Saturday, 15 July 2017

ነገረ ሃይማኖት ክፍል አራት




የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ዶግማ(መሠረተ እምነት) ምንጮች

† ዓለማቀፍ የጉባኤያት
አብያተ ክርስቲያናት እስከ አራተኛው ክፍለ ዘመን ድረስ አንድ ነበሩ፡፡ መሠረተ እምነትን(ዶግማን) የሚቃረኑ የመናፍቃን ትምህርት በሚገጥሙ ጊዜ የአብያተ ክርስቲያናት መሪዎች እየተሰበሰቡ ውሳኔዎችን ይደነግጉ ነበር፡፡ ይህም ሥርዓት የተጀመረው በሐዋርያት ዘመን ነው 51 ዓ.ም. ይህም እስከ አራተኛውመቶ ክፍለ ዘመን የቀጠለ ነው፡፡
የኢየሩሳሌም ጉባኤ4የመጀመርያው ጉባኤ ነው፡፡ አረማዊያን ወደ ክርስትና በቅዱስ በርናባስ አማካኝነት ከተመለሱና በአንጾክያ ቤተ ክርስቲያን ከመሠረቱ በኋላ አንዳንድ አማኞች በመነሳት የሙሴን ሕግ መፈጸም ይገባል በማለት ሁከት ባስነሱ ጊዜ ይህን በተመለከተ ውሳኔ ለመስጠት ሐዋርያት ተሰብስበዋል፡፡5
ይህ ጉባኤ ምንም እንኳን እንደዓለማቀፋዊ ጉባኤ ባንጠቅሰውም የሐዋርያትን ሃይማኖታዊ ጥያቄዎችን ለመመለስ በጉባኤ በመሰብሰብ ውሳኔ ማሳለፋቸው የቤተ ክርስቲያን የጉባኤ ትውፊት ከሐዋርያቱ ጀምሮ የነበረ መሆኑን ያመለክታል፡፡6
የተላለፉ ውሳኔዎች
1. ለጣዖት በመሠዋቱ ምክንያት ረከሰ ምግብ አትብሉ
2. ታንቆ የሞተ እንስሳ አትብሉ
3. ከዝሙት ተጠበቁ የሚሉ ናቸው

ይህ ጉባኤ በሙሴ ሥርዓተ ሕግ ላይ ያተኮረና በወቅቱ ለነበረው ጥያቄ መልስ የሰጠ ነበር፡፡ከዚህ በኋላ የተደረጉ ጉባኤያት ግን መሠረተ እምነት ላይ መሠረት ያደረጉ ነበሩ፡፡ በተለያዩ ጊዜ የተነሱ መናፍቃንን ትምህርታቸውን በመመርመር በጉባኤያቱ ትምህርታቸው እንዲቀርብ በራሳቸው አንደበት ጭምር በመጋበዝ ከመጻሕፍት ከጌታችን ትምህርት ልዩ የሆነውን በመለየት ውሳኔዎችን አሳልፈዋል፡፡
ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በብዙ የታሪክ ምዕራፎች አልፋለች ብዙ ውሳኔዎችንም አሳልፋለች፡፡ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት የተደረጉ የአባቶቻችን የጉባኤ ውሳኔም ምዕመናንን ከምንፍቅና የሚጠብቅ ሆኖል፡፡ እነዚህ ጉባኤያት ታዲያ ለመናፍቃኑ መልስ የሰጡ ናቸው ለዚህ ነው ጉባኤያት ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን መሠረተ እምነት መሠረት ናቸው የምንላቸው፡፡
ኦርቶዶክሳዊት ቅድስት ቤተ ክርስቲያንም ሦስት ዓለም አቀፍ ጉባአያትን ትቀበላለች፡፡ በ325 ዓ.ም. የመጀመርያው ጉባኤ በኒቅያ በ381 ዓ.ም. የቁስጥንጥንያ ጉባኤ እንዲሁም በ451 ዓ.ም. ደግሞ ሦስተኛው ጉባኤ በኤፌሶን ተካሂዶል፡፡ በዚህም ጉባኤ የአበው ሃይማኖት ምን እንደምትመሥል አይተናል የትኛውስ ሐሰት ነው የሚለውን ተመልክተናል ስለዚህም ዳግመኛ በዚህ ስህተት አንገኝም የአባቶቻችንን መንገድ እንከተላለን እንጂ፡፡
የተደረጉበት ዓመት
ጉባኤያቱ
የተወገዘው ትምህርት
325 ዓ.ም.
ጉባኤ ኒቂያ
አርዩስ
ወልድ ፍጡር ነው
381 ዓ.ም.
ቁስጥንጥንያ
አቡናርዩስ
አውሳብዮስ
መቅዶንዩስ
431 ዓ.ም.
ኤፌሶን7
ቢላግዩስ
ንስጥሮስ


