይህን አዲስ የዘመን አቆጣጠር ስሌት ውድቅ በማድረግ በነበረው በጥንቱ የዘመን አቆጣጠር መጠቀማቸውን ቀጠሉ። አዲሱ አቆጣጠር ግን አዲስ ዓመት የሚቀይረው በጥር ወር ሆነ። ለዚህም አንዱና ዋናው ምክንያት በአውሮፓ ከባዱ የቅዝቃዜ ወቅት እያለቀና የፀሐይ ሙቀት እየመጣ የሚሄድበት ወቅት ወርኀ ጥር በመሆኑም እንደሆነም ይነገራል። ስለሆነም የክርስቶስን በዓለ ልደት ከአዲሱ ዓመት መጀመሪያ ጋር አንድ ለማድረግ ሲሉ በዓለ ልደቱን በ December 25 አደረጉት የሚል ነው። ሌላውና በብዙ ምሁራን ዘንድ የሚታመነው አሳብ ደግሞ December 25 የተመረጠበት ምክንያት አውሮፓውያን ክርስትናን ከመቀበላቸው በፊት ያከብሩት ከነበረው የጣዖት በዓል ዕለት የተገኘ ነው የሚለው ነው። ሮማውያን ከቄሣር ኦሬሊያን (275 ዓ.ም.) ጀምሮ የ “ኃያሏ ፀሐይ” ( “Sol Invictus” the Unconquered
Sun) የአምልኮ
በዓልን
በዚሁ
ቀን
ያከብሩ
ነበር።
December 25 የፀሐይ
የልደት
ቀን
ተብሎ
ይጠራ
የነበረ
ሲሆን
በዚሁ
ዕለትም
በመላዋ
የሮም
ግዛት
ታላቅ
አሕዛባዊና
ጣዖታዊ
የእምነት
ሥነ
ሥርዓታዊ
ክብረ
በዓል
ይፈጸም
ነበር።
ኋላ
ሕዝቡ
ክርስትናን
እየተቀበለ
ሲሄድ
ከፍጡር
የፀሐይ
አምልኮና
በዓል
ወደ
እውነተኛው
ፀሐይ
(ፀሐየ
ጽድቅ)
ወደ
ኢየሱስ
ክርስቶስ
አምልኮ
እንዲመለሱና
የእርሱን
በዓለ
ልደት
እንዲያከብሩ
ለማድረግ
ይህንን
ቀን
መርጠዋል።
ይህ
አስተሳሰብ
በዘመኑ
በነበሩ
ጸሐፊዎች
ተመልክቶአል
(W.P. Dawson, “Christmas: Its Origins and Associations,” London, 1902). የፀሐይ አምልኮና ልማድ በተለይም በዚህ ቀን በሕዝቡ ይደረግ የነበረው ጣዖታዊ የበዓል አከባበር ልማድ ብዙዎችን በቀላሉ ሊለቃቸው ስላልቻለ በዚሁ ቀን ላይ የኢየሱስ ክርስቶስን የልደት በዓል ማክበር ደካሞችን ከጣዖታዊ ልማድ ነፃ ለማውጣት ይጠቅማል ብለው በማሰብ ያደረጉት ነው። እንግዲህ እንደ ኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አቆጣጠር መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርሰቶስ ከተወለደ ይኸው ልክ ሁለት ሺሕ አምስት ዓመት ሆነው። ዓመተ ፍዳ አልፎ ዓመተ ምሕረት (የምሕረት ዓመት) በሆነ ዘመን ላይ ስላለን በዓለ ልደቱን ስናከብር እግዚአብሔር ለእኛ ያደረገልንን ታላቅ ውለታ በማስታወስ፣ የፈጸመውን ታላቅና ድንቅ ሰው የመሆን (የተዋሕዶ) ምሥጢር በማሰብና በመረዳት ሊሆን ይገባል። እንዲህ ሲሆን በበዓለ ልደቱ ተገኝተው “ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት ወሰላም በምድር ሥምረቱ ለሰብእ - ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ይሁን፤ ሰላምም በምድር፣ ለሰውም በጎ ፈቃድ” እያሉ ካመሰገኑ ቅዱሳን መላእክት ጋር አብረን ደስ እያለን ምስጋናን ለአምላካችን ልናቅብ ይገባናል። ቅዱሳን መላእክት ለእኛ ለሰዎች የተደረገው መልካም ነገር አስደስቶአቸው ምስጋና ካቀረቡ እኛ የድርጊቱ ባለቤቶች ምን ያህል ደስ ሊለንና ልናመሰግን ይገባን ይሆን? ስለሆነም እግዚአብሔርን እንደማያውቁ እንደ አሕዛብ አብዝቶ በመብላትና በመጠጣት፣ በዘፈንና በጭፈራ፣ በዝሙትና በመዳራት፣ በአጠቃላይ ነፍስንና ሥጋን በሚያጎሰቁሉና ይህን ሁሉ ቸርነት ያደረገልንን አባታችንን እግዚአብሔርን በሚያሳዝኑ ተግባራት ሳይሆን ለክርስቲያን እንደሚገባ በቤተልሔም (በቅድስት ቤተ ክርስቲያን) በመገኘትና ነገረ ልደቱን በማሰብ፣ በያሬዳዊ ዜማ፣ ምስጋና ከሚያቀርቡ አባቶችና መዘምራን ጋር አብረን እናመስግን። የአምላካችንን ውለታና ፍቅርም በሕይወታችን ዘልቆ የታተመና በዓመት አንድ ጊዜ በታኅሣሥ ፳፱ ወይም በየወሩ ፳፱ ቀን ብቻ ሳይሆን በልባችን ጽላት ሊቀረጽና ሁልጊዜም በየዕለቱ ልናስበው ይገባል። ሕይወታችንም ለአምላካችን የሚገዛና ለእርሱ ደስ የሚያሰኝ ሊሆን ይገባዋል።
ስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ ሐመር ኅዳር/ታኅሣሥ ፳፻
No comments:
Post a Comment