አዕማደ ምስጢራት
አምድ ማለት ምሶሶ ማለት ነው፡፡ በአምድ የተሠራ ቤት አይዛባም ያለዓምድ የተሠራ ቤት ግን ይፈርሳል አይጸናም፡፡ እንደዚህም
ሁሉ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን አዕማድ የተባሉ ምሥጢራት ይዞ የተገኘ ሰው ልቡናው በፍቅረ እግዚአብሔር በተስፋ መንግስተ ሰማያት
ይጸናል፡፡ እነዚህን አምስቱን እምነታት ሳይዝ የተገኘ ልቡናው በፍቅረ እግዚአብሔር በተስፋ መነንግስተ ሰማያት አይጸናምና አዕማድ
ይባላሉ፡፡ስለምን ምሥጢር አላቸው ቢሉ በዓይኔ ካላሣያችሁኝ በእጄ ካላሲዛችሁኝ ብሎ አላምንም አልማርም ይሉ ዘንድ አይገባም በቃል
ተምሮ በልቡና ተመራምሮ አዎን ብሎ የሚማሯቸው ስለሆኑ ምሥጢር አላቸው፡፡(ሃይ. አበው ዘአትናትዮስ 14÷ 39 ሃይ. አበው ዘኤራቅሊስ
11÷24 1ኛ ቆሮ 14፥19 1ኛ ሳሙ 17፥40)
አምስቱ አዕማደ ምስጢራት የሚባሉት
ምሥጢረ ሥላሴ፡- የምሥጢረ ሥላሴ ነገር እንዴት
ነው ቢሉ የሥላሴ አንድነት ሦስትነት ምልዓት ስፋት ርቀት ይህንን ማወቅ ማመን ነው፡፡ (ማቴ 28፥20) ማወቅ እንደምን ነው ቢሉ
ምሥጢሩን መማር ነው ማመንስ እንደምን ነው ቢሉ መናፍቃን ካህናት አላዊያን ነገሥታት ሃይማኖታችሁን ተነስተዉ ፈጣራችሁን ካዱ ለጣዖት
ስገዱ ብለው ሰይፍ ስለው እሳት አንድደወ በተነሱ ጊዜ አንክድም ብለው በተማሩት ሃይማኖት ተከራክሮ የደፈረ አንገቱን ለስለት ገላውን
ለእሳት ለውግረት ለሞት የፈራ ስደት ይህንን መቀበል ነው፡፡
ስለምን ምሥጢር ተባለ
የሥላሴን አንድነት ሦስትነት በዓይኔ ካላየሁ በእጄ ካልዳሰስኩ አላምንም ይሉ ዘንድ አይገባም በቃል ተምሮ በልቡና ተመራምሮ
አዎን ብሎ የሚማሩት የሚቀበሉት ነውና ምሥጢር ተብሏል፡፡
ምሥጢረ ሥጋዌ፡- የምሥጢረ ሥጋዌ ነገር እንደምን
ነው ቢሉ ከሦስቱ አካላት ከሥላሴ አንዱ አካል ወልድ በተለየ አካሉ ሰው እንደሆነ ከእግዚእነ ማርያም እንደተወለደ በየጥቂቱ እንዳደገ
በሠላሳ ዘመኑ በማየ ዮርዳኖስ በእደ ዮሐንስ እንደተጠመቀ ገዳመ ቆሮንቶስ ገብቶ አርባ መዓልት አርባ ሌሊት እንደጾመ ሦስት ዓመት
ከሦስት ወር ሕገ ወንጌልን እንዳስተማረ እንደተሰቀለ እንደሞተ እንደተነሳ በአርባኛው ቀን እንደዐረገ በኋላም ይህችን ዓለም ለማሳለፍ
እንደሚመጣ ማወቅ ማመን ነው፡፡(ዮሐ 1፥19)
ስለምን ምሥጢር ተባለ
ረቂቅ መረኮት ርቀቱን ሳይለቅ ከግዙፍ ሥጋ ጋር ተዋሐደ ማለት ሰማይና ምድር የማይችሉት መለኮት ቁመቷ አጭር ወርዷ ጠባብ
