ከመምህር ያሬድ ነጋ የተወሰደ
ይህን ጥያቄ የምናገኘው በመጽሐፈ መነኮሳት ነው፡፡ ለዚህም መልስ ሲሰጥ 4 ነገሮችን ይጠቅሳል ለዛሬ የመጀመሪያውን
ክፍል እንመልከት
ጥሩ መምህር ይሆን ዘንድ
ለዚህም ምሳሌ ይሆነን ዘንድ በአንድ ወቅት አባ መቃርስ የተባለ አባት(በአበምኔትነት) በሚያስተደድረው ገዳም ውስጥ አንድ ወጣኒ(ጀማሪ) መነኩሴ በዚያ ገዳም ውስጥ ነበረ። በዚያም ወቅት ጾር(ፈተና) በረታበትና ወደ አንድ አባት ገዳማዊ ይመክሩት ዘንድ ይሄዳል። እኝያም አባት ከምክር ይልቅ ተቆጥተው "የማትችለውን ለምን ጀመርክ?" በማለት ወደ በአቱ (ፍልፍል ቤት) እንዲሄድ ያደርጋሉ። አሁንም አልቻለምና "አባቴ አልቻልኩም ምን ይሻላል?" ይላቸዋል እሳቸውም መፍትሄ ከመስጠት ይልቅ ተቆጡት፡፡ በመንፈስ ሲያያቸው የነበረው አባ መቃርስ ወጣኒውን ሲፈትኑት የነበሩት ሰይጣናት ወደኝያ አባት እንዲሄዱ ያዛቸዋል ፡፡ እኝያም አባት ከወጣኒው ይልቅ ሰይጣናቱ ቢበረቱባቸው ገዳሙን ጥለው ሊወጡ ሲሉ አባ መቃርስ በር ላይ ቆይቶ "ወዴት እየሄዱነው ኣባቴ?" ብሎ ጠየቃቸው፡፡ "አልቻልኩም አልቻልኩም" እያሉ ሊወጡ ሲሉ አባ መቃርስ እንዲህ ነበር ያላቸው "ምክር ፈልጎ ወደ እርስዎ ቢመጣ ምነው ወጣኒው ላይ የማትችለውን ለምን ጀመርክ ብለው ፈረዱበት?በሉ እንዲህ ማለት አይገባም ብሎ ለሁለቱም ፈተና እየተጋደሉ በባእታቸው እንዴት መፅናት እንደሚገባቸው አስተምሮ ሰይጣናቱን አባረረላቸው" ይለናል፡፡ እኛም በዚህ ምድር ላይ ስንኖር ብዙ ፈተናዎች ሲገጥሙን ፈጣሪያችን የሚፈቅደው ነገ ከእኛ ምክር ፍለጋ ለሚመጡት ልጆቻችን ፣ጓደኞቻችን ፣ተማሪዎቻችን ወዘተ ላይ በኃጢአትህ(ሽ) የመጣብህ(ሽ) ነው እያልን ከመፍረድ ይልቅ ፅናት የሚለምዱበትና ጠላት ዲያብሎስን ድል የሚያደርጉበት ኃይል የሚያገኙበት እንድናሳያቸውና ጥሩ የብርሃን መንገድ(ፍኖተ ብርሃን) እንድናሳያቸው ነውና መፈተናችንን እንውደደው።
No comments:
Post a Comment