ሀልዎተ እግዚአብሔር
የእምነታችን መሠረት የእግዚአብሔር መገለጥ ነው፡፡እግዚአብሔር ከፍጥረታቱ
የራቀ የማይገለጥ በርቀት በርእቀት ያለ አምላክ አይደለም፡፡ በእምነት ለሚፈልጉት የሚገለጥ ቅርብ አምልክ ነው እንጂ፡፡ ሐዋርያው
ቅዱስ ጳውሎስ በመልዕክቱ ‹‹ከጥንት ጀምሮ እግዚአብሔር በብዙ ዓይነትና ብዙ ጎዳና ለአባቶቻችን በነቢያት ተናግሮ ነበር›› (ዕብ
1÷1)
የእምነት መሠረት ሀልዎተ ፈጣሪ ወይም በፈጣሪ መኖር ማመን ነው፡፡
ዓለማችን የእግዚአብሔር መኖርን በተመለከተ በዋነኝነት ሦስት አመለካከቶችን ታራምዳለች፡፡
- በፈጣሪ መኖር የሚያምኑ(Theism)
- በፈጣሪ መኖር የማያምኑ(Anteism)
- የፈጣሪ መኖር ግድ የማይሰጣቸው(አይሰጠንም የሚሉ) (Agnostics)
በፈጣሪ መኖር የማያምኑ በተለያየ ዘመን የተነሱ ፈላስፎች ሳይንቲስቶች
ፖለቲከኞች ሳይኮለጅስቶች ፈጣሪ የለም የሚለው እምነት ማራመዳቸው ቢያመሳስላቸውም እምነታቸውን በተለያየ አቀራረብ የሚከተሉና የተለያየ
አመለካከት ያራምዱ ነበር፡፡ ለአንዳንዶች ይህች ዓለም ፍትሕ አልባ መከራና ችግር የበዛባት ናትና በፈጣሪ የለም ይላሉ፡፡ ለአንዳንዶች
ፈጣሪ በሰው አእምሮ ወይም በሰው ጭንቀትና ብቸኝነት (ፍርሃት) ምክንያት የመጣ ነው ይላሉ፡፡
የፈጣሪ መኖር ግድ የማይሰጣቸው (አይሰጠንም የሚሉ)
(Agnostics) አሉ፡፡ እነዚህ ስለፈጣሪ መኖር አለመኖር አይገደንም ፈጣሪ ቢኖርም ባይኖርም ዓለም እንዲሁ ትቀጥላለች ስለዚህም
በዚህ ዙርያ መጨነቅና መከራከር የለብንም የሚሉ ናቸው፡፡
በዚህ ሀልዎተ እግዚአብሔር ክፍለ ትምህርታችን በአጠቃላይ ስለ እግዚአብሔር
መኖር ቅዱሳት መጻሕፍትና ሌሎችን ማስረጃዎች እየጠቀስን የምንምማርበት ነው፡፡ በመጀመርያ ሰው የሚታየውንና የማይታየውን ዓለም ከምን
ተገኘ መሠረቷና ድዷስ እንዴት ጸኑ እንደ እምነቱ ከሆነ ተመራማሪዎቹ በአዝጋሚ ለውጥ ተገኘ የሚሉት የመጀመርያው ነገር ከምን ተገኘ
አሁንስ ክረምት ከበጋ ቀን ከሌሊት ሙቀት ከብርድ የሚያፈራርቅ ማነው ሌሎችስ ብርሃናትንስ በጨለማ ብቻ እንዲሰለጥኑ ማን አደረገ
አንዳንድ ሰዎች ሰው ቀስ በቀስ እንደቆመ ሄደ ይላሉ ለመሆኑ ሰውን እያዩና ሰውም እንያሰለጠናቸው ያሉት እንስሳት ለምን ቆመው አይሄዱም
