ሥነ ፍጥረት
ሥነ ፍጥረት ማለት ምን ማለት ነው?
ሥነ ፍጥረት የሚለው ቃሉ የግእዝ ሲሆን ሥነ የሚለው ቃል “ሠነየ” አማረ ውብ ሆነ ማለት ነው፡፡ ፍጥረት የሚለው ደግሞ
“ፈጠረ” አስገኘ፥ ካለመኖር ወደ መኖር አመጣ ማለት ነው፡፡ ሥነ ፍጥረት ማለት ያማረ ፥ ውብ የሆነ ፥ የተደላደለ ፥ መልካም የሆነ
ፍጥረት ማለት ነው፡፡ “እግዚአብሔርም ያደረገውን ሁሉ አየ እነሆ እጅግ መልካም ነበረ” ተብሎ እንደተጻፈ (ዘፍ 1፥23 ፤ 1፥31)
እግዚአብሔር ዓለም ሳይፈጠር አንድነቱ ሦስትነቱን ሳይጠቀልለው ሦስትነቱ አንድነቱን ሳይከፍለው እንደዛሬ ሁሉ በአንድነት
በሦስትነት ሲሠለስ ሲቀደስ ይኖር ነበር ፍጥረት ሳይኖር ማን ያመሰግነው ነበር ቢሉ ምስጋና የባሕርዩ ስለሆነ አንድም ምስጉን ባሕርይ
በቅድምና ስለነበረ ለሦስት ዓላማዎችም ፍጥረታትን ፈጠረ ከፍጥረታት መካከል ሰውና መላእክትን ስሙን ለመቀደስ ክብሩን ለመውረስ የተፈጠሩ
ሲሆን የተቀሩት ፍጥረታት ግን ለአንክሮ ለተዘክሮ ለምግበ ሥጋ የተፈጠሩ ናቸው፡፡ (መዝ 148፥1-3፣ ራዕ4፥11፣ ሐዋ 14፥17፣
ሮሜ 1፥21) ይኸውም ስለአምስት ነገር ፈጥጥታል ከሀሊነቱን ባዕልነቱ ርኩብነቱ ዘኢይትረከብነቱ ራትዕነቱን ለመግለጥ ነው፡፡ ከሀሊነቱ
ይህንን ዓለም እምኀበ አልቦ ኀበ ቦ መፍጠሩ በኋላም እምኀበ ቦ ኀበ አልቦ ማሳለፉ ባዕልነቱ ዛሬ ባለጠጋ ሀሉን ጠርቶ ሲያበላ ሲያጠጣ
ለሁሉ የሚያስፈልገውን እንደሚጋብዝ ጌታም ሰውን ፈጥሮ የሚያስፈልገውን ለመላእክትም እንዲሁ የሚያስፈልጋቸውን አድርጎልና ርኩብነቱ
በሥነ ፍጥረት ይገለጣልና ዘኢይትረከብነቱ ባሕርዩ አይመረመረምና ራትዕነቱ ዲያቢሎስ ቢስት እናዳይመረስ አውቆ ቦታውን ለአዳም ሰጥቶታል
አዳም ቢስት እንዲመለስ አውቆ ቦታውን ለመላእክት አስጠብቆለታል፡፡(ዘፍ. 3÷24)
የፍጥረት መገኛ
እግዚአብሔር ፍጥረታትን ያስገኘው ከኹለት ወገን ነው፡፡


እግዚአብሔር ሥነ ፍጥረትን ያስገኘበት ኹኔታ
እግዚአብሔር ፍጥረታቱን ያስገኘበት መንገድ ኹሉን ቻይነቱ የሚያስረዱ ሲኾኑ ሦስት ናቸው፡፡ እነርሱም እንደሚከተለው ቀርበዋል፡-



የስድስቱ ቀን ሥነ ፍጥረታት
የእሑድ ሥነ ፍጥረት
ዘፍ 1÷1 “በመጀመርያ እግዚአብሔር ሰማይና ምድርን ፈጠረ ››
በዚህ ቀን ሰባቱን ፍጥረታት ፈጥሮአል፡፡ (ኩፍ 2÷8) ማን ማን ናቸው ቢሉ ነፍስ እሳት ውሃ መሬት ጽልመት መላእክት ብሩህ
ሰማይ ናቸው፡፡ እንዲህ ከሆነ ለምን ሰማይና ምድርን ፈጠረ ብቻ አለ ቢሉ
ሁሉም በሰማይና በምድር ውስጥ ያሉናቸውና አጠቃሎ ጠራ
ሰሎሞን እሳተ ኅዩለ ነፉሰ ኅይለ አው ማየ ኅዩለ ይላልና እነዚህ ኃያላን ናቸው ሙሴ እነዚህ ጠቅሶ ቢሆን እነዚህ ኃይል
