ምሥጢረ ሥላሴ
የቅድስት ሥላሴ መሠረተ እምነት
ለክርስቲያን ሁሉ የምሥጢረ ሥላሴን ነገር ጠንቅቆ ማወቅ ይገባል፡፡ ይህን የአባቶች ትምህርት በሚገባ
መረዳት ከመናፍቃኑ ትምህርት ለመጠበቅ ወሳኝ ነው፡፡ የነገረ ሥላሴን ያልተረዱ መናፍቃን በተለያየ ወቅት ተነስተው ክህደት ቢዘሩም
አባቶች ከመጻሕፍት እየጠቀሱ በምሳሌ እየተነተኑ እረተዋቸዋል፡፡ ሰባርዮስ የተባለው መናፍቅ እግዚአብሔር ፍጹም አንድ አምላክ እንጂ
ሦስትንት የለበትም አለ በተለያየ ወቅት ተገለጠ እንጂ አንድ ነው አለ እንደ አብ በብሉይ እንደወልድ በሐዲስ እንደ መንፈስ ቅዱስ
በዘመነ ሐዋርያት ይህ ነገረ ሥላሴን ካለመረዳት ነው፡፡ አምላክ ሁለት ነው ያሉም አሉ አንዱ በሰማይ አንዱ በምድር ይገዛል ብለው
ተነስተዋል፡፡ አንድም ባዕል አምላክ ነዳይ ብለው ከፍለውታል ባለጸጋው ባለጸጎችን ፈጠረ ድኃው ነዳያንን ፈጠረ ብለው አስተምረዋል
ሊቃውንትም ከመጻሕፍት ጠቅሰው ረተዋቸዋል፡፡ዳግመኛም ሦስት አማልክት ያሉ ተነስተዋል ሠናይ አምላክ እኩይ አምላክ ራትዕ ብለው ተነስተው
ነበር፡፡ ሠናይ አምላክ እንልማ ይላል እኩይ እናጥፍ ይላል ራትዕ አንተም ተው አንተም ተው ይላል ብለዋል አባቶችም ይህን ከመጻሕፍት
ጠቅሰው አስረድተዋል፡፡ አራት አማልክት ያሉ አሉ የአብ አባት አለው ብለው አንድም ከእግዝእትነ ማርያም የተወለደው ክርስቶስን አራተኛ
ብለው ሊቃውንት ከመጻሕፍት ጠቅሰው ረተዋቸዋል፡፡ ዳግመኛም ሰባት አማልክት አሉ የሚሉ መናፍቃን ለዕለታት ሁሉ አንድ አንድ አማልክት
አሏቸው ብለው አስተምረዋል ሠላሳም ያሉ አሉ ከመባቻ እስከ መባቻ አማልክት አሉ ያሉሦስት መቶ ስሳ አምስት ያሉም
አሉ በቀናት ቆጥረው ሰፍረው ይህንንም አባቶች ጠቅሰው ረተዋቸዋል፡፡ እነዚህ ሁሉ ምሥጢረ ሥላሴን ባለመረዳት የመነጨ ነው ፡፡ ከእነዚህ
ለመለየት እንደ እምነታችን መጠን እንደአእምሮችን ልክ ምሥጢሩን መማር ይገባናል፡፡
ምሥጢረ ሥላሴ በኦርቶዶክሳዊያን
ሥላሴ ማለት ልዩ ሦስትነት ማለት ነው፡፡ ልዩ ሦስትነትን ከመረዳታችን በፊት ደግሞ ‹‹ሦስት››ነትን መረዳት ያስፈልጋል፡፡
በሦስት በሦስትነት መካከል ያለውን ልዩነት በሚገባ ከተረዳን የልዩ ሦስትነትን ትርጉም መረዳት ይቻላል፡፡
ሦስት
ሦስት ማለት በቁጥርነቱ(እንደ ቁጥር) ተመሳሳይ ይሁኑ ወይም የተለያዩ በአንድ አካባቢ መኖራቸውን የሚገለጽልን መስተአምር(ቃል)
ነው፡፡ለምሳሌ ሦስት ሰዎች ስንል ሰው መሆናቸው አንድ ቢያደርጋቸውም የተለያዩ አካላት በመሆናቸው የተለያዩ ናቸው ሥስት የቤት እንስሳት
