ስለመዳናችን ምሥጢር ስለ ጸጋውና ስለ ቤተ ክርስቲያን ምሥጢራት
መዳናችን ቃሉን በማመንና ምሥጢራትን በመፈጸም ነው
ስለመዳን ከማወቃችን በፊት ቀድመን መዳን ምን ማለት ነው የሚለውን ነጥብ መገንዘብ ይገባናል፡፡ በኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ
መዳን ስንል የኃጢአት ደሞዝ ከሆነው ከሞትና ከቅጣት መዳን ብቻ ወይም ከኩነኔ መዳንና ማምለጥ ብቻ አይደለም፡፡ መዳን ኃጢአት ሥርየትን
ማግኘትና ከቅጣት መዳን ብቻ ሳይሆን ከዚያ እጅግ ያለፈ ጥልቅና ሁለንተናዊ ነው፡፡ ይህም መሠረታዊና ዋና ነገር ነው፡፡ ሆኖም ግን
ይህ እንዳለ ሆኖ በዚያ ላይ የተሰጡን ብዙ ጸጋዎችና ሀብታትም አሉ፡፡ ጌታችን ያደረገልን የመዳን ቸርነትና ሥጦታ ስለእኛ ተገብቶ
የኃጢአታችንን ዕዳ መክፈልና እኛን ነጻ ማውጣት ብቻ አይደለም ከዚያ በላይ የሆነ እጅግ በጣም ብዙና ድንቅ ነገር ነው እንጂ፡፡
መዳን ስንል ኃጢአት ካመጣው ፍዳ ሁሉ መዳን ፈጣሪውን እንድናቅ መሆን ሐዲስ ተፈጥሮ መታደስ በቅድስና(እግዚአብሔርን በመመሰል)
ማደግ ናቸው፡፡
በፕሮቴስታንት ትምህርት መሠረት ኃጢአታችን በሙሉ በጌታችን በመስቀል ላይ ሳለ ወደ እርሱ የተላለፈበትን ዕዳነቱን የከፈለበት
ከሆነ በኃጢአታችን አንጠየቅም የሚል ነው፡፡ ምክንያቱም ምትካችን ከሁለት ሺህ ዓመታት አስቀድሞ ከፍሎታልና(እንደነርሱ አባባል ኃጢአታችን
አያስጠይቀንም) የሚል ነው፡፡
ይህ ከሆነ ከዚህ አስተምሮ ወደ የሚከተለው ድምዳሜ ላይ መድረስ ይቻላል ይኸውም የሰው ልጅ በሙሉ(አመነም
ኃጢአት ሠራም አልሠራም) ይድናል የሚለው አስተሳሰብ ነው(universal salvation)ነው፡፡ አለበዚያ ደግሞ ኢየሱስ ክርስቶስ
የሞተው ለማዳን ለመረጣቸውብቻ እንጂ ለመላው የሰው ልጅ አይደለም የሚለው አስተሳሰብ (john calvinʼs limited
atonements) ሆኖም ሁለቱም አስተሳሰቦች ስህተቶች ናቸው፡፡
የካሊቪን ምትክ ቲዎሪ ይህም የሚድኑ አስቀድመው ለመዳን የተወሰኑ ወይም የተመረጡ ጥቂቶች ናቸው
የሚለው ነው፡፡ ይህ ከሉተርን ትምህርት ጋር የሚቃረን ነው ካመነ ይድናል የሚለው ትምህርት ሁሉም ሰው እንዴት ይድናል? የሚለው
የጌታ ትምህርት የሚድኑ ጥቂቶች ናቸው ከሚለው ጋር የሚጋጭ ሆነ …
እንደኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ትምህርት መዳን አንዴ ሚከወን ሳይሆን መዳን ሂደት ነው፡፡ ሰው ለመዳን በቅድምያ ማመን