ሆነውለት ፈጠረ እንዳይሉ ምክንያት ሊያሳጣቸው
ሁሉንም ወደፊት ያነሳቸዋል የጨለማን ተፈጥሮ ወጽልመት መልዕልተ ቀላይ የነፋስን ተፈጥሮ ወመንፈሰ እግዚአብሔር ይጼልል መልዕልተ
መይ ብሎ የመላእክትን ወአዘዞሙ ለኪሩቤል ወለሱራፌል ብሎ (ዘፍ 3÷24)
በዚህ ዕለት ሰባት ፍጥረታት የተፈጠሩ ሲኾን፥ እነርሱም፡-
በመጀመሪያ ሰዓተ ሌሊት - አራቱ ባሕርያተ ሥጋ እና ጨለማ፣
ከኹለተኛው ሰዓተ ሌሊት እስከ ዘጠነኛው ሰዓተ ሌሊት - ከእሳት ሙቀቱን ትቶ ብርሃኑን
ወስዶ ሰባቱ ሰማያትን፣
በዘጠነኛው ሰዓተ ሌሊት ደግሞ መላእክትን ፈጠረ፡፡
እስኪ እያንዳንዳቸውን በመጠን በመጠኑ እንመልከታቸው፡፡
ስለ አራቱ ባሕርያተ ሥጋ
ባሕርይ ማለት የነገር ኹሉ ሥር፣ መገኛ መሠረት ማለት ነው፡፡ ለእግዚአብሔር ሲቀጸል ዘለዓለማዊነቱን ምክንያትና መነሻ የሌለው
መኾኑን የሚያስረዳ ሲኾን ለፍጥረታት ሲቀጸል ደግሞ የዚያ ፍጥረት የመገኘቱ ጥንተ አቋም የሚያስዳ ነው፡፡ እነዚኽ አራቱ ባሕርያተ
ሥጋ የምንላቸውም ከመላእክትና ከነፍስ በስተቀር ሌሎች ፍጥረታት ከእነዚኽ ስለሚገኙ ናቸው /ቅዱስ ኤጲፋንዮስ፣ መጽሐፈ አክሲማሮስ
ገጽ 14/፡፡
አራቱ ባሕርያተ ሥጋ የሚባሉት መሬት ፥ ውሃ ፥ እሳት እና ነፋስ ናቸው፡፡አራቱም ባሕርያት የየራሳቸው ጠባይ አላቸው፡፡




እግዚአብሔር አራቱን ባሕርያትን የፈጠረበት ምክንያት በባሕርዩ አራት ነገሮች እንዳሉ ለመግለጽ ነው፡፡ እነዚህም ኃያልነት
ፈታሒነት መንጽሒነት ባዕልነት ናቸው፡፡
በባዕልነቱ(ባለጸግነቱ) መሬት ትመሰላለች፡፡ ባለጸጋ ሁሉን ያስገኛል መሬትም የምንበላውን የምንጠጣውን የምንለብሰውን ታስገኛለችና
ሀብት ከመሬት ይገኛልና፡፡ ዳግመኛም ምድር ቻይ ናት፤ ፍጥረትን ኹሉ ችላ ትኖራለችና፡፡ “ለምን አረሱኝ፣ ለምን ቆፈሩኝ፣ ለምን ገረፉኝ?” አትልም፡፡ ጌታም ኹሉን ችሎ፣
ታግሦ፣ ሀብቱን ለፍጥረቱ ኹሉ ሳያዳላ ሰጥቶ ይኖራልና፡፡
መንጽሒነቱ በውኃ ይመሰላል፡፡ ይኸውም ውኃ እድፍን ከአካል፣ አካልን ከእድፍ እንደሚለይ ኹሉ ጌታም ነፍስን በጥምቀት ውኃ
ከኃጢአት፣ ኃጢአትንም ከነፍስ ይለያልና፡፡
ኃያልነቱ በእሳት ይመሰላል፡፡ እሳት በተነሣ ጊዜ እርጥቡን ደረቁንም ያቃጥላል፡፡ ባህር ገደል ካልከለለው የብዙ ቀን መንገድ
ሄዶ ያቃጥላል ጌታም ቸርነቱና ርኀራኄው ካልከለከለው በቀር ሁሉን ላጥፋ ቢል ይቻለዋል፡፡
ፈታሒነቱ በነፋስ ይመሰላል፡፡ ገበሬ እህል አጭዶ፣ ወቅቶ በመንሽ ባነሳው ጊዜ ንፋሱ ፍሬውን ከገለባው ይለይለታል ጌታም
ጻድቃንን ከኀጥአን ምዕመንን ከመናፍቃን ይለያልና፡፡
ዘፍ 1÷2 ‹‹ምድርም ባዶ ነበረቸ አንዳችም አልነበራትም ጨለማም በጥልቁ ላይ ነበረ የእግዚአብሔርም መንፈስ በወኃ ላይ