በሆነ እግዝእትኘ ማርያም ማኅጸን ተቻለ ይህንንም በዓይኔ ካላየሁ በእጄ ካልዳሰስኩ አላምንም ይሉ ዘንድ አይገባም በቃል ተምሮ በልቡና
ተመራምሮ አዎን ብሎ የሚማሩት የሚቀበሉት ነውና ምሥጢር ተብሏል፡፡
ምሥጢረ ጥምቀት፡- ስለጌታ እና ስለ ክርስቲያኖች
ጥምቀት የምንማርበት ነው (ማር 16፥16)
ስለምን ምሥጢር ተባለ
ካህኑ ምሥጢረ ጥምቀትን ሲፈጽም አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ
ብሎ ውሃውን ሲባርከው መንፈስቅዱስ በውሃው ላይ ያድርበታል፡፡ ከጌታችን ቀኝ የወጣው ውሃ ይሆናል(ማየ ገቦ) በዚያ የተጠመቀ
ሰው ጸጋ መንፈስ ቅዱስ (ልጅነት) ያገኛል፡፡ ምሥጢሩ ሲፈጸም የሚያይ ወይም የሚጠመቅ ሰው የውሃው ቅዝቃዜ የውሃው ጥቁረት ይታየዋል
እንጂ ከሥላሴ ሲወለድ ጸጋ መንፈስ ቅዱስ ሲያገኝ በዓይነ ሥጋ አይታይም ይህንንም በዓይኔ ካላየሁ በእጄ ካልዳሰስኩ
አላምንም ይሉ ዘንድ አይገባም በቃል ተምሮ በልቡና ተመራምሮ አዎን ብሎ የሚማሩት የሚቀበሉት ነውና ምሥጢር ተብሏል፡፡
ምሥጢረ ቁርባን፡- ስለጌታችን መድኃኒታችን አማናዊ
ስጋና ደም የምንማርበት (ዮሐ 6፥54)
ስለምን ምሥጢር ተባለ
ካህኑ ምሥጢሩን ሲፈጽም አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ ብሎ ኅብስቱን ጽዋውን ሲባርከው
ኅብስቱ ተለውጦ ሥጋ አምልክ ወይኑ ተለውጦ ደመ አምላክ የሚሆንበት ምሥጢር ነው፡፡ ይህንን በዓይኔ ካላየሁ በእጄ ካልዳሰስኩ አላምንም
ይሉ ዘንድ አይገባም በቃል ተምሮ በልቡና ተመራምሮ አዎን ብሎ የሚማሩት የሚቀበሉት ነውና ምሥጢር ተብሏል፡፡
ጌታ ይህንን ያህል ሥጋውን ደሙን ለምን ሰወረው ቢሉ ቢገልጠው የሚቆርብ የሚያቆርብ አይገኝምና፡፡ እንደምን ቢሉ ኅብስቱ
በጻሕል ወይኑን በጽዋ አድርጎ አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስፈኑ ጸጋ መንፈስ ቅዱስ ላዕሌነ ብሎ
ሲባርከው ኅብስቱ ወይኑ ተለውጦ ሥጋ መለኮት ደመ መለኮት ይሆናል እንዴትስ የመለኮት ሥጋ ደም ይፈተታል እንዴትስ ሰው በእሳት ይቀበላል፡፡
ስለዚህም ሰውሮታል፡፡
ምሥጢረ ትንሣኤ ሙታን፡- ስለ ጌታና የሰው ልጆች ትንሣኤ
የምንማርበት ናቸው፡፡(ዮሐ 11፥25)
ስለምን ምሥጢር ተባለ
ይህንንም ምሥጢር በዓይኔ ካላየሁ በእጄ ካልዳሰስኩ አላምንም ይሉ ዘንድ አይገባም በቃል ተምሮ በልቡና ተመራምሮ አዎን ብሎ
የሚማሩት የሚቀበሉት ነውና ምሥጢር ተብሏል፡፡