ሲሆኑ ደግሞ የተለያዩ ሆነው በአንድ መሰባሰባቸውን ያመለክተናል፡፡ ለዚህም ነው ተመሳሳይ ይሁኑ ወይም የተለያዩ በአንድ አካባቢ
መኖራቸውን የሚገለጽልን ነው ያልነው፡፡
ሦስትነት
ሦስትነት ማለት አንድነት ላለው አካል የሚቀጽል ነው፡፡ ይህም ማለት ቃሉ አንድነትን ሊያስከትል የሚችል መሆን አለበት ለምሳሌ
ፀሐይ አንድነት አላት(አንድ ናት) ነገር ግን ሦስትነት(ሦስት ነገሮች) አላት ክበብ ብርሃንና ሙቀቱ ነገር ግን ፀሐይ አንድ ናት፡፡
ሌላ ምሳሌ እንጨምር የሰው ነፍስ አንድ ነው ነገር ግን ሦስተነት አለው ለባዊነት(ማሰብ) ሕያዊነት(እስትንፍስ)ና ነባቢነት(ተናጋሪ
ነት) ነፍስ ግን አንድ ነው እንጂ ሦስት አይደለም፡፡
የሦስትነት ምሳሌዎች
የሰው ነፍስ
ሰው በፈጣሪው አርአያና አምሳል የተፈጠረ ስለሆነ ስለሥላሴ ሦስትንትና አንድንትእንዴት እንደሆነ በመጠኑም ቢሆን ከሰው የተፈጥሮ
ባሕርይ ውስጥ በምሳሌነት ልንጠቅሰው የምንችለው ትምህርት አለ፡፡ ሰውም ፈጣሪውን መምሰሉ በነፍሱ እንጂ በሥጋ አይደለም፡፡ምክንያቱም
እግዚአብሔር መንፈስ ነውና፡፡ ሦስቱ የነፍስ ባሕርያት የተበሳሉ ለባዊነት ነባቢነት ሕያውነት ናቸው፡፡ ሰው አንድ ሆኖ ሳለ ሐሳብ
አለው ሐሳቡን የሚገልጽበት ቃል አለው እንዲሁም ቃሉን የሚያዘስተላልፍበት ሕይወት ወይም እስትንፍስ አለው፡፡ እነዚህ ሦስቱ በአንድ
ሰው ላይ ስለሚገኙ አንድም ሦሥትም ሆነው እናያቸዋልን፡፡
እንዲህ በዚህ ምሳሌ የምንረዳው አብ እንደልብ ወለድ እንደ ቃል መንፈስቅዱስ እንደእስትንፍስ ተመስለው ለሥላሴ እንድነትናሦስትነት
ምሳሌ ሆነው ይነገራሉ፡፡
የነፍስ ልብነቷ፣ ቃልነቷና እስትንፋስነቷን ታስገኛለች፡፡ እንዲሁ በልብነቷ የተመሰለው አብ በቃልነቷ
የተመሰለው ወልድን ይወልዳል፡፡ በእስትንፋስነቷ የተመሰለውን መንፈስ ቅዱስን ያሰርጻል፡፡ ነፍስ ስትገኝ በሦስትነቷ በአንድ ጊዜ
ተገኝታለች እንጂ ልብነቷ ቀድሞ ቃልነቷና እስትንፋስነቷ ኋላ የተገኙ አይደሉም፡፡ እንዲሁ አብ ወልድን በመውለዱ መንፈስ ቅዱስንም
በማስረጹ አይቀድማቸውም፡፡ ልብ ቃል እስትንፋስ በመሆን የከዊን ሦስትነት ቢኖራትም አንዲት ነፍስ እንጂ ሦስት ነፍስ አትባልም፡፡
ሥላሴ በስም፣ በአካል፣ በግብር ሦስት ቢሆኑም ሦስት አካል አይባሉም፤ አንድ አምላክ እንጂ ነገር ግን ነፍስ ሦስትነት ቢኖራትም
በአካል አንድ ናት፡፡ ሥላሴ ግን አብ አካላዊ ልብ ነው፣ ወልድ አካላዊ ቃል ነው፣ መንፈስ ቅዱስም አካላዊ እስትንፋስ ነው፡፡ የአካሉ ሦስት መሆን
ባሕርይው አንድ መሆን አካላቱን አይጠቀልለውም፡፡ ስለሆነም ሥላሴ በባሕርይ አንድ በአካል ሦስት ናቸው ብለን እናምናለን፡፡
ፀሐይ
