Tuesday, 17 January 2017

የእግዚአብሔር መገለጥ

በዲ/ን ያሬድ መለሰ


የፍጥረታት ጌታ በባሕርይው ምጡቅ የሰው ልጅ በሥጋዊ ደማዊ ጥበብ የማይደርስበት ነው፡፡ የእግዚአብሔርን ድንቅ ባሕርያት ከእርሱ እርሱ ለመረጣቸው ቅዱሳን ሰዎች እንደእምነታቸው ጽናት እንደመንፈሳዊ ትሩፋትና ተጋድሎ ይገልጣል፡፡ በሃይማኖት የሚኖር ሰው እግዚአብሔር ማን እንደሆነ ያውቃል የጌታንም ባሕርያት ይገነዘባል፡፡ እግዚአብሔርም በተለያየ ኅቡረ አምሳል ይገለጥለታል፡፡(ዕብ 11) ክርስትናም የመገለጥ ሃይማኖት ነው፡፡ ይህም መገለጥ ትልቅ ሥፍራ አለው ምክንያቱም ዓለም ሁሉ የዳነው በክርስቶስ መገለጥ ነውና(ዮሐ. 316)
እግዚአብሔር ምጡቅ ረቂቅ ከአእምሮ በላይ ቢሆንም ከአባታችን አዳም ጀምሮ በተለያየ ጊዜ ለቅዱሳን ተገልጦል፡፡ (ዘፍ 38) ሊቀ ነቢያት ሙሴ እግዚአብሔርን 570 ጊዜ ያህል አናግሮታል ተገልጦለታልም( ዘኁ 125 )ለቅዱሳኑም ለሄኖክ መዓዛ ባለው እንጨት ለአብርሃም በሦስት ሰዎች አምሳል ለኖኅ በቀስተ ደመና ለያዕቆብ በመሳላል ከፍታ ላይ ተቀምጦ ለኢሳይያስ በዙፍኑ ተቀምጦ ለዕዝራ በአንበሳ አምሳል ለዳንኤል በሽበታም ሰው አምሳል ተገልጦል፡፡ ለነቢያቱም በብዙ ምሳሌ መገለጡም የእግዚአብሔርን የተለያየ ባሕርይ የሚያስረዳ ነው፡፡ በሸመገለ ሰው አምሳል ሲገለጥ ፍትሐዊነቱን፤ ብርቱ ጦረኛ ሲሆን ተዋጊነቱን፤ አንድ ቦታ እንዳጣ ነዳይ መታየቱን በአንድ ቦታ እንደሚዘገይ በሌላ ቦታ የሚቀድመው እንደሌለ መጻፉን አስተውል የባሕርያቱ ጥልቅነትን በመገለጡ እንደሚያስረዳን አስተውክ፡፡ ቅዱስ ኤፍሬም እንዳለ ‹‹እርሱ እንደ መራዳችን መጠን ተገለጠ(አስተማረን) ስንል እርሱ ራሱ እንደኛ ነው ማለታችን አይደለም፡፡ እርሱ በእኛ ምሳሌ ተገለጠ ወይም አልተገለጠ እርሱ ራሱ ነው አይለወጥም፡፡ ሲፈልግ እኛን ለማስተማር አንዱ ጠባያችን ተገልጦ ይታየናል ሌላ ጊዜ ደግሞ አስቀድሞ የለበሰውን እንደልብስ አውልቆ ሌላ ልብስ ለብሶ ይገለጥልናል እርሱ ለእኛ በመንገሩ እርሱ እንዲህ ነው ማለት አይደለም ነገር ግን ባሕርይው የማይመረመር ነውና በምንረዳው በእኛ ምሳሌ ተገኝቶ ፍቃዱን ገለጠልን››
በአጠቃላይ የእግዚአብሔርን የመገለጥ ነገር በሦስት ዘመናት ከፍሎ መመልከት ይቻላል፡፡ የመጀመርያው ከመጀመርያው ሰው አዳም እስከ ሊቀ ነቢያት ሙሴ ድረስ ያለውን በሕገ ልቡና፡- በቃል፣ በራእይ፣ በተዓምር እየተገለጠ በማነጋገር አምላክነቱን አስረድቷል፡፡( ዘፍ.28-18 ዘፍ.39 ዘፍ.121) ሌላው ከሊቀ ነቢያት ሙሴ እስከ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መምጣት ያለውን የሕገ ኦሪት ዘመንም፡-በቃል በራእይ በተአምር እና ሕግና ሥርዓት በመስጠት አምላክነቱን አስረድቷል/አስተምሯል፡፡( ዘኁ 125 ) በመጨረሻም ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ በጠባብ ደረት በአጭር ቁመት ተመራልሶ ከሕግ በታች ሆኖ የሥጋን ባሕርይ ገንዘብ አድርጎ መገለጡን ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ ሆኖ በመካከላቸው ተገኝቶ መምህር ሆኖ የአምላክ ልጅ አምላክ መሆኑን በግልጽ አስረድቷል፡፡
የክርስቶስ መገለጥ ስንል ምን ማለታችን ነው
ቅድስት በቤተ ክርስቲያን የክርስቶስን የመገለጡን ነገር ትልቅ ሥፍራ ትሰጠዋለች፡፡ አስቀድሞም ለነቢያቱ በነገረው መሠረት ተወለደ(ገላ 44) ለቃሉም መዘግየት አላስተዋልንም ይህም ከሌሎቹ መገለጦች ፍጹም ልዩና አስደናቂም ነው ስለዚህም ሁሌም በአንክሮ በአኮቴት በውዳሴና በምሥጋና እናደንቀዋለን፡፡ ለዚህም ነው አበው እግዚአብሔር ዓለምን ከፈጠረበት ጥበቡ ያዳነበት ይበልጣል የሚሉት ሥጋን የለበሰው አምላክ ተወለደ ተጠመቀ ሞተ ተቀበረ በሦስተኛው ቀን ተነሳ አረገ ተመልሶም ለፍርድ ይመጣል ይህ ሁሉ የሆነው ታዲያ በሥጋ በመገለጡ ነው(ራዕ17) ፡፡ የክርስቶስን መገለጥ የምትሰብከውም ክርስትና የመገለጥ ሃይማኖት ናት መባልዋ ለዚህ ነው፡፡