እነዚህን ምሥጢራት ማወቅ መማር እንደአርዮስ ወለድ ፍጡር ነው ከማለት እንደፎጢኖስ የወለድ መገኛው ከእመቤተችን ከተወለደ
ወዲህ ነው እንጂ ከዚያ በፊት አልነበረው ከማለት መዓረገ መንግስት እንደሚሰጡ መናፍቃን አብ ንጉሠ ነገሥት ወልድ ቢትትደድ መንፈስ
ቅዱስ ብለላቴን ጌታ ነው ከማለት መዓረገ ርቀት እንደሚሰጡ መናፍቃን ከነፍስ ነፍሳት ከነፍሳት መላእክት ይረቃሉ ከመላእእት መንፈስ
ቅደስ ይረቃል ከመንፈስ ቅዱስ ወልድ ከወለድ አብ ይረቃል ከማለት በሦስቱ አካላት መካከል ልዩነት እንዳለ ሁሉ እኔ የአብ አገልገጋይ
ነኝ ወልድና መንፈሰ ቅዱሰ ለእኔ ምኔ ናቸው እኔ የወለድ አገልጋይ ነኝ አብና ወልድ ምኔ ናቸው እኔ የመንፈስ ቅዱስ
ባርያ ነኝ አብና ወለድ ምኔ ናቸው ከማለት ከመናናቃኑ ትምህርት ለመጠበቅ ይረደዳዳል፡፡
ነገረ ሃይማኖት
ክፍል አስራ ሦስት
ምሥጢረ ሥላሴ
የቅድስት ሥላሴ መሠረተ እምነት
ለክርስቲያን ሁሉ የምሥጢረ ሥላሴን ነገር ጠንቅቆ ማወቅ ይገባል፡፡ ይህን የአባቶች ትምህርት በሚገባ
መረዳት ከመናፍቃኑ ትምህርት ለመጠበቅ ወሳኝ ነው፡፡ የነገረ ሥላሴን ያልተረዱ መናፍቃን በተለያየ ወቅት ተነስተው ክህደት ቢዘሩም
አባቶች ከመጻሕፍት እየጠቀሱ በምሳሌ እየተነተኑ እረተዋቸዋል፡፡ ሰባርዮስ የተባለው መናፍቅ እግዚአብሔር ፍጹም አንድ አምላክ እንጂ
ሦስትንት የለበትም አለ በተለያየ ወቅት ተገለጠ እንጂ አንድ ነው አለ እንደ አብ በብሉይ እንደወልድ በሐዲስ እንደ መንፈስ ቅዱስ
በዘመነ ሐዋርያት ይህ ነገረ ሥላሴን ካለመረዳት ነው፡፡ አምላክ ሁለት ነው ያሉም አሉ አንዱ በሰማይ አንዱ በምድር ይገዛል ብለው
ተነስተዋል፡፡ አንድም ባዕል አምላክ ነዳይ ብለው ከፍለውታል ባለጸጋው ባለጸጎችን ፈጠረ ድኃው ነዳያንን ፈጠረ ብለው አስተምረዋል
ሊቃውንትም ከመጻሕፍት ጠቅሰው ረተዋቸዋል፡፡ዳግመኛም ሦስት አማልክት ያሉ ተነስተዋል ሠናይ አምላክ እኩይ አምላክ ራትዕ ብለው ተነስተው
ነበር፡፡ ሠናይ አምላክ እንልማ ይላል እኩይ እናጥፍ ይላል ራትዕ አንተም ተው አንተም ተው ይላል ብለዋል አባቶችም ይህን ከመጻሕፍት
ጠቅሰው አስረድተዋል፡፡ አራት አማልክት ያሉ አሉ የአብ አባት አለው ብለው አንድም ከእግዝእትነ ማርያም የተወለደው ክርስቶስን አራተኛ
ብለው ሊቃውንት ከመጻሕፍት ጠቅሰው ረተዋቸዋል፡፡ ዳግመኛም ሰባት አማልክት አሉ የሚሉ መናፍቃን ለዕለታት ሁሉ አንድ አንድ አማልክት