ይህ ሁሉ የኑሮ ሕግ እንዲጣረስ ያደረገው ምንድር ነው እነዚህ ሁሉ ወደ አንድ አቅጣጫ ያመራሉ አንድ ኃይል ስለመኖሩ
ሀልዎተ እግዚአብሔር የሚታወቅባቸው ነገሮች
ብዙዎች በተለይም ቁስ አካላውያን ተፈላሳፊዎች14 እግዚአብሔር መኖሩን በምን እናውቃለን ይላሉ፡፡
አባባላቸው ካላየን አናምንም ነው፡፡ ነገርግን እግዚአብሔር ረቂቅ አካልና ባሕርይ ያለው በመሆኑ ለቁስአካል ወይም ለግዙፍ ሰው አይታይም፡፡
እግዚአብሔርን የምናየው በእምነት ብቻ ነው፡፡ ነገር ግን የእግዚአብሔርን መኖር ማረጋገጫ ለሚፈልጉ በሚከተሉት ነገሮች ማረጋገጥና
መረዳት ይችላሉ፡፡
እግዚአብሔር በሥነፍጥረቱ ይታወቃል
ለፍጥረት ሁሉ አስገኚ አላቸው፡፡ለስዕል ሠዓሊ፣ ለመጽሐፍ ጸሐፊ፣
ለወንበር ጠራቢ አለው፡፡ ለሚንቀሳቀስ ሁሉ አንቀሳቃሽ አለው፣ ለፍጥረትም ሁሉ ፈጣሪ አለው፡፡ ይህም እግዚአብሔር ነው፡፡ (ጥበብ 13፥1-10)
መዝ 99፥6 “ይነግራ ሰማያት ጽድቀ ዚአሁ” ሰማያት አንድም በሰማይ ያሉ ደቂቀ መላእክት
ቸርነቱን ይናገራሉ በማለት የእጁ ሥራ የሆኑ ሰማያትም ሆነ መላእክት የእግዚአብሔ መኖር መታወቂያዎች መሆናቸውን ይገልጽልናል፡፡
መዝ18፥1 ‹‹ሰማያት የእግዚአብሔርን ክብር ይናገራሉ የሰማይም ጠፈር የእጁን
ሥራ ያወራል፡፡››
“…….አሁን ግን እንስሶችን ጠይቅ የሰማይ ወፎች ጠይቅ ይነግርሃል ወይም ለምድር ተናገር እሷም ታስተምርሃለች የባሕር
አሳዎችም ይነግሩሃል፡፡ የእግዚአብሔር እጅ ይህን እንዳደረገ” ኢዮ12፥7 በማለት ፍጥረታትን በመመርመርና አፈጣጠራቸውን በማስተዋል ፈጣሪ
እንዳላቸው መጽሐፍት ይመሰክራሉ፡፡ (ሮሜ1፥20) በተጨማሪ ተመልከት፡፡
ፍጥረታቱን ማን አስገኘ የሚለው ብቻ ሳይሆን ለእጁ ሥራ ለሆነውን
ለእኛ አስተካክሎ ፈቃዳችንን በመፈጸሙ ቀንና ሌሊትን፤ ዘመናትን፤ወራትን በመቀያየሩ ለዚህ ዓለም አንድ መጋቢ ሠራዒ እንዳለው ያሳያል፡፡
እግዚአብሔር ፍጥረታትን ሁሉ በመመገቡ በመጋቢነቱም ጭምር ይታወቃል፡፡ (መዝ 18፥1-3 ፤ ሮሜ 1፥20)
የሕሊና ዳኝነት(ምስክርነት)
የሰው ልጅ በተፈጥሮው መልካም ካደረገ ልዩ ደስታን የመንፈስ እርካታን
ያገኛል፡፡ መጥፎ ሲሰራም ደግሞ ያዝናል ሕሊናውም ይወቅሰዋል፡፡ ይህ በጎ ለሚሰሩ ዋጋ የሚሰጥ ለክፉዋች ደግሞ የሚቀጣ ፈጣሪ እንዳለ
ያስረዳናል፡፡አብነትም አይሁድን ያስጨፈጨፈውና ከቤተ መቅደስ ብዙ ንዋያትን የዘረፈው አንጥያኮስ ‹‹ከዓይኖቼ እንቅልፍ እየተፋና ልቤም እየደነገጠ