የአምላክ ሰው ሆኖ የመገለጥ ምሥጢር


መገለጥ ማለት ረቂቁ አምላክ በተአቅቦ ርቀቱን ሣይለቅ ውሱን ሥጋን ውሱኑም ሥጋ በተአቅቦ ውስንነቱን ሳይለቅ ረቂቅ መለኮትን የሆነበት በአጭር ቃል የቃል ግብር ለሥጋ የሥጋ ግብር ለቃል የሆነበት ረቂቅ ምስጢር ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ቀዳማዊ ደኃራዊ የሆነው አምላክ ሞት የሚስማማው ሆነ፤ ዘመን የሚቆጠርለት ሥጋ ዘመን የማይቆጠርለት ሆነ፡፡ ሥጋ በማይመረመር ምስጢር የመለኮትን ገንዘብ ገንዘቡ ቢያደርግፊተኛውና መጨረሻው ሕያውም እኔ ነኝ ሞቼም ነበርሁ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ሕያው ነኝ /ራእ.117/ ማለት የቻለበት ምስጢር ነው፡፡ የረቀቀው ገዝፎ የገዘፈው ረቆ፣ ሰማያዊው ምድራዊ ምድራዊው ሰማያዊ ሆኖ መታየት ማለት ነው፣ ከዓለም ተሰውሮ የነበረው ምስጢር ግልጥ ሆኖ መታየት ማለት ነው ይህንንም ምሥጢር ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በጢሞቴዎስ መልእክቱእግዚአብሔርን የመምሰል ምስጢር ያለጥርጥር ታላቅ ነው፤ በሥጋ የጠገለጠ፣ በመንፈስ የጸደቀ፣ ለመላእክት የታየ፣ በአሕዛብ የተሰበከ፣ በዓለም የታመነ፣ በክብር ያረገ /1 ጢሞ 316/ በማለት፡፡ ከልደት እስከ ዓቢይ ጾም መጀመሪያ ያለው ጊዜ ዘመነ አስተርእዮ /የመገለጥ ዘመን/ የመታየት ወቅት ይባላል
ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነሥቶ በፍጹም ተዋሕዶ ሰው መሆኑን /ዓለምን ለማዳን መወለዱን የምንገልጽበት ወቅት ነው፡፡
የመገለጡ ዓላማ ምንድን ነው
1.
የሰይጣንን ሥራ ይሽር ዘንድ
ቅዱስ ዮሐንስ በመልእክቱወበእንተ ዝንቱ አስተርአየ ወልደ እግዚአብሔር ከመ ይሰዐር ግብሮ ለጋኔን” “የዲያብሎስን ሥራ ይሽር ዘንድ የእግዚአብሔር ልጅ ተገለጠ፡፡” 1 ዮሐን.38 ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ የተገለጠው የዲያቢሎስን ክፉ ምክር ያስወግድ ዘንድ ነው፡፡
የሰይጣንም ክፉ ግብርም ምንድን ነው?
3 አርዕስተ ኀጦውዕ /የኀጢአት መሠረቶች/ በመጥለፍ /በማታለል/ የሰውን ልጅ ከክብር ማዋረድ ነው፡፡ በዚህም ሥራው የሰው ልጆችን ለአምስት ሺሕ አምስት መቶ ዘመን በኀልዮ በነቢብ እና በገቢር ከመርገም በታች አድርጎ ገዛ ዮሐ.143
እንግዲህ ልጆቹ በሥጋና በደም ስለሚካፈሉ፣ እርሱ ደግሞ በሞት ላይ ሥልጣን ያለውን በሞት እንዲሽር፣ ይኸውም ዲያብሎስ ነው፣ በሕይወታቸውም ሁሉ ስለሞት ፍርሃት በባርነት ይታሠሩ የነበሩትን ሁሉ ነጻ እንዲያወጣ በሥጋና በደም እንዲሁ ተካፈለ፡፡ብሏል ዕብ.214-16
 