አሏቸው ብለው አስተምረዋል ሠላሳም ያሉ አሉ ከመባቻ እስከ መባቻ አማልክት አሉ ያሉሦስት መቶ ስሳ አምስት ያሉም
አሉ በቀናት ቆጥረው ሰፍረው ይህንንም አባቶች ጠቅሰው ረተዋቸዋል፡፡ እነዚህ ሁሉ ምሥጢረ ሥላሴን ባለመረዳት የመነጨ ነው ፡፡ ከእነዚህ
ለመለየት እንደ እምነታችን መጠን እንደአእምሮችን ልክ ምሥጢሩን መማር ይገባናል፡፡
ምሥጢረ ሥላሴ በኦርቶዶክሳዊያን
ሥላሴ ማለት ልዩ ሦስትነት ማለት ነው፡፡ ልዩ ሦስትነትን ከመረዳታችን በፊት ደግሞ ‹‹ሦስት››ነትን መረዳት ያስፈልጋል፡፡
በሦስት በሦስትነት መካከል ያለውን ልዩነት በሚገባ ከተረዳን የልዩ ሦስትነትን ትርጉም መረዳት ይቻላል፡፡
ሦስት
ሦስት ማለት በቁጥርነቱ(እንደ ቁጥር) ተመሳሳይ ይሁኑ ወይም የተለያዩ በአንድ አካባቢ መኖራቸውን የሚገለጽልን መስተአምር(ቃል)
ነው፡፡ለምሳሌ ሦስት ሰዎች ስንል ሰው መሆናቸው አንድ ቢያደርጋቸውም የተለያዩ አካላት በመሆናቸው የተለያዩ ናቸው ሥስት የቤት እንስሳት
ሲሆኑ ደግሞ የተለያዩ ሆነው በአንድ መሰባሰባቸውን ያመለክተናል፡፡ ለዚህም ነው ተመሳሳይ ይሁኑ ወይም የተለያዩ በአንድ አካባቢ
መኖራቸውን የሚገለጽልን ነው ያልነው፡፡
ሦስትነት
ሦስትነት ማለት አንድነት ላለው አካል የሚቀጽል ነው፡፡ ይህም ማለት ቃሉ አንድነትን ሊያስከትል የሚችል መሆን አለበት ለምሳሌ
ፀሐይ አንድነት አላት(አንድ ናት) ነገር ግን ሦስትነት(ሦስት ነገሮች) አላት ክበብ ብርሃንና ሙቀቱ ነገር ግን ፀሐይ አንድ ናት፡፡
ሌላ ምሳሌ እንጨምር የሰው ነፍስ አንድ ነው ነገር ግን ሦስተነት አለው ለባዊነት(ማሰብ) ሕያዊነት(እስትንፍስ)ና ነባቢነት(ተናጋሪ
ነት) ነፍስ ግን አንድ ነው እንጂ ሦስት አይደለም፡፡
የሦስትነት ምሳሌዎች
የሰው ነፍስ
ሰው በፈጣሪው አርአያና አምሳል የተፈጠረ ስለሆነ ስለሥላሴ ሦስትንትና አንድንትእንዴት እንደሆነ በመጠኑም ቢሆን ከሰው የተፈጥሮ
ባሕርይ ውስጥ በምሳሌነት ልንጠቅሰው የምንችለው ትምህርት አለ፡፡ ሰውም ፈጣሪውን መምሰሉ በነፍሱ እንጂ በሥጋ አይደለም፡፡ምክንያቱም
እግዚአብሔር መንፈስ ነውና፡፡ ሦስቱ የነፍስ ባሕርያት የተበሳሉ ለባዊነት ነባቢነት ሕያውነት ናቸው፡፡ ሰው አንድ ሆኖ ሳለ ሐሳብ
አለው ሐሳቡን የሚገልጽበት ቃል አለው እንዲሁም ቃሉን የሚያዘስተላልፍበት ሕይወት ወይም እስትንፍስ አለው፡፡ እነዚህ ሦስቱ በአንድ
ሰው ላይ ስለሚገኙ አንድም ሦሥትም ሆነው እናያቸዋልን፡፡
እንዲህ በዚህ ምሳሌ የምንረዳው አብ እንደልብ ወለድ እንደ ቃል መንፈስቅዱስ እንደእስትንፍስ ተመስለው ለሥላሴ እንድነትናሦስትነት
