Monday, 24 July 2017

ነገረ ሃይማኖት ክፍል ሃያ ስድስት



ስለቁርባን የሌሎች ትምህርትና የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ትምህርት
መታሰቢያ አደርጉት
ቅዱስ ቁርባንን በሚመለከት በዓለም የሚገኙ የሃይማኖት ተቋማት ወይም ግለሰቦች የተለያየ አቋም ሲያራምዱ ይስተዋላል፡፡ እኛም ትምህርታቸውን በሦስት ዓበይት ክፍሎች ከፍለን ማየት እንችላለን
1. Transubstantial
2. Consubsrantial
3. Simple memory ይባላሉ

Transubstantial (ትራንሳብስንሻል)
የመጀመርያው ትራንሳብስንሻል የሚለው ይህ ሥጋየ ነው ይህ ደሜ ነው ከሚለው መጽሐፍ ቅዱሳዊ የወንጌል መሠረት በመነሳት የክርስቶስ ሥጋና ደም መታሰቢያ ሳይሆን አማናዊ ነው፡፡ የክርስቶስ ሥጋና ደም አማናዊ መሆኑን የምሥራቅ ኦርቶዶክሶች የጥናታዊያን ኦርቶዶክሳዊያን ቢቀበሉትም ይህንን ቁርባን ልክ እንደካቶሊካዊያን ጠለቅ ያለ ማብራርያ ከመስጠት እንቆጠባለን በእምነትም እንቀበላለን፡፡
የቶማስ አኩዊነስ ትምህርትና ትራንሳብስንሻል
1215 .. በላተርን ጉባኤ ከጸደቁ ነገረ መለኮታዊ ጉዳዩች መካከል ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን አሁን ድረስ በቅዱስ ቁርባን ላይ የምታራምደው ትምህርት ነው፡፡ ይህም ትምህርትቶማስ አኩዊናስ ትምህርት ነው፡፡ ምንጩ የአርስቶትል ፍልስፍና ነው ቢባልም እነርሱ ግን ከፍልስፍናው ብዙ የራቀ ነው ይላሉ ትምህርቱ ትራንስሰብስቴንሽን ይባላል፡፡ ይህ ጠለቅ ያለና ቅዱስ ቁርባንን በሚመለከት ሰፋ ያለ ትንታኔ የሚያቀርቡበት ነው፡፡ ትራንስሰብስቴንሽን በላተርን እንዲሁም በትሬንት ጉባኤ ውሳኔ መሠረት ‹‹በጸሎት አማካኝነት ኅብስቱ ተለውጦ ሥጋውን ወይኑ ተለውጦ ደሙን ይሆናል ኅበስቱ ብቻውን ወይም ኅብስቱና ወይኑ ወደ ክርስቶስ ሥጋና ደም ይለወጣል ክርስቶስ በቅዱስ ቁርባኑ ላይ ይገኛል በኅብስቱ ቅንጣት ላይም ቢሆን ወይም በወይኑ ጠብታ ላይም ቢሆን ይገኛል፡፡ ነፍስ የተለየው ሳይሆን ነፍስ ሥጋ መለኮት የተዋሐደው ነው፡፡ እንዲሁም ኅብስቱና ወይኑ የገጽታ ለውጥ ሳያደርጉ ወደ ሥጋና ደሙ ይቀየራሉ ይላል፡፡ ሰብስታንስ(ንጥረ ነገር) በውስጡ ያለውን ነገር የሚጠቀልል ነው፡፡ ለምሳሌ ለኮፍያ ሰብስታንሱ ቀለሙ ቅርጹ ወይም ስፋቱ አይደለም ሰብስታንስ(ንጥረ ነገር) ራሱ ኮፍያው ነው፡፡ ይህ ንጥረ ነገሩ በዚህ አግባብ ቁርባኑ ይለወጣል ይቀየራል ይላል ይህ ትምህርት፡፡
ይህንን በሚመለከት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በቅዳሴ ጸሎት ጊዜ ‹‹ኅብስቱ ተለውጦ ሥጋ መለኮት ወይኑ ተለውጦ ደመ መለኮት ይሆናል፡፡›› ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ይህን ትምህርት ለማስተማር ከምትጠቀምባቸው አገላለጾች አንዱ ነፍስ የተለየው መለኮት የተዋሐደው የሚል ነው፡፡ ይህም የሚለወጠው ነፍስ የተለየው መለኮት ደግም የተዋሐደው ነው ይህም ትምህርት ከካቶሊካዊያኑ ትምህርት ይለያል፡፡ ኦርቶዶክሳዊያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብስቱ ተለውጦ ሥጋ መለኮት ወይኑ ተለውጦ ደመ መለኮት ይሆናል ይበሉ እንጂ እንዴት ሆኖ ይሆናል ኅብስቱና ወይኑ በሥጋና ደም መልክ ይገለጻሉ ወይስ ሥጋና ደሙ በኅብስቱና ወይኑ ይገለጣሉ የሚለውን ትንታኔ ምኑ ይቀየራል የሚለውን ትምህርት ጠለቅ ባለ ሁኔታ አታስተምርም፡፡ መደምደምያችን ይህ ሁሉ ምሥጢር ነው የሚል ነው፡፡ የዚህም ምንጩ በምዕራፍ ሁለት ላይ ያየነው የነገረ መለኮታችን ጠባይ ነው፡፡ ከፍልስፍና ይልቅ እምነትን ከሳይንስ ይልቅ ለቅድስና ትኩረት ስለምንሰጥ ነው፡፡
ኦርቶዶክሳዊያን አብያተ ክርስቲያናት ግን በቅዳሴው ጊዜ ‹‹ኅብስቱ ተለውጦ ሥጋ መለኮት ወይኑ ተለውጦ ደመ መለኮት ይሆናል፡፡›› የሚለውን ትምህርት ትቀበላለች፡፡ ጌታችንም ‹‹ ኅብስቱን ባርኮ ይህ ሥጋሄ ነው ጽዋውንም አንስቶ ይህ ደሜ ነው›› ማለቱን በማስታወስ የጌታ ሥጋና ደም መሆኑን ትሰብካለች(ማቴ 2626 ማር 1438 1 ቆሮ 1124 ሉቃ 227-20)
Consubsrantial (ኮንሳብስንሻል)
የዚህ ትምህርት መነሻ በአንደኛ ቆሮንቶስ 1124-25 ላይ ያለው የቅዱስ ጳውሎስ የመልእክት ሐሳብ ነው ቅዱሱ በዚህ መልእክቱ ‹‹መታሰቢያ›› ስለሚል ይህንን በመጥቀስ አማናዊ አይደለም፡፡ ነገር ግን ሥጋ ወደሙ ጸጋ በረከት አለበት ጸጋ በረከት ያሰጣል ቢሆንም አማናዊ አይደለም፡፡
Simple memory (መታሰቢያ)
ስተኛው አስተሳሰብ ደግሞ የሉተር ጥርጥር ቀጥሎም የካሊቨኖች አስተሳሰብ ነው፡፡ ይህም የጌታ ሥጋና ደም መታሰቢያ የሚል አስተሳሰብ አራማጆች ናቸው፡፡
የቅዱስ ቁርባን አማናዊነት
ዛሬ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የምትሠዋው ሕብስትና ወይን ካህኑ በጸሎተ ቅዳሴ ጊዜ ሲባርከው ፍጹም በዕለተ ዓርብ በመስቀል ላይ የተሠዋው የክርስቶስ አማናዊ ሥጋና አማናዊ ደም ወደ መሆን ስለሚለወጥ ፍጹም አማናዊ ነው እንጂ ምሳሌያዊ የሆነ መታሰቢያ አይደለም፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ በሉቃስ ወንጌል በምዕ 22 20 ላይ ለመታሰቢያዬ አድርጉት ስለሚለው ገጸ ንባብ የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ እንደዚህ ይላል፡፡
ለመታሰቢያ አድርጉት ምን ማለቱ ነው
እንጀራም አንስቶ አመሰገነ ቆርሶም ሰጣቸውና ስለ እናንተ የሚሰጠው ሥጋዬ ይህ ነው ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት አለ” (ሉቃ 22-20) መታሰቢያ ማለት ማስታወሻ ማለት ነው፡፡ ይህም ማለት በቁርባን ጊዜ ሕማሜን' ሞቴን ትንሣኤዬን አስታውሱ ሲል ነው(1 ቆሮ 11÷-26-27) ‹‹ይህንን ሕብስት በምትበሉበት ጊዜ እና ይህን ጽዋ በምትጠጡበት ጊዜ ሁሉ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እስከሚመጣበት ጊዜ ሞቱን ትናገራላችሁ›› ለዚህ ነው በቅዳሴ ጊዜ ንዜኑ ሞተከ እግዚኦ ወትንሣኤከ ቅድስተ ነአምን ዕርገተከ ወዳግመ ምጽአተከ የምንለው፡፡
መታሰቢያ የሆነ ነገር አማናዊነትን አያጠፋም