ስለዚህ ጌታ በዘር ይተላለፍ የነበረውን ኀጢአት እንበለ ዘር በመጸነስ የአዳምንን የሔዋን የዲያቢሎስ አገልጋይነት የሚያሳየውን በዮርዳኖስ የቀበረውን የዕዳ ደብዳቤ በጥምቀቱ በሲኦል ያኖረውን በስቅለቱ እንደሰውነቱ ረግጦ እንደአምላክነቱ አቅልጦ ሞትን በትንሣኤው አጥፍቶ ነጻነትን ሰብኮልናል 1 ጴጥ.319
ሦስቱ አርእስተ ኀጣውዕ የሚባሉትም፡-
1.
ስስት፡- ያልሰጡትን መሻት /መፈለግ ስግብግብነት ማለት ነው፡፡
2.
ፍቅረ ንዋይ፡- በቃኝ አለ ማለት ነው፡፡
3.
ትዕቢት፡- አምላክ እሆናለሁ ብሎ መሻት መፈለግ ነው፡፡
ዲያብሎስ ጌታን በእነዚህ በሦስቱ ኀጣውዕ ፈትኖት ድል ተነስቷል፡፡ ማቴ.42-8 እኛም በስስት በፍቅረ ንዋይ እና በትዕቢት እንዳንጠፋ እንደ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ኑሮየ ይበቃኛል ማለትን ልንለምድ ይገባናል፡፡ ወደ ዓለም ያመጣነው አንዳች ነገር የለንም፤ ከእርሱም ልንወስደው የምንችል የለምና፡፡ ምግባችንንና ልብሳችንን ካገኘን ይበቃልና፡፡ ባለጸጋ ሊሆኑ የሚወዱ ግን በጥፋትና በመፍረስ፥ ሰዎችን የሚያሰጥምና በሚያሰንፍ፥ በሚጎዳም በብዙ ምኞትና በፈተና፥ በወጥመድም ይወድቃሉ፡፡ ገንዘብን መውደድ የክፋት ሁሉ ሥር ነውና፥ ይህንም በመመኘት ተሳስተው ሃይማኖታቸውን የለወጡ ብዙዎች ናቸውና፥ ለራሳቸውም ብዙ መቅሠፍትን ሽተዋልና፡፡” 1.ጢሞ.66-11 በማለት መክሮናል፡፡
2.
ለሰው ልጅ ነጻነትን ይሰብክ ዘንድ ነው፡፡ /ይዋጀን ዘንድ ነው/
ለድኆች የምሥራችን ይነግራቸው ዘንድ፣ ለተማረኩትም ነጻነትን ይሰብክላቸው ዘንድ ያዘኑትንም ደስ ያሰኛቸው ዘንድ፣ ዕውሮችም ያዩ ዘንድ፣ የተገፉትንም ያድናቸው ዘንድ፣ የታሰሩትንም ይፈታቸው ዘንድ የቈሰሉትንም ይፈውሳቸው ዘንድ  የተመረጠችውንም የእግዚአብሔርን ዓመት ይሰብክ ዘንድ ነው፡፡ሉቃ.418-20 ገላ.44
3.
እኛ ከእግዚአብሔር እንወለድ ዘንድ ነው፡፡
አምላክ ሰው የሆነው በስሙ አምነን ተጠምቀን የመንግሥተ ሰማያት ዜጋ እንሆን ዘንድ ነው፡፡ ዮሐ.112 ማቴ.2819 ዮሐ.35 ማር.1016 ገላ.326
4.
ጽድቅን ያስተምረን ዘንድ ነው፡፡
ክርስቶስ ወደ ዓለም የመጣበት ዋና ዓላማ ሰውን ለማዳን ሲሆን በተጨማሪ፡- ክርስቶስ ፍጹም በሆነ መልካም አኗኗሩ፣ ጠፍቶ የነበረውን የእግዚአብሔርን አርዓያና አምሳል /ዘፍ. 126-27/ እንደገና ለመመለስ ለሰዎችም የመልካም ኑሮ አብነት ለመሆን፤እንደመምህርነቱ እውነተኛውን ትምህርትና ዕውቀት ለመስጠት ሐሰት አስተምህሮዎች አስተሳሰቦችን ለማረምና ለማስተካከል፤እግዚአብሔር ሰውን የሚወድ ሰማያዊ አባት መሆኑን በተግባር ለማሳወቅና ልባችንም በፍቅር እንዲሞላ ለማድረግ፤እንደ መልካም እረኛና ጠባቂ ድሆችንና ችግረኞችን ለመርዳት ነው፡፡ ቅድስት ቤተክርስቲን ይኼንን ታምናለች፡፡ በመዋዕለ ስብከቱ እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ ወደ እኔ እኔም አሳርፋችኋለሁ፤ ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ፤ ከእኔም ተማሩ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜም ቀሊል ነውና፡፡ብሏል ማቴ.1128-29 ቅዱስ ጴጥሮስምክርስቶስም ደግሞ ፍለጋውን እንድትከተሉ ምሳሌ ትቶላችሁ መከራን ተቀብሎአልሲል እንደተናገረ ጌታችን አርአያ ለመሆን ሰው ሆነ፡፡ (2 ጴጥ 221)
5.
ፍጹም ካሳ ለመክፈል
 