ለፀሐይ ክበብ፣ ብርሃንና ሙቀት አለው፡፡ በክበቡ አብ፣ በብርሃኑ ወልድ፣ በሙቀቱ መንፈስ ቅዱስ ይመሰላሉ፡፡ ክበቡ ብርሃኑን
እና ሙቀቱን ያስገኛል እንጂ ብርሃኑ ሙቀቱንና ክበቡን አያስገኝም፡፡ ሙቀቱም ክበቡንና ብርሃኑን አያስገኝም፡፡
ፀሐይ አንድ ስትሆን ሦስት ነገሮች ስላሏት ሦስት ፀሐይ እንደማትባል ሥላሴም በሥም፣ በአካል፣ በግብር ሦስት ቢሆኑም ሦስት
አማልክት አይባሉም አንድ አምላክ እንጂ፡፡እንዲሁ የመወለድንና የመስረጽን ሁኔታ በፀሐይ ምሳሌነት ማወቅ እንችላለን ከብርሃን አክልና
ባሕርይ ብርሃን እንደሚወጣ ከሙቀት አካልና ባሕርይ ሙቀት እንደሚገኝ እንዲሁም ወለድና መንፈስ ቅዱስ ከአብ መለኮታዊ አካልና ባሕርይ
ይገኛሉ ይወጣሉ፡፡ ይህም ለሥላሴ ምሳሌ ነው፡፡ ከብርሃን የተገኘ ብርሃን ከእውነተኛ አምላክ የተገኘ አምላክ ተብሎ በጸሎተ ሃይማኖት
የጠገለጠው ክፍለ ንባብ ለዚህ አስረጅ ነው (ጸሎተ ሃይማኖት አንቀጽ 3)
የፀሐይ ክብ ከሰማይ እንዳይወርድ አብ ከመንበሩ አይናወጥም፡፡ ብርሃኑና ሙቀቱ ወደ ምድር መድረሳቸው ወልድና መንፈስ ቅዱስ
ወደ ዓለም የመምጣታቸው ምሳሌ ወልድ በከዊን ተዋሕዶ መንፈስ ቅዱስም ኅድረት ተዋሕዶ በዘመነ ሐዋርያት መውረዱን አመልካች ነው፡፡
ምንም እንኳን አብ በተለየ አካሉ ወደ ምድር ባይወርድምከወለድና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ሕልው ሆኖ ይኖራል፡፡
ክበበበ ፀሐይ ብርሃንን ዋዕይን እየላከ መኖሩን ያስታውቃል እንጂ የሚላክ አይደለም፡፡ እንደዚሁ አብ ወለድን መንፈስቅዱስን
እየላከ ሕልውናውን ይገልጻል እንጂ ለማንም የታየና የተገለጸአይደለም(ዮሐ 1÷18)
ያለብርሃንና ሙቀት የፀሐይን ፀሐይነት ማወቅ እንደማይቻል እንዲሁም ያለወልድና ያለምንፈስ ቅዱስ የአብን መለኮትነት ለማወቅ
አይቻልም፡፡
ቀላይ/ባሕር/
ቀላይ/ባሕር/ ሦስት ነገር አለው፡፡ እነዚህም ስፍሐት፣ ርጥበትና ሁከት /የተባለው የባሕሩ እንቅስቃሴ ነው/፡፡ በባህሩ
ስፍሐት አብ በርጥበቱ ወልድ በሁከቱ መንፈስ ቅዱስ ይመሰላሉ፡፡ይህ ሦስት ነገር ያለው ባሕር አንድባሕር እንጂ ሦስት ባሕር እንደማይባል
ሦስት ከዊን ያላቸው ሥላሴም አንድ አምላክ ይባላሉ እንጂ ሦስት አማልክት አይባሉም፡፡
እሳት
እሳት ሦስት ነገር አለው፡፡ እነዚህም ብርሃን፣ ሙቀትና አካል(ክበብ) ነው፡፡ አለው፡፡ በክበቡ አብ፣ በብርሃኑ ወልድ፣
በሙቀቱ መንፈስ ቅዱስ ይመሰላሉ፡፡ ክበቡ ብርሃኑን እና ሙቀቱን ያስገኛል እንጂ ብርሃኑ ሙቀቱንና ክበቡን አያስገኝም፡፡ ሙቀቱም
ክበቡንና ብርሃኑን አያስገኝም፡፡
ሦስትነቶች ለምን ሦስት አያባሉም?