ነው፡፡ በሥልጣን ዘመኔ በጣም ቸርና ተወዳጅ የነበርኩት እኔ ለምን አሁን እንዲህ ያለ ታላቅ ጭንቀት ደረሰብኝ ብዮ ራሴን በጠየቅሁት
ጊዜ በኢየሩሳሌም የፈጸምኩትን በደል ማስታወስ ጀመርኩ፡፡ የበሩንና የወርቁን ዕቃዎች የወሰድሁትና የይሁዳ ሕዝብመም እንዲፈጅ ትዕዛዝ
ያስተላለፍኩት ያለምንም ምክንያት ነበር፡፡ ይህ አሁን በባዕድ ሀገርና በጭንቀት የመሞት ዕድለ ቢስነት ያጋጠመኝ በፈጸምኩት በደል
ለመሆኑ እርግጠኛ ነኝ፡፡›› 1ኛ መቃ. 6÷10-13 ቅዱስ ጳውሎስም ‹‹ሕግ የሌላቸው አህዛብ ከባሕርያቸው የሕግ ትዕዛዝ ሲያደርጉ እነዚያ ሕግ ባይኖራቸው እንኳ ለራሳቸውና
ሕግ ናቸውና እነሱም ሕሊናቸው ይመሰክርባቸዋል፡፡ ሐሳባቸው እርስ በርሳቸው ሲካሰስ ወይም ሲያመካኝ በልባቸው ተጻፈውን የሕግ ሥራ
ያሳያሉ፡፡›› ሲል ቅዱስ ጳውሎስ ተናግሯል፡፡ (ሮሜ 12፥14-15) ጥህም ሕግ ያልተጻፈላቸው እንኳ በሕሊናቸው ዳኘነት መልካም ስራ ሲሰሩ ማየታችን ሰውን አዋቂ አድርጎ የፈጠረ
አንድ አምላክ መኖሩን ያስረዳናል፡፡
የሰው ልጅ የተፈጥሮ ዝንባሌ
ሰው በተፈጥሮ ረዳት ፈላጊ ነው፡፡ እነዚህ ነገሮች ቢኖሩኝ ብሎ
የተመኛቸውን ሁሉ ቢያገኝ ሌላ የሚመኘው አያጣም፡፡ ይህም ጎደሎና ረዳት የሚያስፈልገው ጎዶሎውን የሚሞላለት ሌላ ረዳት ፈላጊ መሆኑን
ያረጋግጣል፡፡ ምንም እገዚአብሔርን ባያውቅና ባያምነው በኑሮው ግን ሁልጊዜ ይህንe የማይደክም የማይሸነፍና የፈለጉትን ሊሰጥ የሚችል
ረዳት ወይም አምላክ ይፈልጋል፡፡
በዓለም ላይ የሚገኙ ልጆች የአምልኮት ሥርዓታቸው ቢለያይ ነው እንጂ
ፈጣሪ መኖሩን ያምናሉ፡፡ እግዚአብሔር መኖሩን የሃይማኖት መጻሕፍትን ተረድቶ ብቻ ሳይሆን ተፈጥሮአዊ ስሜቱ ወይም ዝንባሌው ስለሚገፈፋፋው
ጭምር ነው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ በአቴና ውስጥ
አሪዎስፋጎስ በተባለ ጣኦት ቤት ውስጥ ‹‹ለማይታወቅ አምላክ›› ተብሎ የተጻፈውን መነሻ በማድረግ ብዙ ሰዎችን
አሳምኖእንዳጠመቀ ተጽፎ ይገኛል፡፡(ሐዋ 17፥22-34)
መጽሐፍ ቅዱስ
መጽሐፍ ቅዱስ የሚጀምረው የሰማይና የምድር ፈጣሪ ማን እንደሆነ በመግለጽ