ቀጥሎም ምሥጢራትን መፈጸም ይገባል፡፡ ለመዳን መሠረታዊ የሆኑት ምሥጢራት መካከል ዳግመኛ የምንወለድበት ጥምቀትን መፈጸም የመንፈስ
ቅዱስ ጸጋ የምናግኝበት ምሥጢረ ሜሮን መፈጸም ቀጥሎም ከእግዚአብሔር ጋር በሕብረት የምንኖርበትን ምሥጢረ ቁርባንን መፈጸም ይገባል
በዚህም ብቻ አያበቃም መንፈሳዊ ትሩፋትና ተጋድሎ መፈጸም ይገባናል፡፡
ምሥጢረ ጥምቀት
ጥምቀት የሚለው ቃል አጥመቀ - ካለው የግእዝ ግሥ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም መነከር መዘፈቅ በተጸለየበት ውሃ ውስጥ ገብቶ
መውጣት መጥለቅ ማለት ነው፡፡
ስለጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጥምቀት
ሕዝቡ ሁሉ ከተጠመቀ በኋላ ጌታችን ወደ ዮሐንስ ቀርቦ አጥምቀኝ አለው፡፡ ዮሐንስም ‹‹እኔ በአንተ እጠመቅ ዘንድ ይገባኛል
እንጂ እንዴት አጥምቀኝ ትላለህ›› ብሎ ይከለክለው ነበር፡፡ ጌታችን ግን ‹‹ አሁንስ ፍቀድልኝ እንግዲህ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባልና፡፡››
(ማቴ 3÷15) ቢለው ፈቀደለትና አጠመቀው በዚህም ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት ተብሏል ፤ ታላቅ ክብርና ጸጋም ተሰጥቶታል፡፡ (ሉቃ
7÷28)
ጌታችን ለምን ተጠመቀ
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዮሐንስ እጅ የተጠመቀው እንደ አይሁድ ሥርዓት ለመንጻት አይደለም፡፡ ጌታችን ኃጢአት ኖሮበት
ሊነጻ የተጠመቀ ሳይሆን ከእርሱ ጋር አንድነት ይሰጠን ዘንድ ተጠመቀ፡፡ በመጠመቁ ኃይል የሚያገኝ ሆኖ አይደለም፡፡ በጥምቀቱ ጥምቀታችንን
ቀድሶልን ሰይጣንን የምናሸንፍበት ኃይል ሊሰጠን የእግዚአብሔር ልጅ የምንሆንበት ጸጋ ሊያድለን ተጠመቀ እንጂ፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ በዘመነ ኦሪት ተሠውሮና ረቆ የነበረውን ምሥጢረ ሥላሴን ሊገልጥልን ተጠምቋል፡፡ (ማቴ 3÷16) ይኸውም
ወልድ በዮርዳኖስ ሲጠመቅ አብ በደመና መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል ተገልጧል፡፡ ስለዚህም ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ጌታ የተጠመቀበትን
ዕለት ኢጲፋንያ ብለውታል፡፡ ኢጲፋንያ ቃሉ የፅርዕ ሲሆን በግእዝ አስተርዕዮ በአማርኛ መታየት/መገለጥ/ ማለት ነው፡፡
ጌታ በማን ተጠመቀ