የሦስትነት ምሳሌዎች ሕጸጽ
ታዲያ ሦስትነቶች ለምን ሦስት አያባሉም? የሚለውን ጥያቄ መመለስ በሦስትና በሦስትነት መካከል ያለውን ልዩነት እንድንገነዘብ
ይረዳናል፡፡ምክንያቱም ከሦስቱ አንዱ ለብቻው ማግኘት ስለማይቻል ነው፡፡ ለምሳሌ ከሰው ነፍስ መካከል ለባዊነትን ለብቻ ማግኘት አይቻለንም
ወይም ሕያውነትን ወይም ነባቢነት የማይነጣጠሉ አንድ ናቸው፡፡ሰው እያወቀና እየተናገረ የማይተነፍስ አይደለም፡፡ ወይም እየተነፈሰና
እየተናገረ የማያስብ አይደለም(የተለየ እክል ካልገጠመው በቀር) እንዲሁም እያሰበና እየተነፈሰ የማይናገር አይደለም፡፡(ተናጋሪነት
ሐሳብን መግለጥ ማለት ነው) እንዲሁ ቅድም በምሳሌነት ያነሳነው ፀሐይ ተመሳሳይ ነው፡፡ ክበብ ሙቀትና ብርሃኑ ያለመነጣጠል ያሉ
ናቸው፡፡
ሰው በቃሉ በትንፋሹ ሦስት እንደሚሆን ስለዚህ እግዚአብሔር ሰውን እንደመልካችን እንደምሳሌያችን እንፍጠር አለ፡፡ ሰውየው
የአብ ምሳሌ ነው ቃልም የወለድ እስትንፋሱም የመንፈስ ቅዱስ ምሳሌ ነው፡፡ ነገር ግን ሰውየው እስትንፍሱንና ቃሉን ለማየት ኃይል
አይኖረውም፡፡ መልክ ስለሌላቸው በውስጡ ሲጮሁ ይሰማቸዋል እእጂ ቃልና እስትንፍስም መልክ ስለላቸው ሰውየውን ሊያዩት አይችሉም፡፡
ነገር ግን መልክና ገጽ ሳይኖራቸው መኖራቸው የታወቀ ነው፡፡ ምሳሌም ከሞመስሉት ያንሳልና ሰም ከወርቅ እንዲያንስ ሰውም ከተመሰለበት
ከእግዚአብሔር ያንሳል ይጎላል፡፡ ለሥላሴ ግን እንዲህ አይደለም ለአብ ከፍጡረን መልክ የማይመሳሰል(ፍጹም አምላክን ሊመስለው የሚችል
ማንም እንደሌለ ልብ ብሏል) የወልድና የመንፈስ ቅዱስን መልክ የሚመስል ፍጹም መልክ አለው፡፡ለወለድና ለመንፈስ ቅዱስም እንዲሁ
ነው፡፡
ልዩ ሦስትንት
ይህም ከሥነ ፍጥረታት መካከል ለምሥጢረ ሥላሴ ምሳሌ ነው፡፡ ነገር ግን ምሳሌው ሕጸጽ ወይም ጉድለት አለበት፡፡ ለዚህም
ነው ሥላሴ ማለት ልዩ ሦስትነት ማለት ነው ያልነው ልዩ የሚለውን ቅጽል የጨመርንበትም ለዚህ ነው፡፡ ለምሳሌ ካነሳነው መካከል ፀሐይ
ሕጸጽ ወይም ጉድለት አለበት ስለዚህም ለሥላሴ ፍጹም ምሳሌ ሊሆን አይችልም፡፡ ከጉድለቱ መካከል አንዱን እንኳን ብንገልጽ ከፀሐይ
ሦስቱ አካላት መካከል ሁለቱ(ሙቀትና ብርሃኑ) ወደ ምድር ሲደርሱ አንዱ(ክበቡ) ግን አይደርስም፡፡ ይህም ለሥላሴ ፍጹም ምሳሌ እንዳይሆን
ያግደዋል፡፡ ለዚህም ነው ከሦስትነት የዘለለ ልዩ ሦስትነት መቀዳደም የሌለበት ሕጻጽ የሌለበት የምንለው፡፡
የእግዚአብሔር ሦስትነት
የሥላሴ ሦስትነታቸው እንዴት ነው ቢሉ በአምስት ነገር ነው፡፡ በስም፣ በአካል በገጽ በመልክዕና በግብር ሦስት ናቸው፡፡
የአካል ሦስትነት
በአካል ሦስትነት ማለት የአብ አካል የብቻው ነው የወለድ የመንፈስ ቅዱስም አካል የብቻው ነው በአካል መገናኛ የላቸውም
እስመ አካለ አብ ካልዕ እም አካለ ወለድ ወካልዕ እምአካለ መንፈስቅዱስ እንዲል መቃርዮስ (በሃይማኖተ አበው 1 ቁ 8) የፀሐይና
የሥላሴ ሦስትነት መገናኛ የላቸውም የብቻው ነው ማለታችን የፀሐይ ሦስትነት የግብር ብቻ ነው የአካል አይደለም በአካ አንድ ነው