† ጉባኤ ኒቅያ

የአርዮስ ኑፋቄ

ወልድ ባልነበረበት ጊዜ አብ ነበረ አብ ወልድን ከምንም ፈጠረና የእግዚአብሔር ልጅ እንዲሆን አደረገው ይህም መለት እግዚአብሔር አብ ወልድን እንደማንኛውም ፍጥረት ፈጥሮታል በኋላም ሥልጣን ስለሰጠው ፈጥሮ ፈጥሮበታል ብሎ አስተማረ፡፡

ፈጥሮ ፈጠረበት?

ለዚህ ትምህርቱ መነሻ የሆነው ኃይለ ቃል ምሳ 8፥26 ትቤ ጥበብ ፈጠረኒ መቅድመ ኩሉ ተግባሩ ጥበብ ከፍጥረታት ሁሉ እስቀድሞ እኔን ፈጠረችኝ በማለት ጥበብ የተባለ ወልድ ነው ብሎ አስታማረ
የአርዩስ ትምህርት የተቀዳው ከማን ነው?
አርዩስ ትምህርቱን የቀዳው ከፈላስፎቹ አፍላጦንና አሪስጣጣስ ሲሆን እነዚህ ፈላስፎች ዓለም የተፈጠረው በራሱ በእግዚአብሔር በቀጥታ ሳይሆን እግዚአብሔር በፈጠራቸው መናፍስት ወይም ኃይሎች አማካኝነት ነው ብለው አስተምረዋል፡፡ ይህን ትምህርት አርዮስ አዲስ ቅርጽ በማስያዝ መናፍስት ያሏቸውን ክብር ይግባውና ወልድ ነው በማለት የእነዚህን ‹‹ፈላስፎች›› ትምህርት መጽሐፋዊ በማድረግ ብዙዎችን አስቷል፡፡
የአባቶች መልስ
አባቶቻችን ጸሎተ ሃይማኖትን እስከ ሰባተኛው አንቀጽ ድረስ የነገጉት በዘህ ጉባኤ ላይ ነው ይህም ፍጹም መጽሐፋዊና ለመሠረተ እምነታችንን ማሳያ ነው፡፡ ይህን የጸሎተ ሃይማኖት ክፍል ጥንታዊያን ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት ሲጠቀሙት የምሥራቅ አብያተ ክርስቲያናት(ከግሪካዊያን ውጪ)ና ካቶሊካዊያን እናምናለን በሚለው ፈንታ አምናለሁ ብለው ቅርጹን ቀይረው ይጠቀሙበታል፡፡ሌላው ልዩነት ከአብ የሰረጸ የሚለውን ካቶሊካዊያኑ ከአብና ከወልድ የሰረጸ ብለው ቀይረውታል፡፡
የሃይማኖት መሠረት
ሁሉን የፈጠረ አንድ አምላክ በሚሆን በእግዚአብሔር እናመናለን
ሰማይና ምድርን የፈጠረ የማይታየውንና የሚታየውን ዓለም ሳይፈጠር ከእርሱ ጋር የነበረ
አንድ የአብ ልጅ በአንድ ጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እናምናለን
ከብርሃን የተገኘ ብርሃን ከእውነተኛ አምላክ የተገኘ እውነተኛ አምላክ
የተወለደ እንጂ ያልተፈጠረ በባሕርዩ ከአብ ጋር የሚስተካከል ሁሉ በእርሱ የሆነ
በሰማይም በምድርም ካለው ያለእርሱ ምንም ምን የሆነ የለም
ስለእኛ ስለሰዎች እኛን ለማዳን ከሰማይ ወረደ 8
በመንፈስ ቅደስ ግብር ከቅድስት ድንግል ማርያም ፍጹም ሰው ሆነ
ደግሞ ስለእኛ ተሰቀለ ሞተ ተቀበረ በሦስተኛው ቀን ከሙታን ተነሣ
በቅዱሳን መጻሕፍት እንደተጻፈ በክብር ወደ ሰማይ ዐረገ፡፡
በአባቱም ቀኝ ተቀመጠ
ዳግመኛም በሕያዋንና በሙታን
ለመፍረድ በምስጋና ይመጣል ለመንግስቱም ፍጻሜ የለውም፡፡