ምሳሌ ሆነው ይነገራሉ፡፡
የነፍስ ልብነቷ፣ ቃልነቷና እስትንፋስነቷን ታስገኛለች፡፡ እንዲሁ በልብነቷ የተመሰለው አብ በቃልነቷ
የተመሰለው ወልድን ይወልዳል፡፡ በእስትንፋስነቷ የተመሰለውን መንፈስ ቅዱስን ያሰርጻል፡፡ ነፍስ ስትገኝ በሦስትነቷ በአንድ ጊዜ
ተገኝታለች እንጂ ልብነቷ ቀድሞ ቃልነቷና እስትንፋስነቷ ኋላ የተገኙ አይደሉም፡፡ እንዲሁ አብ ወልድን በመውለዱ መንፈስ ቅዱስንም
በማስረጹ አይቀድማቸውም፡፡ ልብ ቃል እስትንፋስ በመሆን የከዊን ሦስትነት ቢኖራትም አንዲት ነፍስ እንጂ ሦስት ነፍስ አትባልም፡፡
ሥላሴ በስም፣ በአካል፣ በግብር ሦስት ቢሆኑም ሦስት አካል አይባሉም፤ አንድ አምላክ እንጂ ነገር ግን ነፍስ ሦስትነት ቢኖራትም
በአካል አንድ ናት፡፡ ሥላሴ ግን አብ አካላዊ ልብ ነው፣ ወልድ አካላዊ ቃል ነው፣ መንፈስ ቅዱስም አካላዊ እስትንፋስ ነው፡፡ የአካሉ ሦስት መሆን
ባሕርይው አንድ መሆን አካላቱን አይጠቀልለውም፡፡ ስለሆነም ሥላሴ በባሕርይ አንድ በአካል ሦስት ናቸው ብለን እናምናለን፡፡
ፀሐይ
ለፀሐይ ክበብ፣ ብርሃንና ሙቀት አለው፡፡ በክበቡ አብ፣ በብርሃኑ ወልድ፣ በሙቀቱ መንፈስ ቅዱስ ይመሰላሉ፡፡ ክበቡ ብርሃኑን
እና ሙቀቱን ያስገኛል እንጂ ብርሃኑ ሙቀቱንና ክበቡን አያስገኝም፡፡ ሙቀቱም ክበቡንና ብርሃኑን አያስገኝም፡፡
ፀሐይ አንድ ስትሆን ሦስት ነገሮች ስላሏት ሦስት ፀሐይ እንደማትባል ሥላሴም በሥም፣ በአካል፣ በግብር ሦስት ቢሆኑም ሦስት
አማልክት አይባሉም አንድ አምላክ እንጂ፡፡እንዲሁ የመወለድንና የመስረጽን ሁኔታ በፀሐይ ምሳሌነት ማወቅ እንችላለን ከብርሃን አክልና
ባሕርይ ብርሃን እንደሚወጣ ከሙቀት አካልና ባሕርይ ሙቀት እንደሚገኝ እንዲሁም ወለድና መንፈስ ቅዱስ ከአብ መለኮታዊ አካልና ባሕርይ
ይገኛሉ ይወጣሉ፡፡ ይህም ለሥላሴ ምሳሌ ነው፡፡ ከብርሃን የተገኘ ብርሃን ከእውነተኛ አምላክ የተገኘ አምላክ ተብሎ በጸሎተ ሃይማኖት
የጠገለጠው ክፍለ ንባብ ለዚህ አስረጅ ነው (ጸሎተ ሃይማኖት አንቀጽ 3)
የፀሐይ ክብ ከሰማይ እንዳይወርድ አብ ከመንበሩ አይናወጥም፡፡ ብርሃኑና ሙቀቱ ወደ ምድር መድረሳቸው ወልድና መንፈስ ቅዱስ
ወደ ዓለም የመምጣታቸው ምሳሌ ወልድ በከዊን ተዋሕዶ መንፈስ ቅዱስም ኅድረት ተዋሕዶ በዘመነ ሐዋርያት መውረዱን አመልካች ነው፡፡
ምንም እንኳን አብ በተለየ አካሉ ወደ ምድር ባይወርድምከወለድና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ሕልው ሆኖ ይኖራል፡፡