ዮሐንስም ጌታን ‹‹ ሌላውን በአንተ ስም አጠምቃለሁ አንተን ግን በማን ስም ላጥምቅህ ›› ብሎ ጠይቆት ነበር፡፡ ጌታም ‹‹ እንደ መልከጼዴቅ ሥርዓት አንተ የዘላለም ካህን ነህ ብርሃንን የምትገልጽ የአብ የባህርይ ልጅ ሆይ ይቅር በለኝ ብለህ አጥምቀኝ›› ብሎታል እንዳለውም ጌታን አጥምቆታል፡፡(መዝ 109-4) ዮሐንስ ጌታን ሲያጠምቀው እጁን አልጫነበትም ነበር ፤ ለምን ቢሉ እጁን ጭኖበት ቢሆን ኖሮ አይሁድ ጌታችንን በዮሐንስ ከበረ ባሉ ነበረና፡፡
ጌታ ለምን ወደ ዮሐንስ ሄዶ ተጠመቀ
ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዮሐንስን ወደኔ መጥተህ አጥምቀኝ አላለውም ሄዶ ተጠመቀ እንጂ፡፡ እንደ ሥርዓቱ ቢሆን
ሎሌው ወደ ጌታው ይሄዳል እንጂ ጌታው ወደ ሎሌው አይሄድም፡፡ ጌታችን ዮሐንስን መጥተህ አጥምቀኝ ቢል ኖሮ ዛሬ ሹማምንት መኳንንት
መጥታችሁ አጥምቁኝ ባሉ ነበርና ነገር ግን ወደ ቤተ ክርስቲያን ሄደው ይጠመቁ ሲል ለአብነት ሄዶ ተጠምቋል፡፡
ጌታ መቼ ተጠመቀ
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በ30 ዓመቱ በ5531ዓ.ዓ ወይም በ31ዓ.ም በዘመነ ሉቃስ ጥር 11 ቀን ከሌሊቱ በ10 ሰዓት
ተጠምቋል፡፡ ሲጠመቀም ዮርዳኖስ ወንዝ በመካከሉ ተከፍሎ ወደ ፊትና ወደ ኋላ ሸሽቷል ኮረብቶችና ተራሮች በመዝለል አምላክነቱን መስክረዋል፡፡
(መዝ 113÷3-8 መዝ 76(77) ÷16)
ጌታ ለምን በሠላሳ ዘመኑ ተጠመቀ
1. የእስራኤልን ሥርዓት/ሕግ/
ለማክበር ነው ይኸውም በእስራኤል ሕግ አንድ ሰው መንፈሳዊ ሥራ የሚሠራው ከ 30 ዘመኑ በላ ሲሆነው ስለነበረ ነው፡፡
2. አዳም የ 30 ዓመት ጎልማሳ ተደርጎ
ተፈጥሮ በ 40 ቀኑ ያገኛትን ልጅነት አስወስዶ ነበርና ያን እንደመለሰለት ሲያጠይቅ
ጌታ ለምን በዮርዳኖስ ተጠመቀ
1. ዮርዳኖስ በጌታ ዘመን ነቁ/መነሻው/
አንድ ሲሆን ወረድ ብሎ ዮር እና ዳኖስ በመባል ለሁለት ተከፍሎ አንዱ ወደ አንዱ ወደ አሕዛብ አንደኛው ሕዝብ
/የአብርሃም ወገን ወደ ሆኑት/ይፈሳል፡፡ ከዚያም ተመልሶ ተጋጥሞ ይወርዳል ጌታም የተጋጠመበት ቦታ ተጠምቋል፡፡ ይህም ምሳሌነት
አለው፡፡ ዮርዳኖስ አንድ መሆኑ የሰው ዘር ሁሉ መገኛው አንድ መሆኑ (የአንድ የአዳም ዘር መሆኑ) ምሳሌ ነው፡፡ ወረድ ብሎ ለሁለት
መከፈሉ ሕዝብ እና አሕዛብ ተብሎ ለሁለት የመከፈላቸው ምሳሌ ተመልሶ መጋጠሙና ጌታ የተጋጠመበት ቦታ መጠመቁ ክርስቶስ የመጣው ለአዳም
ዘር ሁሉ እንደሆነ ሲያስረዳ ነው፡፡ እንዲሁም ሕዝብ እና አሕዛብን አንድ ሊያደርግ እንደመጣ ያጠይቃል፡፡