† ጉባኤ ቁስጠጥንጥንያ
በጉባኤው ላይ ትምህርታቸው የተወገዘባቸው መናፍቃን

† አቡናርዮስ ዘላዞቅያ ክህደት
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መለኮት የሥጋ በሆነች ነፍስ ብቻ ተተክቶ ሕማምን ስቅለትንና ሞትን ከሥጋ ጋር ተቀበለ ይላል፡፡በዚህ ብቻ አላበቃም መንፈስ ቅዱስ ትልቅ ነው ወልድ ከመንፈስ ቅዱስ ትልቅ ነው አብ ከሁሉ ትልቅ ነው ብሎ አስተምሮል፡፡

የአባቶች መልስ
ጌታ ነፍስ ያልተዋሐደው ነው ወይም በነፍስ ፈንታ መለኮት ከሥጋ ጋር ተዋሐደ ማለት የቤተ ክርስቲያንን የነገረ ድኅነት ትምህርት ጋር የሚቃረን ነው፡፡ ነፍስ የሌለውን ሥጋ ተዋሕዶ እንዴት የሰው ነፍስን ሊያድን ይችላል ብለው መልስ ሰጥተዋል፡፡
በሥላሴ መካከል መበላለጥ አለ የሚለው ትምህርት በጉባኤ ኒቅያም ጭምር የተወገዘ ነው፡፡ የጉባኤ ኒቅያ ትምህርት የሆነው ጸሎተ ሃይማኖት ‹‹ከአብ ጋር የሚተካከል ›› የሚለውን አንቀጽ የሚያነብ ሰው በቅድስት ሥላሴ መካከል የሥልጣን ልዩነት እንደሌለ በጉልህ ይረዳል፡፡ ይህ የአባቶች ትምህርት መጽሐፋዊ ሲሆን የመናፍቁ የአቡሊናርዮስ ትምህርት ግን የመጽሐፍ ማስረጃ የሌለው ተራ ክህደት ነው፡፡

† የአውሳብዩስ ትምህርት
እንደሰባርዩስ ትምህርት ሦስቱ አካላት በተለያዩ ሁኔታዎች የተገለጡ ናቸው፡ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ የምንለው ሦስቱ አካላት በተለያዩ ሁኔታዎች መገለጥ ነው እንጂ የተለያዩ አካል ያላቸው ሆነው አይደለም፡፡ ይህን ትምህርት በመቅዳት በኦሪት እንደ አብ በሐዲስ እንደ ወልድ በዘመነ ሐዋርያት ደግሞ እንደ መንፈስ ቅዱሰ የተገለጠው አንድ ነው የአካል ሦስትነት የለውም ብሎ አስተማረ፡፡11
ይህም ተራ ፍልስፍና ነው አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ፍጽም መልክ ፍጹም ገጽ ፍጽም አካል ያላቸው መሆኑን በሚያመለክት ሁኔታ በማቴ 3፡17 በተለያየ አምሳል በዩርዳኖስ ወንዝ ስለወልድ መመስከራቸው ምስክር ነው፡፡ (1ኛ ዮሐ 5፥12)