ክበበበ ፀሐይ ብርሃንን ዋዕይን እየላከ መኖሩን ያስታውቃል እንጂ የሚላክ አይደለም፡፡ እንደዚሁ አብ ወለድን መንፈስቅዱስን
እየላከ ሕልውናውን ይገልጻል እንጂ ለማንም የታየና የተገለጸአይደለም(ዮሐ 1÷18)
ያለብርሃንና ሙቀት የፀሐይን ፀሐይነት ማወቅ እንደማይቻል እንዲሁም ያለወልድና ያለምንፈስ ቅዱስ የአብን መለኮትነት ለማወቅ
አይቻልም፡፡
ቀላይ/ባሕር/
ቀላይ/ባሕር/ ሦስት ነገር አለው፡፡ እነዚህም ስፍሐት፣ ርጥበትና ሁከት /የተባለው የባሕሩ እንቅስቃሴ ነው/፡፡ በባህሩ
ስፍሐት አብ በርጥበቱ ወልድ በሁከቱ መንፈስ ቅዱስ ይመሰላሉ፡፡ይህ ሦስት ነገር ያለው ባሕር አንድባሕር እንጂ ሦስት ባሕር እንደማይባል
ሦስት ከዊን ያላቸው ሥላሴም አንድ አምላክ ይባላሉ እንጂ ሦስት አማልክት አይባሉም፡፡
እሳት
እሳት ሦስት ነገር አለው፡፡ እነዚህም ብርሃን፣ ሙቀትና አካል(ክበብ) ነው፡፡ አለው፡፡ በክበቡ አብ፣ በብርሃኑ ወልድ፣
በሙቀቱ መንፈስ ቅዱስ ይመሰላሉ፡፡ ክበቡ ብርሃኑን እና ሙቀቱን ያስገኛል እንጂ ብርሃኑ ሙቀቱንና ክበቡን አያስገኝም፡፡ ሙቀቱም
ክበቡንና ብርሃኑን አያስገኝም፡፡
ሦስትነቶች ለምን ሦስት አያባሉም?
የሦስትነት ምሳሌዎች ሕጸጽ
ታዲያ ሦስትነቶች ለምን ሦስት አያባሉም? የሚለውን ጥያቄ መመለስ በሦስትና በሦስትነት መካከል ያለውን ልዩነት እንድንገነዘብ
ይረዳናል፡፡ምክንያቱም ከሦስቱ አንዱ ለብቻው ማግኘት ስለማይቻል ነው፡፡ ለምሳሌ ከሰው ነፍስ መካከል ለባዊነትን ለብቻ ማግኘት አይቻለንም
ወይም ሕያውነትን ወይም ነባቢነት የማይነጣጠሉ አንድ ናቸው፡፡ሰው እያወቀና እየተናገረ የማይተነፍስ አይደለም፡፡ ወይም እየተነፈሰና
እየተናገረ የማያስብ አይደለም(የተለየ እክል ካልገጠመው በቀር) እንዲሁም እያሰበና እየተነፈሰ የማይናገር አይደለም፡፡(ተናጋሪነት
ሐሳብን መግለጥ ማለት ነው) እንዲሁ ቅድም በምሳሌነት ያነሳነው ፀሐይ ተመሳሳይ ነው፡፡ ክበብ ሙቀትና ብርሃኑ ያለመነጣጠል ያሉ
ናቸው፡፡
ሰው በቃሉ በትንፋሹ ሦስት እንደሚሆን ስለዚህ እግዚአብሔር ሰውን እንደመልካችን እንደምሳሌያችን እንፍጠር አለ፡፡ ሰውየው
የአብ ምሳሌ ነው ቃልም የወለድ እስትንፋሱም የመንፈስ ቅዱስ ምሳሌ ነው፡፡ ነገር ግን ሰውየው እስትንፍሱንና ቃሉን ለማየት ኃይል
አይኖረውም፡፡ መልክ ስለሌላቸው በውስጡ ሲጮሁ ይሰማቸዋል እእጂ ቃልና እስትንፍስም መልክ ስለላቸው ሰውየውን ሊያዩት አይችሉም፡፡