ትንቢት እና ምሳሌውን
ለመፈጸም ሲል ነው


ምሳሌው፡-
v አብርሃም ነገሥተ ኮሎዶጎሞርን
ከእነርሱ ጋር የነበሩትን ድል ነሥቶ ዮርዳኖስን ተሸግሮ መልከጸዴቅን ማግኘቱ፡- አብርሃም የምዕመናን ዮርዳኖስ የጥምቀት መልከጼዴቅ
የክርስቶስ ምሳሌ (ዕብ 7÷1-10) አብርሃም ዮርዳኖስን ተሸግሮ መልከጼዴቅን እንደተገናኘ እኛም ክርስቶስን ለማግኘት የእግዚአብሐር
የፀጋ ልጅ ለመባል መጠመቅ ይገባናል፡፡
v ኤልያስ ዮርዳኖስን ተሸግሮ ወደ ብሔረ ሕያዋን ማረጉ፡- ኤልያስ ዮርዳኖስን ተሸግሮ ወደ ብሔረ ሕያዋን እንዳረገ 2ኛ ነገ
2-7-11 እኛም በጥምቀት ከእግዚአብሔር ተወልደን ገነት መንግሥተ ሰማያት እንገባለን፡፡
ኢዮብ በዮርዳኖስ ተጠምቆ
ከደዌ መፈወሱ ፡- ኢዮብ የምእመናን ፤ ደዌ የመርገመ ሥጋ የመርገመ ነፍስ ፤ ዮርዳኖስ የጥምቀት፤ ኢዮብ በሠይጣን ፈተና ምክንያት
በደዌ ተይዞ ሳለ እግዚአብሔር ከደዌው እንዲድን በዮርዳኖስ ወንዝ እንዲጠመቅ አዞታል ተጠምቆም ድኗል፡፡ ምእመናንም በተጠመቁ ጊዜ
ከመርገመ ሥጋ ከመርገመ ነፍስ ይድናሉ፡፡
v ሦርያዊው አለቃ ንእማን ከለምጹ በነቢዩ ኤልሳ አማካኝነት በዮርዳኖስ ወንዝ ተጠምቆ መዳኑ፡- ንእማን የምእመናን ፤ ለምጽ
የኃጢአት የመርገም ፤ ኤልሳ የካህናት ፤ ዮርዳኖስ የጥምቀት ምሳሌ፡፡ ንእማን ከለምጹ በዮርዳኖስ ተጠምቆ እንደዳነ እኛም በካህናት
አማካኝነት በጥምቀት ከኃጢአት ከመርገም እንድናለን እንፈወሳለን፡፡
የአዳምና የሔዋንን የእዳ ደብዳቤ ለመደምሰስ(ቆላ 2-14)
አዳምና ሔዋን ትዕዛዝ በመተላለፋቸው ከገነት ሲባረሩ ዲያብሎስ አገዛዝ አጸናባቸው፡፡ አገዛዜን እንዳቀልላችሁ ስመ ግብራችሁን
ጽፋችሁ ስጡኝ አላቸው፡፡ እነርሱም “አዳም የዲያብሎስ ባርያ ሔዋን የዲያብሎስ ገረድ” ብለው በ2 እብነ በረድ ጽፈው ሲሰጡት አንዱን
በሲኦል አንዱን በዮርዳኖስ ሸሽጎታል፡፡ ጌታም በዮርዳኖስ በተጠመቀ ጊዜ ይህን የእዳ ደብዳቤ እንደሰውነቱ ረግጦ እንደ አምላክነቱ
አቅልጦ አጥፍቶታል፡፡ በዕለተ ዓርብም ጌታ በአካለ ነፍስ ወደ ሲኦል ወርዶ በሲኦል ያለውንም ደምስሶታል፡፡
ጌታችን ለምን በውሃ ተጠመቀ






መንፈስ ቅዱስ በአምሳለ ርግብ
ለምን ወረደ



የጥምቀት ጥቅም

ሰው በስመ ሥላሴ በሚጠመቅበት
ጊዜ የእግዚአብሔር የፀጋ ልጅነት ያገኛል (ማቴ 18÷19-20) ከእናት ከአባታችን በስጋ አንዴ እንወለዳለን በጥምቀት ደግሞ ዳግመኛ
እንወለዳለን፡፡ የመጀመሪያው ግዙፍ ሁለታኛው ረቂቅ ነው፡፡ የእግዚአብሔር ልጅ ለመሆን ግድ መጠመቅ ያስፈልጋል፡፡ጌታችን ይህንን