ሰፍፎ ነበር››
የጨለማን ተፈጥሮ አመጣ ጨለማው በውሃው ላይ ሰፍሮ ነበር የነፋስን ተፈጥሮ አመጣ ይጼልል በሚለው ይነፍሕ ይላል አንድ ነው
የእግዚአብሔር መንፈስ በውሃው ላይ ይሰፍፍ ነበር፡፡
መንፈሰ እግዚአብሔር ያለውንም መሻፍቃን የሚባል ሊቅ ለማያት ሕይወት የሚሆናቸው ማያትን የሚያጠራቸው ነፍስ ነው ብሎ ተርጎሞታል፡፡
ኦሪትም በጥምቀት የሚሰጥ የመንፈስ ቅዱስ ምሳሌ ነው ብሎታል፡፡ ሳዊሮስም ከእመቤታችን ደመ ድንግልናዋን የከፈለ የመንፈስ ቅዱስ
ምሳሌ ነው ብሎል ሃይ አ ሳዊ ዘአንጾኪያ ክፍል ዘጠኝ)
እግዚአብሔር ጨለማን መፍጠሩ ጨለማ ውስጥ ያለ ነገር እንደማይታወቅ ኹሉ መሠወሪያውን በጨለማ ያደረገው እግዚአብሔርም በባሕርየ
መለኮቱ እንደማይመረመር /መዝ.16፡11/፤ የሚመረመረው በሃይማኖት ብቻ እንደኾነ እንድናውቅ ነው፡፡
ሰባቱ ሰማያት
“የሰማይ ምጥቀቱ ሳይታይ ሰባቱ ሰማያትም ሳይቆጠሩ” ብሎ እዝራ መናገሩ ሰማያት ሰባት መሆናቸውን እንረዳለን(ዕዝ 4፥4)
እነዚህም
ጽርሐ አርያም ፡- ከሁሉም
በላይ ናት ለመንበረ መንግሥት እንደ ጠፍር ታገለግላለች፡፡ዳር ድንበሯ ከእግዚአብሔር በቀር ማንም አያውቀውም፡፡






ዘፍ 1÷3 ‹‹ እግዚአብሔርም ብርሃን ይሁን አለ መልካም እንደሆነ አየ እግዚአብሔርም ብርሃንና ጨለማን ለየ››
ለይኩን ብርሃን ያለበት ምክንያት ምንድን ነው? ቢሉ ጌታ መላእክትን ሕያዋን ለባዊያን ነባቢይን አድርጎ ፈጥሮቸው ነበርና
ምንተ ንሕነ አይቴ መጻእነ ወመኑ ፈጠረነ ወሚመ በበርእስነኑ ተፈጠርነ ተባባሉ ዲያቢሎስ አሐዜ መንጦላይት ቅሩበ እግዚአብሔር ከሁሉ
በላይ ሆኖ ተፈጥሮልና ከወደላይ ፈጠርኩህ የሚል ድምጽ አጣ ከወደታችም እንዲህ ሲሉ ሰማ እኔ ፈጠርኩ ልበል ብሎ አሰበ አስቦም አልቀረ
አነ ፈጣሪሆሙ ለእሉ ፍጡራን አለ ያጊዜ መላእክቱ ለሦስት ተከፍለዋል አንተ ፈጠርከን ያሉ አሉ ምን አንተ ተትፈጥረን እኛ ፈጠርንህ
እንጂ ያሉ አሉ ያሉ አሉ የተጠራጠሩ አሉ ምን አንተ ተትፈጥረን እኛ ፈጠርንህ እንጂ ያሉ ከዲያቢሎስ ጋር ወድቀዋል፡፡ ያን ጊዜ
በመላእክት ከተማ ሽብር ሆነ ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት ንቁም በበኅላዌነ እስከንረክቦ ለአምላክነ ብሎ አጽንቶቸዋል፡፡ ለብስራትም
ያበቃው ይህ ነው፡፡
በኋላም ጨርሰው ሳይክዱ ለይኩን ብርሃን ብሎ ተገለጠላቸው ይህም ብርሃን እውቀት ሆኗቸው ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ብለው አመስግነውታል፡፡
ስለምን ብርሃንን በነቢብ ፈጠረ ቢሉ


