Thursday, 5 January 2017

የካቶሊካዊያን ብቻ የሚቀበሏቸው ጉባኤያት

የካቶሊካዊያን ብቻ የሚቀበሏቸው ጉባኤያት
ጉባኤ ላተራን የመጀመርያው
የቤተ ክርስቲያኒቱ መሪ በራሱ ሥልጣን ጳጳሳትን ይሾም ዘንድ ከመንግስትም ጋር በሕብረት እንዲሰሩ የተወሰነበት ጉባኤ ነው፡፡ ይህ ጉባኤ መሠረተ እምነት ላይ የተመረኮዘ ጉባኤ አይደልም፡፡ ተጨማሪ 25 ቀኖናዎችና ድንጋጌዎች በዚህ ጉባኤ ላይ ተሰርተዋል፡፡
ጉባኤ ላተራን የሁለተኛ
ይህም ስለካህናት የጋብቻ ሁኔታ ስለዲያቆናትና ስለመነኮሳት የአኗኗር ሥርዓት ቀኖና የተሰራበት ነው፡፡ ቀሳውስትና መነኮሳት በድንግልና ሕይወት መኖር እንደሚገባቸው ካቶሊካዊያኑ የወሰኑት በዚህ ጉባኤ ነበር፡፡ ይህ ቀኖና ከጥንታዊያን ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት ልዩ የሆነ ነው ምክንያቱም ቀሳውስት ሕጋዊያን ጭምር መሆን ይችላሉና ነው፡፡ ተጨማሪ 30 ቀኖናዎችና ድንጋጌዎች በዚህ ጉባኤ ላይ ተሰርተዋል፡፡
ጉባኤ ላተራን የሦስተኛ
የፖፕ አመራረጥ ሥርዓትን በተመለከተ ቀኖና የተሰራበት ነው፡፡ ፖፑ የጉባኤውን ሁለት ሦስተኛ ድምጽ አግኝቶ መመረጥ እንዳለበት ይደነግጋል ይህም ሥርዓት እስከ ፖፕ ጆን ፖል ሁለተኛ ድረስ የተሰራበት ነው፡፡በገንዘብ ክህነትን ስመቀበል ሲሞናዊነትና ስለሕገወጥ የመሳሪያ ሽያጭ በዚህ ሙስሊሙን መርዳት በሚመለከትም ውሳኔ አሳልፎል፡፡
ጉባኤ ላተራን የአራተኛ
በዚህ ጉባኤ ቢያንስ የእምነቱ ተከታይ የሆነ ሰው በትንሣኤ ንስሐን እንዲቀበልና ቁርባን አንዲቆርብ የተደነገገበት ነው፡፡ቁርባን መታሰቢያ እንደሆነም የወሰኑት በዚህ ጉባኤ ነው፡፡[1]
የመጀመርያው ለዩን
ይህ ጉባኤ የተለየ ውሳኔ ያላሳለፈ ጉባኤ ስሆን በዚህ ጉባኤ ላይ ከስፔን ከፈረንሳይ ከጣሊያን ግዛት ብቻ የተወጣጡ የካቶሊክ አባቶች እንደተሳተፉ ይነገራል ይህም የሆነበት ምክንያት በወቅቱ በነበረው የፖለቲካ ችግን ልዩን የጀርመን ግዛት ተዘግታ በንጉሡ ፉሬድሪክ ሁለተኛ ተዘግታ ስለነበር ነው፡፡በጉባኤው 22 ምዕራፍ ያካተተ ውሳኔ ተላልፉል፡፡
በዚህ ጉባኤ ላይ ከግሪክቤተ ከርስቲያን ጋር በመስማማት ወደ ቀደመ አንድነታቸው ለመምጣት ጥረት የተደረገበት ነው፡፡ ነገር ግን በወቅቱ የነበሩት ነገሥታት በማስፈራራት በስምንት ቀናት ውስጥ የፖፑን ሐሳብ እንዲቀበሉ ግድ አሏቸው፡፡ ግሪክ ቤተ ክርስቲያንም የተወከሉ አባቶች ይህንን አልቀበልም በማለታቸው እንደቀድሞ እስካሁንም ድረስ ተለያይተው ይኖራሉ፡፡
ይህ ጉበኤ ስለሰው ነፍስ ዘለዓለማዊነት የተወሰነበት ጉባኤ ነው፡፡ ካቶሊካዊያኑ ስለሰው ነፍስ ያላቸው አቋም ምን እንደሚመስል ማሳወቁ እዚህ ጋር ጠቃሚ ሳይሆን አይቀርም አንዲህ የምናሊ ‹‹Every spiritual soul is created immediately by God-it is not <> by the parents>> በማለት ለእያንዳንዱ ጽንስ አዲስ ነፍስ ወዲያውኑ እንደሚፈጠርላት ያስተምራሉ፡፡ creationism የሚባለው አስተምሕሮ ይህ ነው፡፡
የመንፍቅንኑን በስም ሳይጠቀስ ይህን ውሳኔ አሳልፏል ‹‹ሰዎች በቅድስና መለወጥ ይገባቸዋል እንጂ ቅድስና በሰዎች አይለወጥም››[2] የሚል ጉባኤው ሌሎች የቀኖና ማሻሻዎችን አድርጓል፡፡
ጉባኤ ተረንት
በዚህ ወቅት በተሐድሶያኑ ሰፊ ዘመቻ የተካሄደበት ወቅት በመሆኑ በመሠረተ እምነት ላይ ሰፊ ውይይትና ውሳኔ አሳልፈዋል፡፡
*      ስለትውፊትና ባሕል
*      ስለምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን
*      ስለቅዱስ ቁርባን
*      ስለነገረ ድኅነት
*      ስለቅዱሳን አማላጅነትና የመጽሐፍ ቅዱስ ቀኖናን በሚመለከት በሰፊው ተወያይቶ  ውሳኔንን አሳልፎል፡፡