ለኒቆዲሞስ ሲያስረዳ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር ወደ መንግሥተ ሰማያት ሊገባ አይችልም ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው ከመንፈስ የተወለደ
መንፈስ ነው (ዮሐ3÷3-6)በማለት አስረድቶታል፡፡
ድኅነት ለማግኘት
ሰው የዘለዓለም ሕይወት የነፍስ
ድኅነት ለማግኘት መጠመቅ አለበት (ዮሐ3÷3-6 ማር 16÷16)
ያመነ የተጠመቀ ይድናል በማለት
ጌታችን ለመዳን ማመን ብቻ ሳይሆን መጠመቅ እንደሚገባ ትእዛዝ ሰጥቶል ለዚህም እንበቃ ዘንድ ጥምቀትን አዘጋጅቶል በምስጢረ ጥምቀት
ድኅነት እንደሚገኝ አምነን እና ተጠምቀን የዘለዓለም ሕይወት መውረስ ይገባል ፡፡
ሥርየተ ኃጢአት
ለማግኝት ይጠቅምል
ጥምቀት ኀጢአትን ያስተሰርያል
በኀጢአት የቆሸሸ ሰውነትንም ይቀድሳል ለዚህ ነው አባቶቻችን በጸሎተ ሃማኖት ላይ ኀጢአት በሚሰረይባት በአንዲት ጥምቀት እናምናለን
ያሉት፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስም በትምህርቱ ያመኑትን ሰዎች ንስሐ ግቡ ኃጢአታችሁ ይሠረይ ዘንድ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ ብሎቸዋል፡፡
ነብዩ ሕዝቅኤልም “ጥሩ ውሃንም እረጭባችኃለሁ እናንተም ተጠራላችሁ ከእርኩሰታችሁም አጠራችሀኆለሁ” በማለት ተናግሮዋል፡፡ (ሕዝ36÷-25
ሐዋ22÷16 አፌ5÷26-27)
ወነአምን በአሐቲ ጥምቀት ለሥርየተ
ኃጢአት
አባቶቻችን ኃጢአትን በምታስተሰርይ
በአንዲት ጥምቀት እናምናለን ማለታችን ጥንተ አብሶ እንደኃጢያት ተቆጥሮ ነው የሚሉ አሉ፡፡ ይህ ግን የክርስቶስን የማዳን አገልግሎት
መገደብ ነው ክርስቶስ ግን ለሁሉም እንደሞተ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ታስተምራለችና መጻሕፍትም ይህንን ይገልታሉና፡፡ ስለዚህም
ክርስቶስ ላመኑትም ላላመኑትም ሞቶ ሕይወት ካቀዳጀ አበው ኃጢአትን በምታስተሰርይ በአንድት ጥምቀት እናምናለን ማለታቸው ለየትኛው
ኃጢያት ነው ቢሉ ለጥንተ አብሶ ሳይሆን ለንዑሰ ክርስቲያን ኃጢአት ነው፡፡ ንዑሰ ክርስቲያን በነበረበት እምነት ኃጢአት ቢሰራ ይህንን
ኃጢአት ጥምቀት ታስወግዳለች ሲል ነው እንጂ አንዳንዶች እንደሚሉት ጥንተ አብሶን አመልካች አይደለም፡፡

ማንም ሰው የቤተ ክርስቲያን አባል
ወይም የክርስቲያን ወገን ለመሆን ቤተ ክርስቲያን ከምትሰጠው ምስጢራት ተካፋይ ለመሆን መጠመቅ አለበት ከሌሎች ምስጥራት አስቀድሞ
