ተዋሕዶ
ተዋሕዶ ማለት አንድ መሆን ማለት ነው፡፡ አንድም ከሁለት አካል አንድ አካል
ከሁለት ባሕርይ አንድ ባሕርይ መሆን ነው፡፡ አምላክ ሰው ሆነ የሰውነት ባሕርይን ገንዘብ አደረገ፡፡ ከኃጢአት በስተቀር የሰውነት
ሥራ ሁሉ ሠራ ፡፡ ሰውም አምላክ ሆነ አምላካዊ ባሕርይን ገንዘብ አደረገ አምላካዊን ሥራን ሠራ (ዕብ 4÷ 15) የሥጋ የመለኮት
ባሕርይ ምንድን ነው ቢሉ
ከተዋሕዶ በፊት
|
በተዋሕዶ አንድ የሆነው
ኢየሱስ ክርስቶስ
|
|
የቃል ገንዘብ
|
የሥጋ ገንዘብ
|
|
ፈጣሪ ነው
|
ፍጡር ነው
|
ሲፈጥር ታይቷል(ዮሐ 9÷6-8
|
ከአብ የተወለደ
|
ከአፈር የተፈጠረ
|
ከድንግል ተወለደ( ሉቃ 2÷7)
|
ሕግ አውጪ ነው
|
ሕግ ፈጻሚ ነው
|
ሕግን ሠራ (ማቴ 5÷17-44) ሕግን ፈጸመ (ሉቃ 2÷23-24)
|
ዘመን አይቆጠርለትም
|
ዘመን ተቆጠረለት
|
ዘመን ተቆጠረለት በየጥቂቱም አደገ እኔ ቀዳማዊ ነኝ አለ (ሉቃ 2÷42 2÷52) (ዮሐ 1÷
1-2)
|
አዛዥ ነው
|
ታዛዥ ነው
|
ታዘዘ፤ አዘዘ )ሉቃ 2÷52) (ማቴ 20÷8)
|
ሁሉን ያውቃል
|
እውቀት ተከፍሎ አለበት
|
አልዓዛር መሞቱን አወቀ (ዮሐ 11÷13) አልዓዛር የተቀበረበትን ጠየቀ
|
አያንቀላፋም
|
ያንቀላፋል
|
አንቀላፋ(ማር 4÷35-39) (ሉቃ 8÷22)
|
አይራብም
|
ይራባል
|
ተራበ (ማቴ 3÷3) የተራቡትን በበረከት አጠገበ (ሉቃ 9÷10-17)
|
አይጠማም
|
ይጠማል
|
ተጠማ (ዮሐ 19÷29) የሕይወት ውሃን ሰጠ (ዮሐ 7÷37)
|
አይደክምም
|
ይደክማል
|
ደከመ(ሉቃ 22÷44)
|
ረቂቅ ነው
|
ግዙፍ ነው
|
ታየ ተዳሰሰ (1ኛ ዮሐ 1÷1) ተሰወረ (ዮሐ 8÷59) በባሕር ላይ ተራመደ (ማቴ
10÷25)
|
ምሉዕ ነው
|
ውሱን ነው
|
ከአብ ቀኝ ሳይለይ ከድንግል ተወለደ (ሉቃ 2÷7)
|
ሕያው ነው
|
መዋቲ ነው
|
ሞት ይይዘው ዘንድ አልቻለም (ሐዋ 2÷24)
|
እንደ ቤተ ክርስቲያናችን ትምህርት በተዋሕዶ የቃል ገንዘብ ለሥጋ የሥጋ ገንዘብ ለቃል ሆነ ማለት ቀዳማዊ ያልነበረው ሥጋ
ቀዳማዊ ሆነ፡፡ ረቂቅ የነበረው መለኮት በሥጋ ታየ ተዳሰሰ የማይራበው ተራበ የማይጠማው ተጠማ ዘመን የማይቆጠርለት መለኮት ዘመን
ተቆጠረለት ዘመን የሚቆጠርለት ሥጋ ዘመን የማይቆጠርለት ሆነ፡፡ ሁለቱ አካላት አንዱ አንዱን ሳያጠፋው ሳይለውጠው ያለመቀላቀል ያለመደራረብ