ነገር ግን መልክና ገጽ ሳይኖራቸው መኖራቸው የታወቀ ነው፡፡ ምሳሌም ከሞመስሉት ያንሳልና ሰም ከወርቅ እንዲያንስ ሰውም ከተመሰለበት
ከእግዚአብሔር ያንሳል ይጎላል፡፡ ለሥላሴ ግን እንዲህ አይደለም ለአብ ከፍጡረን መልክ የማይመሳሰል(ፍጹም አምላክን ሊመስለው የሚችል
ማንም እንደሌለ ልብ ብሏል) የወልድና የመንፈስ ቅዱስን መልክ የሚመስል ፍጹም መልክ አለው፡፡ለወለድና ለመንፈስ ቅዱስም እንዲሁ
ነው፡፡
ልዩ ሦስትንት
ይህም ከሥነ ፍጥረታት መካከል ለምሥጢረ ሥላሴ ምሳሌ ነው፡፡ ነገር ግን ምሳሌው ሕጸጽ ወይም ጉድለት አለበት፡፡ ለዚህም
ነው ሥላሴ ማለት ልዩ ሦስትነት ማለት ነው ያልነው ልዩ የሚለውን ቅጽል የጨመርንበትም ለዚህ ነው፡፡ ለምሳሌ ካነሳነው መካከል ፀሐይ
ሕጸጽ ወይም ጉድለት አለበት ስለዚህም ለሥላሴ ፍጹም ምሳሌ ሊሆን አይችልም፡፡ ከጉድለቱ መካከል አንዱን እንኳን ብንገልጽ ከፀሐይ
ሦስቱ አካላት መካከል ሁለቱ(ሙቀትና ብርሃኑ) ወደ ምድር ሲደርሱ አንዱ(ክበቡ) ግን አይደርስም፡፡ ይህም ለሥላሴ ፍጹም ምሳሌ እንዳይሆን
ያግደዋል፡፡ ለዚህም ነው ከሦስትነት የዘለለ ልዩ ሦስትነት መቀዳደም የሌለበት ሕጻጽ የሌለበት የምንለው፡፡
የእግዚአብሔር ሦስትነት
የሥላሴ ሦስትነታቸው እንዴት ነው ቢሉ በአምስት ነገር ነው፡፡ በስም፣ በአካል በገጽ በመልክዕና በግብር ሦስት ናቸው፡፡
የአካል ሦስትነት
በአካል ሦስትነት ማለት የአብ አካል የብቻው ነው የወለድ የመንፈስ ቅዱስም አካል የብቻው ነው በአካል መገናኛ የላቸውም
እስመ አካለ አብ ካልዕ እም አካለ ወለድ ወካልዕ እምአካለ መንፈስቅዱስ እንዲል መቃርዮስ (በሃይማኖተ አበው 1 ቁ 8) የፀሐይና
የሥላሴ ሦስትነት መገናኛ የላቸውም የብቻው ነው ማለታችን የፀሐይ ሦስትነት የግብር ብቻ ነው የአካል አይደለም በአካ አንድ ነው
በግብር ሦስት ነው የሥላሴ ግን በግብር ብቻ ሳይሆን በአካል ሦስት ነው
ገጽ ማለት ፊት ነው፡፡ ሥላሴ በገጸ ሦስትነት አላቸው የአብ ገጽ የብቻው ነው የወለድ የመንፈስ
ቅዱስም ገጽ የብቻው ነው፡፡ቀድመን እንዳነሳነውሰባርዮስ የተባለው መናፍቅ እግዚአብሔር ፍጹም አንድ አምላክ እንጂ ሦስትንት የለበትም
አለ ሊቃውንት እነደዛማ አንዳትል ቅዱስ ጴጥሮስ በስመ አበብወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ብሏል ቢሉት በተለያየ ወቅት ተገለጠ እንጂ አንድ