ምስጢረ ጥምቀት የሚፈጸመው ያለእርሱ የተቀሩትን ምስጢራት መፈጸም ስለማይቻል ነው፡፡ የተጠመቀ ሰው የእግዚአብሔር ሕዝብ እስራኤል
ዘነፍስ ይሆናል እግዚአብሔር በቤተ ክርስቲያን በኩል የሚያድለውን በረከትና ፀጋ ይካፈላል ከክርሰቶስ መንጋ /ከምዕመናን/ ጋር አንድ
ይሆናል፡፡ (ገላ 8÷24)
ጥምቀት አንዲት ናት
“አንድ ጌታ አንድ ሃማኖት አንዲት ጥምቀት” በማለት ቅዱስ ጳውሎስ የጥምቀትን አንዲትነት በግልጽ
አስቀምጧል (ኤፌ4÷5) እውነተኛ ሃይማኖት አንድ ስለሆነ በዚህ እምነት የምንጠቀመው ጥምቀትም አንድ ሊሆን ግድ ነው፡፡ በጸሎተ
ሃይማኖትም ጥምቀት አንዲት ሰለመሆኗ ”በአንዲት ጥምቀት እናምናለን” በማለት አበው ደንግገውልናል፡፡ጥምቀት አንድ
ብቻ የሆነበት ምክንያት
ከሥጋዊ ወላጆቻችን
የምንወለደው አንዴ እንደሆነ ከመንፈሳዊ አባታችን የምንወለደው መንፈሳዊ ልደታችንም አንድ ጊዜ ብቻ ነው አይደገምም (ዮሐ
3÷6-7)
ለጥምቀት ምሳሌ የሆነው
ግዝረት አንድ ጊዜ ብቻ እንደሚፈጸም ጥምቀትም አንድ ጊዜ ብቻ ይፈጸማል፡፡ (ቆላ 2÷11-13)
ጥምቀት የክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ምሳሌ ነው፡፡ ክርስቶስ የሞተው የተነሣውም አንድ ጊዜ ነው፡፡ እንደዚሁ ሁሉ ጥምቀትም
አንድ ጊዜ ብቻ ይፈጸማል፡፡ (ሮሜ 6÷4)
የጥምቀት ዓይነቶች
ልጅነት የምታሰጠዋ አንዲት ጊዜ ብቻ የምትፈጽመው ጥምቀት በአራት ወገን /ዓይነት/ትከፈላለች፡፡
የውኃ ጥምቀት
የንስሐ እንባ/አንብአ
ንስሐ/
ደመ ሰማዕት
ባሕረ እሳት ናቸው
የጥምቀት ምስጢራዊ ፍቺ ከክርስቶስ ጋር መሞትና መነሣት ነው፡፡ ይህም ቅዱስ ጳውሎስ በጻፈው በሮሜ መልእክቱ እንረዳለን፡፡
(ሮሜ 6÷5) ስለዚህ ለውሃ ጥምቀት ሳይደርሱ በመንገድ ላይ ስለክርስቶስ ሲመሰክሩ በአላውያን ሰይፍ ያለፉት አይድኑም አይባልም፡፡
እነዚህ ሰዎች በደማቸው ወይም እሳት ውስጥ በመጣላቸው ስለክርስቶስ ከክርስቶስ ጋር በመሞታቸው ከእርሱ ጋር ያነሣቸዋል፡፡ ስለሆነም
በክርስቶስ አምነው ሁሉን አሟልተው ነገር ግን በውሃ ሳይጠመቁ ቆይተው ስለክርስቶስ መስክረው የሞቱ በደማቸው የተጠመቁ ስለሆነ ወደ
እሳትም የጣሏቸው እንደሆነ እሳቱ የጥምቀት ባህር ይሆንላቸዋል፡፡ እንደ እውነተኛ ጥምቀትም እንደሚቆጠርላቸው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን
ታስተምራለች፡፡
ይቆየን ይቀጥላል
ስብሐት ለእግዚአብሔር
No comments:
Post a Comment