በተአቅቦ(በመጠባበቅ) አንድ መሆን ተዋሕዶ ይባላል፡፡
የማይመረመር የማይለወጥ ቃል የሚለወጥ ሥጋን ተዋሕዶ መለወጥ ይስማማው የነበረን ሥጋን የማይለወጥ አደረገው፤ መለኮት በተዋሕዶ
በሥጋ ተገለጠ ፡፡ የማይለወጥ ባሕርይ ያለው ቃል የሚለወጥ ባሕርይ ባለው በሥጋ ሞቶ የአዳምን ዘር ሁሉ አዳናቸው፡፡ (ዮሐ 1÷
14፤ 1ኛ ጢሞ 3÷ 16፤1ኛ ጴጥ 3÷ 21፤ፊሊ 2÷ 6-8፤ ሃይ.አበ.ገፅ 23÷ 13)
ቅዱስ ኤፍሬም እመቤታችንን ባመሰገነበት ውዳሴው “…. ሰው የማይሆን ሰው ሆኗልና ቃል ተዋሕዷልና ጥንት የሌለው ሥጋ ጥንታዊ
ቀዳማዊ ሆነ ዘመን የማይቆጠርለት መለኮት ዘመን ተቆጠረለት የማይታወቅ ተገለጠ የማይታይ ታየ የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ በእርግጥም
ሰው ሆነ፡፡ ትናንት የነበረው ዛሬም ያለው መቼም የሚኖረው ኢየሱስ ክርስቶስ እንሰግድለትና እናመሰግነው ዘንድ አንድ ባሕርይ ነው”
ሲል እንደ ተናገረ (ውዳሴ ማርያም ዘረቡዕ)
እንደዚህ ሁሉ ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ “ ምን እላለሁ ምንስ እናገራለሁ ከዘመን አስቀድሞ የነበረ እርሱ ትንሽ ሕፃን
ሆኗልና እኔ ፈጽሜ አደንቃለሁ ከሰማየ ሰማያት በላይ የሚሆን በዘለዓለማዊ ዙፋን የሚኖር እርሱ በበረት ተጣለ ከሥጋዌ አስቀድሞ አይዳሰስ
የነበረ አንድ እርሱ በምድራዊያን እጅ ተዳሰሰ ኀጢአትን የሚያስተሰርይ እርሱን በጨርቅ መጠቅለሉን ይህን ወዷልና ክብሩ ተለይቶት
የነበረ ሥጋን ክቡር አምላክ ሊያደርገው የፀጋ ገዢነትን አጥቶ የነበረን ሥጋንም የባሕርይ ገዢ በመሆን ሊገልጠው ወደደ ›› ሲል
እንደተናገረ
የተዋሕዶ ምሳሌዎች በመጽሐፍ
ቅዱስ
ዕፀ ጳጦስ (ዘፀ
3÷ 2)


ነበልባሉ ከቁጥቋጦው ተዋሕዶ ነበልባሉ ሐመልማሉን ሳያቃጥለው ሐመልማሉ ነበልባሉን ሳያጠፋው መገለጹ አካላዊ ቃል እግዚአብሔር
ወልድ በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ማሕጸን ባደረ ጊዜ እመቤታችን እሳተ መለኮቱ ሳያቃጥላት ከእርሷም የነሣውን ሥጋ እና
ነፍስ ሳይለውጠው የመዋሐዱ ምሳሌ ነው፡፡ ሐመልማሉ ነበልባሉን እንዳላጠፋው የቅድስት ድንግል ማርያም ሥጋ እሳተ መለኮት ሳይሽረው