የመጀመርያው የቨቲካን ጉባኤ
ይህ ጉባኤ የካቶሊክን እምነት ምንነት የፖፑን ሥልጣንና ፖፑ ፍጹም ከስሕተት የጸዳ መሆኑን በዚህ ጉባኤ ላይ ውሳኔ አሳልዋል፡፡
ይህ ጉባኤ ምንፍቅናን ለማውገዝ የተሰነበሰበ አይደለም፡፡ በወቅታዊ ሁኔታች ላይ ተወያይቶ ውሳኔውን ያሳልፏል፡፡ከሌሎች የክርስትና ክፍሎች ጋር ሊኖር ስለሚገባው ግንኙነት ስለቅዱሳት መጻሕፍት እና ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ተወያይቷል፡፡
በዚህ ጉባኤ 1870 ዓ.ም. ቫቲካን አንድ ጉባኤ ላይ የተወሰነው ፖፑ ፍጹም አይሳሳትም የሚለውን ሐሳብ በዚህ ጉባኤ ተነስቶ ዳግመኛ አጽንተውታል፡፡
ለአብያተ ክርስቲያናት መለያያት ምክንያት የሆኑ ጉባኤያት
ለጥንታዊያን ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት ማለትም እስክንድርያ(ኢትዮጵያና ኤርትራን ይጨምራል) ሶርያ ሕንድና አርመን የጉባኤውን ሐሳብ በመቃወም በኃይልና በማስፈራራት ከጉባኤው እንዲወጡ በመሆኑ ለአብያተ ክርስቲያናቱ መለያየት ምክንያት ሆኖል
2.      ጉባኤ ቁስጥንጥንዩስ አራተኛ
ይህ ጉባኤ ለሁለቱ ቤተ ክርስቲያን ክፍፍል መፈጠር እንደመነሻ የሚታይ ነው ይህም በዚህ ጉባኤ ላይ የተነሳው የመንፈስ ቅዱስ ከአብና ከወልድ የሰረጸ ነው የሚለው ትምህርት ነው ይህ ትምህርት ከዚህ በፊት ያልነበረ ስርዋጽ ነውና ይህን በመቃወም የምሥራቅ አብያተ ክርስቲያናት የሮም ቤተ ክርስቲያን ፖፕን ወቀሱ መናፍቅ ነህም አሉ፡፡ በዚህም ምክንያት ጉባኤው ተደረገ የሮም ቤተ ክርስቲያን መሪ ነችና የእኛ ሐሳብ ያደመጥ አለች ይህንን ምሥራቃውያን ተቃወሙት ፓፕ ኒኮላስም በዚህ ጉባኤ ላይ የስሕተት ትምህርቱን አጸደቀው፡፡ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን እስካሁን ድረስ ዘሰረጸ እምአብ ወእም ወልድ ብለው ያስተምራሉ፡፡

ጉባኤው የተደረገበት ዘመን

ጉባኤ

የጉባኤው መግለጫ

የጉባኤውን ውሳኔ ተከትሎ

451
ኬልቄዶን
         ምንታዌ     
ጥንታዊያን አብያተ ክርስቲያናት
870
አራተኛው ቁስጥንጥንያ
መንፈስቅዱስ ከአብና ከወልድ የሚሰርጽ መሆኑ የወሰነበት ጉባኤ[3]
የምዕራብ አብያተ ክርስቲያናት
መለካዊያኑ በቅድመ ስማቸው የቀጠሉ ሲሆን በ1054 ዓ.ም. ከምዕራባዊያኑ ካቶሊካዊያን ተገንጥለዋል፡፡ ይህም የሆነበት ምክንያት በዋነኝነት ካቶሊካዊያኑ መንፈስ ቅዱስ ከአብና ከወልድ የሰረጸ ነው የሚለውን ትምህርት በማስተማራቸው ይህንንም የቁስጥንጥንያ ቤተ ክርስቲያን በመቃወሟ ነው፡፡ ነገር ግን እስካሁን ድረስ ሁሉት ባሕርይ የሚለውን ትምህርት የሚቀበሉ በመሆናቸው ከጥንት ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት በመሠረተ እምነት ደረጃ ልዩ ብያደርገንም በነገረ መለኮት አረዳድ ባሕል ግን በብዙ የምንቀራረብ ነን፡፡






[1] The Council formally repeated Catholic teaching, that Christ is present in the Eucharist and thus clarified transubstantiation.
[2] People must be transformed by holiness not holiness by the pepole
[3] Pop Nicholas l say I had refused to recognize Patriarch I of Constantinople who attached the pop as a heretic.because the pop teach the concept of Filioque(holy sprit emanating from God the father and the son

No comments:

Post a Comment