በፊት ጨለማን ፈጥሮ በኋላ ብርሃንን ለምን ፈጠረ ቢሉ
በፊት ብርሃንን ቢፈጥር
ሠናይ አምላክ ብርሃን እኩይ አምላክ ጨለማን ፈጠረ ባሉ ነበር ምክንያት ለማሳጠት
የሚያሰስፈልገውን በፊት የማያስፈልገውን በኋላ መፍጠር ክፉውን በፊት በጎውን በኋላ ማምጣት ለጌታ ልምዱ ነውና በፊት የሚያልፈውን
ምድር አውርሶ በኋላ የማያልፈውን መንግስተ ሰማያትን እነዳወረሰን በፊት የምታልፈውን ኦሪት በኋላ የማታልፈውን ወንጌል እንደሠራልን
በፊት መከራውን በኋላ ጸጋውን ክፍሩን እንደሚያወርሰን
ሌሎች ይህንን ይዘው በዚህ ዕለት የፈጠረው ስምንት ፍጥረት ነው ይላሉ ነገር ግን ኩፍሌ ወገብረr እግዚአብሔር ሰብዓተ ዘመደ
ይላልና በዚህ ይረታሉ፡፡ ይህም ብርሃን ከሰባቱ ልዩ አይደልም የተዳፈነ እሳት በጭድ በገለባ እንዲገለጡ በእሳት ባሕርይ ተሰውሮ
የነበረውን መግለጥ ነው፡፡
መላእክት
መልአክ የሚለው የግእዝ ቃል ኹለት ትርጉሞች አሉት፡፡ አንደኛው አለቃ፣ ሹም ማለት ነው፡፡ በዮሐንስ ራእይ ላይ የምናገኛው
ሰባቱ የአቢያተ ክርስቲያናት አስተዳዳሪዎች መላእክት ተብለው መጠራታቸውም ከዚህ አንጻር ነው /ራእ. 2 እና 3/፡፡ ኹለተኛውና
ከተነሣንበት ርእስ አንጻር ስናየው ደግሞ መልክእተኛ፣ የተላከ የሚል ትርጕም አለው /ዕብ.1፡14/፡፡ ይኸውም የመላእክት ተግባር
ምን እንደኾነ የሚያስረዳ ቃል ነው፡፡ መላእክት ከእግዚአብሔር ወደ ሰው፥ ከሰውም ወደ እግዚአብሔር የሚላላኩ መናፍስት ናቸውና፡፡
መላእክት በሌላ ስማቸው የሰማይ ሠራዊት ተብለው ይጠራሉ፡፡
መላእክት ኹለት ወገን ናቸው፡፡ ብርሃናውያን መላእክትና የጨለማ አበጋዝ የኾነው የዲያብሎስ ሠራዊት የኾኑት እኩያን መላእክት፡፡
ስለዚህ የእግዚአብሔርን መላእክት ከሌሎቹ መላእክት በአጠራር የምንለያቸው ቅዱስ በሚል ቅጽል ነው፡፡
ከሰባቱ ሰማያት በኋላ መፈጠራቸው ለምን እንደኾነ አክሲማሮስ ሲገልጥ፡- “በፊት ፈጥሯቸው ቢኾን እኛም አብረነው ፈጠርን፤
ያዝንለት፤ ተራዳነው ባሉ ነበር፡፡ አንድም ርሱ ቢመሠርት እኛ ገነባን፤ ርሱ ቢገነባ እኛ መሠረትን ባሉ ነበር፡፡ ይህም ሳጥናኤል
በኋላ እኔ ፈጠርኳችኁ እንዳለው ማለት ነው” ይላል፡፡ ተፈጥሮአቸውም ካለ መኖር ወደ መኖር ነው፡፡ መላእክት እንደ እሳት የሚሞቁ፣
እንደ ነፋስ የሚረቁ ስለ ኾነ፤ አንድም እንደ እሳት እንደ ነፋስ ፈጣኖችና የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚፈጽሙ ኃያላን ስለኾነ ባሕርያቸውን
ለመግለጥ ከነፋስና ከእሳት ተፈጠሩ ይባላሉ /መዝ.103፡4፣ መዝሙረ ዳዊት ንባቡ ከነትርጓሜው፣ ገጽ 489 /፡፡
መላእክት ስንት ወገን ናቸው?
