ሁለት ባሕርይ ትምህርትና የአንድ ባሕርይ ትምህርት
የልዩን ጦማር ፍጽም ክህደትና የንስጥሮስን ትምህርት በመድገም ዳግመኛ የአባቶቹን ድንበር ያፈረሰ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ጦማሩን
የተመለከተው ንስጥሮስም የክህደቱ ትምህርት ስለሰመረለት የሮምን ቤተ ክርስቲያን አወድሶል፡፡ ጦመሰሩ በአጭሩ ክርስቶስ ሁለት ባሕርይ
ሁለት ሕላዌ አንድ አካል አለው የሚል ነው፡፡ በልዩን ፍልስፍና አካልና ባሕርይ የተለያዩ ናቸው የሚል ነው፡፡
አባቶቻችን ከአካል የተለየ ባሕርይ የለም ከባሕርይ የተለየ አካል የለም ብለው አስተምረውናል፡፡ ከአካል የተለየ ባሕርይ
ከሌለ ደግሞ ሁለት ባሕርይ ካልን ሁለት አካል ወደሚል ትምህርት ይወስደናል፡፡ ይህ ትምህርት ደግሞ የንስጥሮስ ትምህርት ነው ይህ
የንስጥሮስ ትምህርት ታዲያ ቀድሞ በአባቶቻችን በጉባኤ ኤፌሶን የተወገዘ ነው፡፡ወይም አካልን አንድ ካልን በባሕርይም አንድ ወደ
ማለት ይመራናል ይህም እንደ ቅዱስ ቄርሎስ ነው፡፡ ሁለቱ ባሕርያት በመተባበር የየራሳቸውን ድርሻ ይሰራሉ ‹‹መለኮት ይገብር ግብረ
መለኮት ትስብእት ይገብር ግብረ ትስብአት›› የሚል ጦማር ነበር፡፡ይህም ጦማር ተአምራት ያደረገው መለኮት መከራን የተቀበለው ሥጋ
ብሎ ያስተምራል፡፡
የኬልቄዶን ጉባኤ የተሳታፊዎች ቁጥር 636 ሲሆን ይህም የሆነበት ምክንያት ከቀድሞ ጉባኤያት ሁሉ
ታላቅ ጉባኤ ለማስመሰል ነው፡፡ በዚህ ጉባኤ ላይ ከዚህ በፊት የንስጥሮስን ትምህርት በመደገፋቸው ምክንያት የተወገዙ ሰዎች ጭምር
የተሳተፉበት በመሆኑ በአባቶች ዘንድ ግርታን ፈጥሮል፡፡ ቅዱስ ዲዮስቆሮስም የእስክንድርያን አብያተ ክርስቲያናትን ወክሎ በጉባኤው
ላይ ተገኘ፡፡ የጉባኤያቱ አባላትም ተቃውሞ አጸኑበት ተከሳሽም አደረጉት የአውጣኪ ትምህርት ደጋፊ ነህ ውጣ አሉት፡፡ ቅዱሱም መንበሩን
ለማስከበር ሲል ወጣ ይህንን የአርመን የሕንድና የሶርያ አብያተ ክርስቲያናት ተቃወሙ፡፡ ግሪኮቸቹና የምዕራብ አብያተ ክርስቲያናት
ግን ከምሥራቃዊያኑ ጋር ተባበሩ፡፡የካቶሊክ ትምህርት ይህን የልዮንን ምፍቅና የሚከተል ነው ይህም ለንስጥሮስ ትምህርት እጅግ የቀረበ
ሐሳብ ነው፡፡ የትምህርቱ ሐሳብ ልዮነት ሰፋ ያለና ከላይ በሚገባ ያብራራነው ቢሆንም ቅሉ በዋነኝነት ግን ሁለት ባሕርይ(In
two natures) በሚለው ምትክ ከሁለት ባሕርይ(from two natures) ብንለው ሚስተካከል እንደሆነ ልብ ልንል ይገባናል፡፡
የንስጥሮስ ትምህርት
|
የአውጣኬ ትምህርት
|
የቅ/ዲዮስቆሮስ ትምህርት
|
የልዮን ትምህርት
|
ሁለት ባሕርይ
ሁለት ፍቃድ
ሁለት አካል
|
አንድ ባሕርይ
አንድ አካል
በመጠፋፋት
|
አንድ ባሕርይ
አንድ አካል
በተዋሐዶ
|
ሁለት ባሕርይ
አንድ አካል
|
የተንሸዋረረው እይታ መነሻ
የዚህ ትምህርት መነሻ ክርስቶስ
የሚለው ቃል ትርጉም ነው፡፡ ክርስቶስ ማለት የተቀባ የነገሠ የከበረ ማለት እንደሆነ በመገንዘብ የተቀባ የሚለውን የቃል ትርጉም
በመውሰድ ቅድም በአራቱ ነጥቦች ላይ እንዳስቀመጥነው ‹‹አብ ቀባዒ ወልድ ተቀባዒ መንፈስ ቅዱስ ቅብዕ›› የሚል በመሠረተ እምነት
ላይ ተፋልሶ የሚፈጥር ትምህርት ነው ቅብዓት
ተዋሕዶ በመጠባበቅ(በተአቅቦ)
በምሥጢረ ተዋሕዶ ውስጥ ልናሳው የሚገባው ቁምነገር ተዓቅቦ ያለመሆኑን ነው፡፡ ተዐቅቦ እንደ ድያድርስ እንደንስጥሮስ እንደአውጣኬ
በመቀላለቀል ሳይሆን በተዋሕዶ ሥጋ ከመለኮት ጋር ተዋሐደ ስንል ባሕርይውን ማለትም ግዙፍነቱን ውስንነቱን አጭርነቱን ደካማነቱን
መዋቲነቱን ወዘተ ሳይለቅ ከመለኮት ጋር ተዋሐደ እንላለን፡፡ ለመለኮትም እንዲሁ ነው ያለመቀላቀል ያለመለያት መለኮት የሥጋን ሥጋም
የመለኮትን ባሕርይ ገንዘብ አደረገ እንላለን
እኛ ተአቅቦ ስንል በመጠባበቅ ያለመጠፋፋት ለማለት ነው፡፡ ይሀም ማለት እንደብርዝ በመቀላቀል ውኃ ማሩን አሟልቶ ማሩን
ውኃውን አጣፍጦ እንደሚሆነው አይደለም፡፡ እንደቡናና ወተት ወተቱ ቡናውን አንጽቶት ቡናው ወተቱን አጥቁሮት ስም ማዕከላዊ መላክ ማዕከላዊ እናደሚያሳይ ሳይሆን ረቂቁ ሲገዝፍ ምልዑም ሲወሰን የቀደመ ምልዐቱ ርቀቱ ሳይቀርም ሥጋም በተዋሕዶ ሲረቅ ሲመላ የቀድሞ ግዙፍነቱ ውስንነቱ ሳይቀር ማለት ነው፡፡
ይቆየን ይቀጥላል
ስብሐት ለእግዚአብሔር
No comments:
Post a Comment