ነው እንደ አብ በብሉይ እንደወልድ በሐዲስ እንደ መንፈስ ቅዱስ በዘመነ ሐዋርያት ብሎ ሦሥትንተት የላቸውም አለ ሊቃውንቱም ጥቅመ
ሰናዖርን ያፈረሱ ጊዜ ኑ እንውረድ ብለው የለምን ቢሉት እርሱም ይህስ የሦስትንት አይደለም ዛሬ አንዱ ሰው አርባውን ሃምሳውን ኑ
እንቅረድ እንደሚለው ነው፡፡ ሊቃውንቱም ቀድሞ በደብረ ሲና አነ ውእቱ አምላከ አብርሃም አምላከ ይስሐቅ አምላከ ያዕቆብ ሦስት ጊዜ አምላክ
አለ ቢሉት እርሱም ዛሬ ብዙ ሃገር የሚገዛ እኔ የእገሌ ጌታ እንደሚል እንደዛው ነው እንጂ ሦስትንትን አያመለክትም አለሊቃውንቱም
ንግበር ሰብአ በአርያነ ወበአምሳሊነ ብለው የፈጠሩት አዳም ቃል ልብ እስትንፋስ ይዞ መገኘቱን ታምን ትክድ አሉት እርሱም አምን
አለ እነርሱም ይዞ ከተገኘ እርሱ ከማን አመጣው ትላለህ ለሥላሴ ሦስትነት የላቸውም ትላለህን አለ ብለህ እመን ሲሉት በዚህ ምሳሌነት
እረተውታል፡፡
መልክ ማለት ልዩ ሕዋሳትን (ዓይን፣ጆሮ፣አፍንጫ…..) የያዘውን ነው፡፡ የቀረው ብዙ ነው ሥላሴ በመልክ ሦስት ናቸው ማለት
እንዴት ነው ቢሉ ለአብ የብቻው ዓይን ጆሮ እጅ እግር አለው ለወልድም ለብቻው አለው ለመንፈስ ቅዱስም ለብቻው አለው ሥላሴ በመልክ
ሦስት ናቸው ማለት ነው፡፡(ሃይማኖተ አበው ዘአትናትዎስ 14 ቁ 13)
ቀድመን እንዳነሳነው አፍርንጅ የተባለ መናፍቅ ለሥላሴ መልክ የለውም (እግዚአብሔር ዝርው መንፈስ ነው አካል የለውም) ብሎ
ተነስቶ ነበር፡፡ የእግዚአብሔር ዓይኖች ወደ ጻድቃኑ ጆሮዎቹም ወደ ልመናቸው ነው የሚለውን ጠቀሱበት ይህስ ስላዩ ዓይኖች አላቸው
የሥላሴን መልክ አያስረዳም አለ ንግበር ሰብአ ብሎ ሰውን በመልኩና በአርአያው መልክ መፍጠሩን ታምናለህን አሉት አዎን አምናለሁ
አላቸው ታዲያስ መልኩን ከወዴት አመጣው ትላለህ አሉት በዚህም እረተውታል፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር በአካል ሦስት መሆኑን በግልጽ ይነግረናል (ማቴ 3፥16) “ጌታ ኢየሱስም ከተጠመቀ በኋላ ወዲያው
ከውሃ ወጣ እነሆ ሰማያት ተከፈቱ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንደ ርግብ ሲወርድ በእርሱም ላይ ሲመጣ ታየ፣ እነሆም ድምጽ ከሰማያት
መጥቶ በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው አለ” ይህ የአካል ሦስትነቱን ያስረዳናል ይኸውም፡-




ይቆየን ይቀጥላል
ስብሐት ለእግዚአብሔር
No comments:
Post a Comment