ሳይለውጠው የመዋሐዱ ምሳሌ ነው፡፡ ሐመልማል ከነበልባል አንዱ አንዱን ሳያጠፋ እንደታዩ ሥጋ ከመለኮት ጋር ሳይጠፋፉ አንድ የመሆናቸው
ምሳሌ ነው፡፡
የኢሳይያስ ፍሕም ኢሳ
6÷6


ነቢዩ ኢሳይያስ ባለመታዘዙ ምክንያት የተነሣ ከንፈሩ ለምጽ ወጥቶበት በፍሕም እንደዳነ መጽሐፍት ይመሰክራሉ፡፡ እሳቱ ተለውጦ
ከሰል ፤ ከሰሉ ተለውጦ እሳት አልሆነም፡፡ ሁለቱም ከሰል ከሰልነቱን እሳትም እሳትነቱን ሳይለቅ ተዋሕደው ፍሕም ሆነዋል፡፡ በፍሕም
ውስጥ እሳት እና ከሰል ፈጽሞ ሊለዩ በማይችሉ ተዋሕዶ አንድ ሆነዋል፡፡ የመለኮት እና የሥጋ ተዋሕዶ እንዲህ ነው፡፡ መለኮት መለኮታዊ
ባሕርዩን ሳይለቅ ሥጋም ሥጋዊ ባሕርዩን ሳይለቅ በተዋሕዶ የተገለጸው ኢየሱስ ክርስቶስ (ሥግው ቃል) አዳም ከበደሉ ከሞቱ የማዳኑ
ምሣሌ ነው፡፡
የተዋሕዶ ምሳሌዎች በሥነ ፍጥረት
የጋለ ብረት
ታላቁ የቤተክርስቲያን አባት ቅዱስ ቄርሎስ የነገረ ሥጋዌን ነገር በጋለ ብረት መስሎ አስተምሯል፡፡
አንድን ብረት ከእሳት ባስገቡት ጊዜ ብረትነቱን ሳይለቅ እሳቱም እሳትነቱን ሳይለቅ በብረቱ ቅርፅ ልክ እሳት ይሆናል፡፡
ይህንንም እሳትና ብረቱ ስለተዋሐዱ የጋለ ብረት ብለን እንጠራዋለን እንጂ ብረት ወይም እሳት ብቻ ብለን አንጠራውም፡፡ በመጋዝ እንኳን
ብረቱን ብንተረትረው እሳቱ ፍጹም ተዋሕዶት እናገኘዋለንና፡፡ የአካላዊ ቃል እና የትስብዕት(የሥጋን) ተዋሕዶ እንዲሁ ነው፡፡
ከተዋሕዶ በኋላ ሁለትነት የለም አንዱን አካል ያን ይሰራል አንለውም ፍፁም ተዋሕደዋልና ነገር ግን በዚህ ምሳሌ ማስተዋል
ያለብን ብረቱ ከእሳቱ ወጥቶ ከበረደ በኋላ ምሳሌው ለተዋሕዶ ማሳያ ሊሆን አይችልም፡፡
የሰው ነፍስና ሥጋ
የሰው ልጅ ከእናቱ ማሕፀን ሥጋና ነፍስን ነስቶ ፅንስ ከሆነበት ቀን ጀምሮ ይህ ነፍስ ነው ይህ ሥጋ ነው ብሎ መለያየት
እንደማይቻል ሁሉ ሥጋና መለኮትም ከተዋሕዶ በኋላ ይህ ሥጋ ነው ይህ መለኮት ነው ፤ ይህ ሥጋዊ ሥራ ነው ይህ መለኮታዊ ሥራ ነው
ተብሎ መክፈል አይቻልም፡፡ ነፍስ ረቂቅነቷን ለቃ ሳትገዝፍ ሳትለውጥ ሥጋም ግዙፍነቱን ለቆ ሳይረቅ እንደተዋሐደ መለኮትም ርቀቱን
ምልዐቱን ትቶ ሳይገዝፍ ሥጋም ግዙፍነቱን ውሱንነቱን ለቆ ሳይረቅ በመጠባበቅ አንድ አካል አንድ ባሕርይ ለመሆናቸው ምሳሌ ነው፡፡
ይቆየን ይቀጥላል
ስብሐት ለእግዚአብሔር
No comments:
Post a Comment