በአዳም ምክንያት ወደ ዓለም ኀጢያት ወደ ዓለም ገብቶ ትውልዱን ሁሉ ተቆጣጥሮ ስለነበር የሚጸለየው ጸሎት የሚሠዋው መሥዋዕት የሚያድን አልነበረም፡፡ (ኢሳ 646) ብዙዎች የብሉይ ኪዳን አበው ደማቸውን አፍሰዋል፡፡ መራራ ሞትን ታግሰዋል ነገርግን የበደል ካሳ መሆን ግን አልቻሉም ምክንያቱም የበደሉ ዘር ስለነበረባቸውና የእግዚአብሔር ክብር ስለጎደላቸው፡፡ ስለዚህም ፍፁም አምላክ የሆነ አምላካዊ ቃል በምድር ላይ ፍፁም አምላክ ፍፁም ሰው ሆኖ ተገለጠ፡፡
 
የዓለምን ኀጢያት ተሸከመ (ኢሳ 534) ቅድስት ሕይወቱንም መሥዋዕት አድርጎ ካሳ ከፈለልን (ኢሳ 535) ቅዱስ ጳውሎስበዓለም ፍፃሜ ራሱን በመሠዋት ኀጢአትን ሊሽር አንድ ጊዜ ተገልጧልናብሎ እንደተናገረው (ዕብ 926) በተጨማሪም (ዮሐ 1015-18) ተመልከት
6.
ፍቅርን ያሳየን ዘንድ ነው፡፡ 
 ምንም ዓይነት ረብ ጥቅም ሳይፈልግ እንዲሁ በከንቱ ወደደን፡፡ ዮሐ.316  ‹‹ፍቅር ሰሐቦ ለወልደ ኃያል እመንበሩ ወአብጽሆ እስከ ለሞት›› ፍቅር ኃያል ወልድን ከመንበሩ ሳበው እስከሞትም አደረሰው›› በማለት ሊቃውንት የተናገሩበት ምክንት ይህ ነው፡፡
እግዚአብሔር ምን ያህል እንደወደደን እነሆ እዩ እኛ ኀጢአተኞች ስንሆን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞተ፤ እንግዲህ በደሙ ከጸደቅን ከሚመጣው መከራ በእርሱ እንድናለን፡፡ እኛ የእግዚአብሔር ጠላቶቹ ስንሆን በልጁ ሞት ይቅር ካለን ከታረቅን በኋላም በልጁ ሕይወት እንድናለን፡፡ብሏል፡፡ ሮሜ.58-11 ወንድሞቻችን ሆይ እግዚአብሔር ይህን ያህል ከወደደን እኛም እርስ በርሳችን ልንዋደድ ይገባናል፡፡ እግዚአብሔርንስ ከቶ ያያሉ ሰው የለም እርስ በርሳችን ከተዋደድን ግን እግዚአብሔር አብሮን ይኖራል፡፡ ፍቅሩም በእኛ ፍጹም ይሆናል፡፡ብሏል፡፡ 1 ዮሐ.410-13
ይቆየን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር

No comments:

Post a Comment