ነው፡፡ በመጀመርያ እግዚአብሔር ሰማይና ምድርን ፈጠረ ብሎ ፈጣሪ ዓለማት እግዚአብሔር መሆኑን ይገልጣል፡፡ እስከፍጻሜውም መጋቢነቱት
ቸርነቱን ፈጣሪ ዓለማትነቱን ይገልጻል፡፡ ስለዚህም ለእግዚአብሔር መኖር በአስረጅነት የሚገለጽ ነው፡፡
ሀልዎተ ፈጣሪ ላይ ሰዎች የተለያየ አመለካከት አራምደዋል ከእነዚህ መካከል ጥቂቶቹን እንመልከት
የታለስ ፍልስፍና
ታለስ የመጀመርያ ፈላስፋ እንደሆነ ይነገርለታል፡፡ እንደ እርሱ
አሳብ ከሆነ ፍጹም እውነት ውኃ ነው፡፡ ይህንንም ሲያስረዳ ውኃ ለሁሉ ፍጥረት ያስፈልጋል፡፡ ውኃነት የሌለው ፍጥረት የለም እርሱ
ከመሬት ወደ ሰማይ ቢተንም አይቀርም ይመለሳል ዘርን የሚያበቅላል ሙቀትን የሚያስገኝ መሬት የተነጠፈች በእርሱ ላይ ነነው ፡፡ ከዚህም
በላይ በሦስት ሁኔታወች ማለትም በጠጣርነት በጋዝነት በፈሳሽነት የሚገኝ በመሆኑ ውኃ ፍጹም እውነት ነው ይል ነበር፡፡ ነገር ግን
ውኃ በራሱ የሚገኝ አይደለም ማን አሰገኘው ብንል መልስ አይሰጠንም፡፡
እነሶቅራቶስና ፕላቶ ስሙን አይጥሩት እነጂ ሁሉን ያስገኘ ሁሉን
ጠብቆ የሚኖር አንድ ወይም ብዙ የማይታወቁ አማላክት አሉ ብለው የታየስን ፍልስፍና ያጣጣሉት፡፡
የኒዝቼ አስተሳሰብ
ይህ ሰው ደግሞ በ1960ቹ እንደፈረንጆች አቆጣጣር የነበረ ሲሆን አምላክ
በባሕርው ሞቷል ብሎ ያስተማረ ነው፡፡ አማላክ በባሕሪው ከሞተ አምላክ ማለት ምን ማለት ነው ራሱን ሊያድን የማይችል ሌሎች ፍጥረታትን
እንዴት ሊያድን ይችላል፡፡
የቶማስ አኩናስ ማረጋገጫ
ለእግዚአብሔር መኖር አምስት ማረጋገጫዎችን ያስቀመጠ ነው
- ዓለም ወይም ጊዜና ቦታ አለ
- ራሱ አስገኝ ሊኖን አይችልም
- እምኀበ አልቦ ሊገኝ አይችልም
- መነሸና መድረሻ በሌለው ተከታታይ ድርጊትና ውጤት የጸና አይደለም
- ስለዚህ ለራሱ ምክንያት በሌለው(ባልተፈጠረና) ፍጹም ከቦታ ጊዜ ውጭ በሆነ የተፈጠረ የተገኘ መሆን አለበት
ሌሎች ፈላስፎችም ሀልዎተ እግዚአብሔርን በተመለከተ የየራሳቸው ወይም አመክንዮ
ቢያቀርቡም አብዛኞቹ በፈጣሪ መኖር ላይ ይስማማሉ፡፡ የብዙ ፈላስፎችን
ጥናት ያቀረበው ሚለር እርግጥ
ነው እግዚአብሔር አለ በማለት
ለማስቀመጥ የተገደደው ከዚህ የወጣ ፍልስፍና ባለመኖሩ ነው፡፡
ይቆየን
ይቀጥላል
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
No comments:
Post a Comment