† የመቅዶንዩስ ትምህርት

ይህን ትምህርት ያሰራጨው መናፍቅ የአርዩስ ትምህርት ደጋፊ ነበር፡፡ ጌታችንን የካደውን አርዩስን የሚከተል ሰው መንፈስ ቅዱስን ቢክድ አይደንቅም፡፡ እንዲህም ብሎ ያስተምር ነበር፡፡ መንፈስ ቅዱስ በፍጥረታቱ ሁሉ የተሰራጨ የእግዚአብሔር ፍጡር ነው እንጂ በአብና በወልድ ደረጃ ያለ አይደለም በመላእክት መልክ ተፈጥሮ ከመላእክት ከፍ ያለ ነው ብሎ አስተማረ፡፡
አባቶቻችን የመቅዶንዩስን ትምህርት በማውገዝ የጸሎተ ሃይማኖት ክፍል ላይ ተጨማሪ ስለመንፈስ ቅዱስ የሚያወሱ ክፍሎችን ጨምረዋል፡፡ ይህ ምንፍቅና ተራ ፍልስፍና እንጂ መጽሐፋዊ አይደለም፡፡(1ኛ ዮሐ 5፥12)

† የኤፌሶን ጉባኤ

በጉባኤው ላይ ትምህርታቸው የተወገዘባቸው መናፍቃን

† ቢላግዩስ

የዚህ ሰው ክህደት የአዳም ኃጢአት ለልጆቹ አልተላለፈም፡፡ አንድ ሰው በሚወልድ ጊዜ ኣዳም ከኃጢአት ከመውቁ በፊት እንዳለ ሆኖ ይወለዳል፡፡በዚህም አንድ ሰው ወደ ከፍተኛ የቅድስና ደረጃ የሚደርሰው የእግዚአብሔርን እርዳታ ሳይጠይቅ ነው ብሎ አስተማረ፡፡13
ይህ ትምህርት የምሥጢረ ድኅነትን ትምህርት ዋጋ የሚያሳጣ ነው፡፡ አምላክ ሰው ስለምን ሆነ ብለን ብንጠይቅ መልስ ለመመለስ ይቸግረናል፡፡ ምክንያቱም ሁሉም ሰው ከኃጢአት ነጻ ሆኖ ይወለዳል ብሎ ያስተምራልና
መጽሐፍትም ይህን ትምህርት ትክክል እንዳልሆነ ይመሰክራሉ፡፡(መዝ 51፥3 ሮሜ5፥12 1ኛ ቆሮ 15፥22)

† ንስጥሮስ
የእግዚአብሔር ቃል ከሁሉ በፊት ነበረ መሆኑን አምናለሁ ማርያም የእምላክ እናት ነች የሚለውን አባባል ግን አላምንም፡፡ የክርስቶስ እናት መሆኗን አልክድም ነገር ግን እናትነቷ ለትስብእት ነው፡፡ ማርያም እግዚአብሔርን አልወለደችም ነገር ግን ከሥጋ የሚወለድ ሥጋ ነው ከመንፈስ የሚወለድ መንፈስ ነው፡፡ ፍጡር ሆና የወለደችው የእግዚአብሔር መሳርያ ፍጡር እንጂ ፈጣሪ አይደለም፡፡ በዚህም የተነሳ ጌታችን ሁለት ጠባይ ሁለት አካልና ሁለት ፍቃድ አለው፡፡ ሰብአ ሰገል ለጌታ መስገዳቸው አግባብ አይደለም ምክንያቱም ሕጻኑ ኢየሱስ ገና መለኮት ያልተዋሐደው ሥጋ ነውና፡፡(ማቴ 2፥11)
የአባቶች መልስ

ቅዱስ ቄርሎስ አባታችን እመቤታችን ወላዲተ አምላክ መባል እንደሚገባት አምላክንም እንደወለደች በጉባኤው ላይ አብራርቶል፡፡ የጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተዋሕዶ የከበረ ያለመለወጥ ያለመከፈል ያለኅድረት ሥጋና መለኮት መዋሐዳቸውን አንዱ የአንዱን ባሕርይ ገንዘብ ማድረጉን በስፋት አስተማረ፡፡ ሁለት ፍቃድ ሁለት ባሕርይ ሁለት አካል የሚለው የንስጥሮስ ትምህርትም በዚህ ጉባኤ ተወግዞል።

ይቆየን ይቀጥላል
ስብሐት ለእግዚአብሔር

No comments:

Post a Comment