በግብር ሦስት ነው የሥላሴ ግን በግብር ብቻ ሳይሆን በአካል ሦስት ነው
ገጽ ማለት ፊት ነው፡፡ ሥላሴ በገጸ ሦስትነት አላቸው የአብ ገጽ የብቻው ነው የወለድ የመንፈስ
ቅዱስም ገጽ የብቻው ነው፡፡ቀድመን እንዳነሳነውሰባርዮስ የተባለው መናፍቅ እግዚአብሔር ፍጹም አንድ አምላክ እንጂ ሦስትንት የለበትም
አለ ሊቃውንት እነደዛማ አንዳትል ቅዱስ ጴጥሮስ በስመ አበብወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ብሏል ቢሉት በተለያየ ወቅት ተገለጠ እንጂ አንድ
ነው እንደ አብ በብሉይ እንደወልድ በሐዲስ እንደ መንፈስ ቅዱስ በዘመነ ሐዋርያት ብሎ ሦሥትንተት የላቸውም አለ ሊቃውንቱም ጥቅመ
ሰናዖርን ያፈረሱ ጊዜ ኑ እንውረድ ብለው የለምን ቢሉት እርሱም ይህስ የሦስትንት አይደለም ዛሬ አንዱ ሰው አርባውን ሃምሳውን ኑ
እንቅረድ እንደሚለው ነው፡፡ ሊቃውንቱም ቀድሞ በደብረ ሲና አነ ውእቱ አምላከ አብርሃም አምላከ ይስሐቅ አምላከ ያዕቆብ ሦስት ጊዜ አምላክ
አለ ቢሉት እርሱም ዛሬ ብዙ ሃገር የሚገዛ እኔ የእገሌ ጌታ እንደሚል እንደዛው ነው እንጂ ሦስትንትን አያመለክትም አለሊቃውንቱም
ንግበር ሰብአ በአርያነ ወበአምሳሊነ ብለው የፈጠሩት አዳም ቃል ልብ እስትንፋስ ይዞ መገኘቱን ታምን ትክድ አሉት እርሱም አምን
አለ እነርሱም ይዞ ከተገኘ እርሱ ከማን አመጣው ትላለህ ለሥላሴ ሦስትነት የላቸውም ትላለህን አለ ብለህ እመን ሲሉት በዚህ ምሳሌነት
እረተውታል፡፡
መልክ ማለት ልዩ ሕዋሳትን (ዓይን፣ጆሮ፣አፍንጫ…..) የያዘውን ነው፡፡ የቀረው ብዙ ነው ሥላሴ በመልክ ሦስት ናቸው ማለት
እንዴት ነው ቢሉ ለአብ የብቻው ዓይን ጆሮ እጅ እግር አለው ለወልድም ለብቻው አለው ለመንፈስ ቅዱስም ለብቻው አለው ሥላሴ በመልክ
ሦስት ናቸው ማለት ነው፡፡(ሃይማኖተ አበው ዘአትናትዎስ 14 ቁ 13)
ቀድመን እንዳነሳነው አፍርንጅ የተባለ መናፍቅ ለሥላሴ መልክ የለውም (እግዚአብሔር ዝርው መንፈስ ነው አካል የለውም) ብሎ
ተነስቶ ነበር፡፡ የእግዚአብሔር ዓይኖች ወደ ጻድቃኑ ጆሮዎቹም ወደ ልመናቸው ነው የሚለውን ጠቀሱበት ይህስ ስላዩ ዓይኖች አላቸው
የሥላሴን መልክ አያስረዳም አለ ንግበር ሰብአ ብሎ ሰውን በመልኩና በአርአያው መልክ መፍጠሩን ታምናለህን አሉት አዎን አምናለሁ
አላቸው ታዲያስ መልኩን ከወዴት አመጣው ትላለህ አሉት በዚህም እረተውታል፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር በአካል ሦስት መሆኑን በግልጽ ይነግረናል (ማቴ 3፥16) “ጌታ ኢየሱስም ከተጠመቀ በኋላ ወዲያው
ከውሃ ወጣ እነሆ ሰማያት ተከፈቱ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንደ ርግብ ሲወርድ በእርሱም ላይ ሲመጣ ታየ፣ እነሆም ድምጽ ከሰማያት
መጥቶ በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው አለ” ይህ የአካል ሦስትነቱን ያስረዳናል ይኸውም፡-




ይቆየን ይቀጥላል
ስብሐት ለእግዚአብሔር
No comments:
Post a Comment