እስራኤል ዘሥጋ በምድረ በዳ የበሉት መና በቤተ መቅደስ እንዲቀመጥ የልጅ ልጆቻቸው አባቶቻችን በምድረ በዳ የመገበ አምላክ እያሉ እንዲያስተውሉ ለመታሰቢያነት ተቀምጦ ነበር፡፡ በቤተ መቅደስ የተቀመጠው መና ትክክለኛ አማናዊ ነበር እንጂ ለመታሰቢያ በዚያ በመቀመጡ ከሰማይ የወረደ መና መሆኑን አያስቀረውም፡፡ አሮን በእጁ የሚይዛትን ተአምራት ያደረገባት በትሩ ለመታሰቢያነት/ለሚያምጹ/ ልጆች ምልክት ሆና ትቀመጥ ተብላ ተቀመጠች፡፡ የዚህች በትር ለመታሰቢያነቱ መቀመጥ አማናዊነቱን አላጠፋውም የአሮን በትር መታሰቢያ መሆኑ ያጎደለበት ክብር የቀነሰበት ነገር አልነበረም( ዘጸ 16÷32 ዘኁ 17÷10)
በምሣሌ ያስተማረው አይደለም
ጌታ በምሣሌ ያስተምርና ግልጽ ካልሆነላቸው ያብራራላቸው ነበር ለምሳሌ፡-
U  ማቴ 15÷16-17 ሰውን የሚያረክሰው እጅ ሳይታጠብ መብላት ሳይሆን ከአፍ የሚወጣ ክፉ ንግግር መሆኑን
U  ከፈሪሳውያን እርሾ ተጠበቁ ሲል ከፈሪሳውያን ክህደት እርሾ ተጠበቁ እንጂ ከእንጀራ እርሾ አለመሆኑን
o ዳግመኛ ተወለዱ ሲል ዳግመኛ ከእናታችሁ ማህጸን ተወለዱ ማለቱ ሳይሆን ከውሃና ከመንፈስ ተወለዱ ማለቱ እንደሆነ አስረድቷል፡፡

ጌታ ስለ ምሥጢረ ቁርባን እውነተኛነት ሲያስተምር የሚያስጨንቅ ንግግር ነው ማን ሊሰማው ይችላል; በማለት ከደቀ መዛሙርቱ ብዙዎች እርሱን ከመከተል ወደ ኋላ ባሉ ጊዜ በሚያስተምረው ትምህርት ላይ ተጨማሪ እውነተኛነቱን በማጠናከር አስተማረ እንጂ ከዚህ በፊት እንደሚመስላቸው ምሳሌዎች አልተረዱም ግልጽ አልሆነላቸውም ብሎ ተጨማሪ ትንታኔ አልሰጠበትም፡፡
ማጠቃለያ
U  ቅዳሴ ሲጀመር ያልነበረ ሰው አይቆርብም፡፡ ቅዳሴ ሲጀመር ያልነበረ ካህንም እንደዚሁ ሥጋ ወደሙን ሲቀበል ሆነ ሊያቀብል አልተፈቀደለትም፡፡
U   በንስሐ ያለ ሰው የንስሐ ጊዜውን ሳይፈጸም ለሞት የሚያበቃ ደዌ ቢታመም ሥጋ ወደሙን ከመቀበል አይከለከልም፡፡
U   መሥዋዕት የሚሠዋው ቅዳሴም የሚቀደሰው በኤጲስ ቆጶስ ፈቃድ ተሠርቶ በኤጲስ ቆጶሱ ተባርኮ በተጀመረ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ነው፡፡
በቤተ ክርስቲያን የሚሠዋው የጌታ ሥጋና ደም እውነተኛ በዕለተ ዓርብ በመስቀል ላይ የተሠዋው ራሱ የክርስቶስ ሥጋና ደም ነው፡፡ ራሱ ባለቤቱ ሕብስቱንይህ ስለ ብዙዎቹ የሚቆረስ ሥጋዬ ነውበማለት አረጋግጧልና፡፡ (ማቴ 26÷26)
ይቆየን ይቀጥላል
ስብሐት ለእግዚአብሔር

No comments:

Post a Comment