መላእክት ኹለት ወገን ናቸው፡፡ ብርሃናውያን መላእክትና የጨለማ አበጋዝ የኾነው የዲያብሎስ ሠራዊት የኾኑት እኩያን መላእክት፡፡
ስለዚኽ የእግዚአብሔርን መላእክት ከሌሎቹ መላእክት በአጠራር የምንለያቸው ቅዱስ በሚል ቅጽል ነው፡፡
መላእክት መቼ ተፈጠሩ?
መላእክት የተፈጠሩት በመዠመሪያው ቀን ነው /ኩፋ.2፡7-8/፡፡ መዝሙረኛው ክቡር ዳዊትም ይኽን በማስመልከት፡- “በእግዚአብሔር
ቃል ሰማያት ተፈጠሩ፤ የሰማይ ሠራዊትም ኹሉ በአፉ እስትንፋስ” ይላል /መዝ.32፡6/፡፡
ምንም እንኳን በመዠመሪያው ቀን የተፈጠሩ ቢኾኑም ግን ከአራቱ ባሕርያተ ሥጋና ከሰባቱ ሰማያት በኋላ
በ9ኛው ሰዓተ ሌሊት ነው የተፈጠሩት፡፡ ይኽ ለምን እንደኾነ ቅዱስ ኤጲፋንዮስ አክሲማሮስ በተባለ መጽሐፉ ላይ፡- “በፊት ፈጥሯቸው
ቢኾን እኛም አብረነው ፈጠርን፤ ያዝንለት፤ ተራዳነው ባሉ ነበር፡፡ አንድም ርሱ ቢመሠርት እኛ ገነባን፤ ርሱ ቢገነባ እኛ
መሠረትን ባሉ ነበር፡፡ ይኽም ሳጥናኤል በኋላ እኔ ፈጠርኳችኁ እንዳለው ማለት ነው” በማለት ያብራሯል /አክሲማሮስ ዘእሑድ፣ ገጽ
24/፡፡
አንዳንድ ሊቃውንት መላእክት ከሰው በፊት ስለተፈጠሩ የሰው ታላላቅ ወንድሞች ናቸው ይሏቸዋል፡፡
ተፈጥሮአቸውም ካለ መኖር ወደ መኖር ነው፡፡ መላዕክት እንደ እሳት የሚሞቁ፣ እንደ ነፋስ የሚረቁ ስለ ኾነ /ዝኒ ከማኁ/
አንድም እንደ እሳት እንደ ነፋስ ፈጣኖችና የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚፈጽሙ ኃያላን ስለኾነ ባሕርያቸውን ለመግለጥ ከነፋስና ከእሳት
ተፈጠሩ ይባላሉ /መዝ.103፡4፣ መዝሙረ ዳዊት ንባቡ ከነትርጓሜው፣ ገጽ 489 /፡፡
ተ.ቁ
|
የማዕረግ አይነት
|
ሊቀ መላእክት
|
የተሾመበት ሰዓት
|
የሚገኙበት ከተማ
|
1
|
መላእክት ዘኢየሩሳሌም
|
‹‹ሳጥናኤል››
|
3
|
ኢየሩስአሌም ሰማያዊት
|
2
|
ኪሩቤል
|
ኪሩብ
|
4
|
ኢዮር
|
3
|
ሱራፌል
|
ሱራፊ
|
5
|
ኢዮር
|
4
|
ኃያላት
|
ቅዱስ ሚካኤል
|
6
|
ኢዮር
|
5
|
አርባብ
|
ቅዱስ ገብርኤል
|
7
|
ራማ
|
6
|
መናብርት
|
ቅዱስ ሩፋኤል
|
8
|
ራማ
|
7
|
ሥልጣናት
|
ቅዱስ ሱርኤል
|
9
|
ራማ
|
8
|
መኳንንት
|
ቅዱስ ሰዳካኤል
|
10
|
ኤረር
|
9
|
ሊቃናት
|
ቅዱስ ሰላታኤል
|
11
|
ኤረር
|
10
|
መላእክት
|
ቅዱስ አናንኤል
|
12
|
ኤረር
|
ይቆየን ይቀጥላል
ስብሐት ለእግዚአብሔር
No comments:
Post a Comment